በልዩ ፖሊስና በኦሮሞ አርሶ አደር በምእራብ ሐረርጌ ከፈተኛ ውጊያ እየተካሄድ ነው-ከ30በላይ ህይወት ጠፍታል

አባይ ሚዲያ
በወንድወሰን ተክሉ

በምስራቃዊው የኢትዮጵያ ክፍል በሶማሊ ክልል ልዩ ፖሊስ ሃይል በሚመራና በምእራብ ሐረርጌ ኦሮሞ አርሶ አደሮች መካከል ዓርብ መስከረም 1ቀን 2017 በተካሄደ ውጊያ ከአስራ በላይ ወታደሮችን ጨምሮ ከሰላሰ በላይ ሰዎች ህይወት ማለፈን ከስፍራው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የሱማሌ ክልል ፕሬዚዳንትና የህወሃት ልዩ አፍቃሪ በሆኑት አቶ አብዲ ሞሀመድ ኦማር የሚታዘዘው የክልሉ ልዩ ፖሊስ ሚሊሺያ በምስራቅ እና በምእራብ ሐረርጌ ባሉት 68 መንደሮች ይገባኛል ጥያቄን በማንሳት ባለፈው መጋቢት ወር ከመቶ በላይ ንጹሃን ያለቁበትን ወረራ ከፈጸመ በሃላ ክልሉ ሰላም ርቆት ነዋሪው በፍርሃት የተሞላ ህይወት የሚኖሩበት ክፍል እንደሆነ ይታወቃል።

ከሐሙስ ጀምሮ ለተከፈተው ከባድ ጦርነት መነሻው ምን እንደሆነ ባይገለጽም ጦርነቱ እየተካሄደ ካለበት ምእራብ ሐረርጌ ሚኤሶ ነዋሪዎች እንዳሉት በጣም የታጠቀው
የሱማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ ሚሊሺያ ከዚህ በፊት የኦሮሚያን መንደሮች በመውረር ሴቶቻን በመድፈር፣ከቦቶችን በመዝረፍ ተግባሩ አሁንም ለመዝረፍ ወረራ ሲፈጽም የኦሮሞ አርሶ አድርም ባለው ሃላ ቀር መሳሪያ እራሱን ለመከላከል ውጊያ መግጥሙን ይናገራሉ።

በዚሁ ምእራብ ሐረርጌ ዞን በተመሳሳይ የሱማሌው ልዩ ፖሊስ ሚሊሺያ ጥቃት የሰባት ሰው ህይወት ያለፈ ሲሆን በሐሙስና ዓርብ ጦርነት ከሞቱት 30በላይ ሰዎች ውስጥ የአጥቂው ሚሊሺያ አባላት ይኑሩበት ወይም አይኑረበት የተገለጸ ነገር የለም።

`የሱማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ ብዙዎች ጃንጃዊድ እያሉ የሚጠሩት ሚሊሺያ በ2007 በኦጋዴን ክልል የነበረውን የኦ.ብ.ነ.ግ ለመዋጋት በሚል በህወሃት መራሹ መንግስት የተቃቃመ ሚሊሺያ ሲሆን ታጣቂዎቹና የሚሊሺያው አመራር አባላት በሱማሊያ የነበረው የቀድሞው አሊተሃድ አል ኢስላሚያ [AIAI]እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። ሚሊሺያው ከተቃቃመ በሃላ በኦጋዴን ሕዝብ ላይ እጅግ አሰቃቂ የተባሉ የዘር ማጽዳት ጭፍጨፋን በማካሄድ ክልሉን እንዳጸዳ የሚነገርለት ሃይል ሲሆን በፕሬዚዳንት አብዱ መሀመድ ኦማር የቀጥታ ትእዛዝ ብቻ የሚንቀሳቀስ ሚሊሺያ እንደሆነ ይታወቃል።

በምእራብ ኦሮሚያ በሐረርጌ ምስራቅና ምእራብ ዞኖች ይገባኛል የሚለውን 68መንደሮች ለመቆጣጠር በጭካኔው የታወቀውን የሱማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ ሚሊሺያን በመጠቀም በተደጋጋሚ ግዜ ወረራዎችን በመፈጸም ከባድ ጉዳት በኦሮሞ ተወላጆች ላይ በማድረስ የገፋበት ቢሆንም የፌዴራሉ መንግስት በጉዳዩ ጣልቃ ገብቶ ግጭቱን ሲያስቆም እንዳልታየ ነዋሪዎቹ ይናገራሉ።
ባለፈው ሚያዚያ በኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ እና በሱማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ ሞሀመድ ኦማር መካከል ግጭቱን በሰላም ለመፍታት ስምምነት መደረጉ የተገለጸ ሲሆን በስምምነቱ መሰረት በነሀሴ 19ቀን 2017 በተደረገው ሁለተኛ ዙር ስብሰባ ከ68ቱ አወዛጋቢ መንደሮች ውስጥ 48ቱ በኦሮሚያ አስተዳደር ስር እንዲቀር ከስምምነት ተደርሳል መባሉ የሚዘነጋ አይደለም።

ሆኖም ብዙም ሳይቆይ የሱማሌው ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሀመድ የተስማሙበትን ውድቅ በማድረግ ቀደም ብሎ በነበረው ጥያቄ የ68ቱ መንደሮች አስተዳደር በጅጅጋ ስር መሆን አለበት በማለቱ የሰሞኑ ተከታታይ ውጊያዎች መፈጠር ምክንያት እንደሆነ ይታመናል።

ከምስራቅ ሐረርጌ ጉርጉሱም ያሉ የሀገር ሽማግሌዎች አዲስ አበባ ድረስ በመጋዝ ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ የሱማሌ ክልልን ልዩ ፖሊስ ሚሊሺያን ከግዛታቸው እንዲያወጡላቸውና ከወረራቸውም እንዲታቀቡ እንዲያዙላቸው ተማጽኖ ቢያቀርቡም ከጠ/ሚ/ሩ እሺታ በስተቀር የተግባር እርምጃ እንዳልተወሰደ ይናገራሉ።