ቻይና በደጃፌ ጦርነት እንዲነሳ አልፈቅድም ባለች ማግስት አሜሪካ፣ደ/ኮሪያና ጃፓን በሰሜን ላይ እርምጃ ለመውሰድ መከሩ

0

አባይ ሚዲያ
በወንድወሰን ተክሉ

ሐሙስ ነሀሴ 31ቀን 2017 ቻይና ደጃፍ በሆነኝ በኮሪያ ልሳነ ምድር ጦርነትም ሆነ ማህበራዊ ቀውስ እንዲነሳ አልፈቅድም ባለች ማግስት ደቡብ ኮሪያ ከአሜሪካን እና ጃፓን ጋር በሰሜን ላይ በሚወስዱት ወታደራዊ እርምጃ መምከራቸውን የሴኡል ምንጩን ጠቅሶ የዛሬይቱ ራሺያ ዜና ጣቢያ [RT]ዘገበ።
ሶስቱ ሀገሮች ባደረጉት ወታደራዊ ዘመቻቸው ምክክር ሌላ በአሜሪካን እና በደቡብ ኮሪያ መካከል አዲስ የሚሳይል ቴክኖሎጂ ስምምነትም መደረጉን ዜና ጣቢያው ገልጾ ስምምነቱ ደቡብ ኮሪያ አሁን ከታጠቀችው ባለ 800ኪ ሜ ርቀት ተወንጫፊ ሌላ ከፍ ያለ እርቀት የሚጋዝ ሚሳይል እንድታመርት ያደርጋታል ሲል ገልጻል።

በአሜሪካን እና በደቡብ ኮሪያ መካከል በ1972 ስምምነት መሰረት ደቡብ ኮሪያ በአሜሪካን ሚሳዪል ቴክኖሎጂ 180ኬ.ሜ ርቀት የሚወነጨፍ ማምረት እንደምትችል የሚፈቅድ ሲሆን ከግዜ በሃላ ከሰሜን ኮሪያ ተደጋጋሚ ትንኮሰ በሃላ ስምምነቱ ለብዙ ግዜ እየተከለሰ እስከ 800ኪ.ሜ ርቀት መጋዝ የሚችልና እስከ 500ኪ.ግ ክብደት የሚመዝን ሚሳዪል እንድታመርት መፍቀዱ ተግልጻል። ሆኖም አሁን በሰሜን ኮሪያ በኩል እየተሰነዘረ ያለው ማስፈራሪያ ያስበረገጋት አሜሪካ ለወዳጃ ደቡብ ኮሪያ ተጨማሪ ኪሎሜትሮችን መጋዝ የሚችል ሚሳዪል እንድታመርት የፈቀደችላት ሲሆን በቢሊዮን የሚቆጠር የጦር መሳሪያ ሽያጭ ስምምነትም ማድረጋቸውን ዘገባው ያብራራል።

በነሀሴ 29ቀን በሰሜን ኮሪያ ተተኩሶ በጃፓን ግዛት ሆካይዶ ዓየር ላይ በማለፍ በፓስፊክ ውቂያኖስ ከወደቀው የሰሜን ኮሪያ ቦለስቲክ ሚሳዪል ሙከራ በሃላ የኮሪያ ልሳነ ምድር ፖለቲካዊ ትኩሳት እለት በእለት እየጨመረ በመምጣት አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን ዘገባዎች ይጠቁማሉ።

የአሜሪካው መከላከያ ምኒስትር ጀምስ ማቲስ ከደቡብ ኮሪያ አቻቸው ሶንግ ዩንግ ሙ ጋር ባደረጉት ምስጢራዊ ምክክር በሴኡል በኩል በቀረበው ወታደራዊ ፕላን ዙሪያ ከስምምነት የደረሱ ሲሆን የውይይቱን ዝርዝር ፕላን ግን ከመናገር እንደተቆጠቡ ዘጋቢው ገልጻል።

ጎን ጎን ለጎን ደግሞ የአሜሪካ፣ደቡብ ኮሪያ እና የጃፓን ወታደሮችና ዓየር ሃይሎች ተካፋይ የሆኑበት ከፍተኛ ወታደራዊ ዝግጅትና ልምምድ ከእረቡእ ጀምሮ ላልፉት ሶስት ተከታታይ ቀናቶች በሰሜን ኮሪያ ድንበር አቅራቢያ እያካሄዱ እንዳሉ የተገለጸ ሲሆን ከአሜሪካን ዓየር ሃይል የኒውክሌር መሳሪያ ተሸካሚ የሆኑ [B-1B strategic bombers and four Marine Corps F-35Bs] ሁለት ተዋጊ ጄቶች እንደተሳተፉበት ተግልጻል።

ቀደም ሲል የሶስቱ ሀገሮች የጋራ [አሜሪካ፣ደቡብ ኮሪያና ጃፓን] የጋራ ወታደራዊ ጡንቻ ማሳያ ልምምድ ከመፈጸሙ በፊት ቻይና በመከላከያ ምኒስትር ቃል -አቀባዩ ሬን ጉጂያንግ በኩል የሶስቱን ሀገራት ወታደራዊ ዝግጁነት በማውገዝ “በኮሪያ ልሳነ ምድር ጦርነት እንዲነሳም ሆነ ማህብረሰባዊ ቀውስ እንዲፈጠር በፍጹም አልፈቅድም” በማለት ከረር ያለ አቃማን እንዳሳወቀች የተገለጸ ሲሆን አቃማ ከሞስኮ በኩል ድጋፍ ያስገኘ ቢሆንም በዋሽንግተን በኩል ግን የተሰጣት ምላሽ እንደሌለም ተገልጻል።
ሰሜን ኮሪያ በዚህ በያዝነው ዓመት ብቻ 14ግዜ ያህል የረጅምና መካከለኛ ርቀት ሚሳዪሎችን የተኮሰች ሲሆን አሜሪካና ደቡብ ኮሪያ የሚያደርጉትን የወረራ ወታደራዊ ልምምዳቸውን በመተው ለደህንነቴ ዋስትና እስካልሰጡኝ ድረስ እያጠናከርኩ ከመሄድ በስተቀር የምትውበት ምክንያት የለም በሚለው አቃማ በመጽናት ማምረቱንም ሆነ መለማመዱን ገፍታበታለች።

ቻይና እና ራሺያ ከደቡብ ኮሪያ በኩል ሆነው የጸጥታው ምክር ቤትም ሆነ አሜሪካም በተናጥል የሃይል እርምጃ በመጠቀም ቀውሱን ለመፍታት እንዳይወሰኑ አጥብቀው እየተከላከሉ ያሉ ሀገሮች ሲሆን በተለይ ራሺያ አሁን ከአሜሪካን ጋር ካለችበት ኢኮኖሚያዊያና ዲፕሎማሲያዊ ጦርት አንጻር ሞስኮን ከፒዮንጊያንግ ጋር ተሰልፋ እስከመዋጋት ሳያደርሳት አይቀርም ሲሉ የጦር ባለሙያዎች ይናገራሉ።

ራሺያና ቻይና በየብስ የሰሜን ኮሪያ ተጎራባች ሀገሮች ከመሆናቸው ባሻገር ሁለቱም ሀገራት በመጀመሪያው የ1950ኮሪያ ጦርነት ከዛሬዋ ሰሜን ኮሪያ ጋር ተሰልፈው ከአሜሪካን መራሹ ህብረት ጋር መዋጋታቸው አይዘነጋም።