ህወኃት ቤት ጥይት፣ ህዝብ ቤት ክብሪት አይጠፋም [በፀ/ት ፂዩን ዘማርያም]

እውቁ ፕሮፊስር አስራት ወልደየስ የኢትዩጵያ አባት፣ የሃገራችንን የፖለቲካ ትርፍ አንጀት በኦፕሬሽን ለማውጣት ሲሞክሩ የሽታው ደዌ ካንሰር እንደሆነና ካልተቆረጠ መዳን እንደማንችል አልገባንም ነበር፣ አባታችን በእስር ተሰቃይተው ተሠውልን፡፡ ካንሰሩ ከተስፋፋ የሃገር ሞት እንደማይቀር የተገዱ፣ ከሁለት አስርት በኃላ፣ ቆይቶ ጉዳዩ የገባቸው የአማራ ጀነራል መኮንኖች  የፕሮፊስር አስራት ጥያቄ በማንሳታቸው ለእስር ተዳረጉ፡፡ ቤተሰባቸው ተበተነ፣ የሚረዳቸው ወገንና አስታዋሺ አጡ፡፡ ዛሬ የኢትዩጵያ ህዝብ ከዳር እስከ ዳር ይሄን የወያኔን የፖለቲካ ካንሰር ለመቁረጥ ቆርጦ ተነስቶል፣ ለልጆቻችን መሬታችንን ተነጥቀን፣ ነጻነታችንን አጥተን፣ ባርነት ከማውረስ ሞት እንመርጣለን ብለው ለትግል ተነስተዋል፡፡ ምንም አይነት ምድራዊ ኃይል አይበግረንም፣ ‹‹ህወኃት ቤት ጥይት፣ህዝብ ቤት ክብሪት አይጠፋም!!!›› ለዚህ ነው የሚሉት፡፡

የቻይናውያኑ ዜድቲኢ እና ሀዊ  ካንፓኒዎች ከኢትዩጵያ የህዝብ ደህንነት መስሪያ ቤትና፣  ከኢትዩጵያ ቴሌኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬሽን ጋር የስለላ ሴራ በኢትዩጵያ ህዝብ ላይ ያከናውናሉ፡፡ የቻይና መንግሥት በኢትዩጵያ የስለላ መረቡን በዜድቲኢና ሀዊ ቴሌኮሙዩኒኬሽን በኩል የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥት በመደገፍና ህዝባዊውን ትግል በመሰለልና በማፈን ከፍተኛውን ድርሻ በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡ የቻይና ኮምኒስት ፓርቲ ንብረት የሆኑት፣ቻይና የቴሌኮም ካንፓኒ፤ዜድቲኢ ZTE Corporationና ሀዊ Huawei Technologies Co. Ltd. ድርጅቶች ለህወሃት/ኢህአዲግ መንግስት የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎት ዘርፍን ውስጥ በመሰለልና የሃገሪቱን ምስጢርና የተቃዋሚ ፓርቲዎችን በስለላ መረብ በማስገባት ከፍተኛ ጥቃት አድርሰዋል፡፡ ከዚህም ውስጥ በዋቢነት የሚጠቀሰው በ2009 ዓ/ም የሃገር ውስጥና ዓለም ዓቀፍ የስልክ ጥሪዎች የሰዎችን የስልክ ቁጥርን በመጥለፍ ለወያኔ መንግሥት ያበረከቱት የስለላ ሥራ በማስረጃ ይጠቀሳል፡፡ ዓለም ዓቀፍ የስልክ ጥሪዎች በመጥለፍ ከግንቦት ሰባት ፀሃፊና ሊቀመንበር ጋር የስልክ ግንኙነት አድርጋችኃል በማለት፡– 

1/ ከአንዳርጋቸው ጽጌ ጋር ያደረገው ግንኙነት

2/ ከብርሃኑ ነጋ ጋር ያደረገው ግንኙነት

እንዲሁም በሃገር ውስጥ የስልክ ጥሪዎች በማድረግ የምትገናኙት መንግሥት ለመገልበጥ እያሴራችሁ ነው፡፡ ከግንቦት ሰባት ጋር ትገናኛላችሁ ተብለው ለብዙ ወራቶች የስልክ መስመሮቻቸውን በመጥለፍ የሚያደርጉትን ንግግር በመቅዳት ህገ መንግሥታዊ መብታቸውን በመጣስ መንግስታዊ ስለላ ከተካሄደባቸው የአማራ ጀነራል መኮንኖችና የሲቨል ዜጎች ላይ የተፈፀመ ወንጀል ታሪክ የማይረሳው አንድ ቀን እነዚህ ጀግና የህዝብ ልጆች ለኢትዩጵያ ህዝብ ሲሉ የህወሃት/ኢህአዴግ መንግሥት የታገልንለት ህዝባዊ ዓላማን ሳተ፣ የታገልንው ለዚህ አይደለም በማለት በኢትዩጵያ መከላከያ ሠራዊት ስብሰባዎች በግልፅ ሲናገሩ እንደነበር ሠራዊቱ ያውቃል፡፡

  1 / ተፈራ ማሞ ጨርቆስ         2 / አሣምነው ፅጌ ተበጀ     
3 ሻለቃ አዱኛ አለማየሁ 4 ሻለቃ ፋናዬ ውቤ
5 ሌተናል ኮነሬል የሺዋስ ወርቁ 6 ሌተናል ኮነሬል የሺዋስ አጥናፉ
7 ይበልጣል አለማየሁ 8 ጀነራል ሃይሌ ጥላሁን         
9 ሻለቃ ተስፋዬ እንዳለ 10 ሻምበል ተመስገን ባይለየኝ
11 ሌተናል ኮነሬል ሰለሞን 12 ሙሉጌታ አድማሴ አበጋዝ
13 መሃመድ ጀማል 14 መንግሥቱ አበበ
15 መላኩ ተፈራ 16 ሻለቃ መኮንን ወርቁ
17 ጎሽራድ ፀጋው 18 ጎበና በላይ
19 ጌቱ ወልዴ 20 ገበያሁ አይችሉህም
21 እማዋይሽ አለሙ 22 ሻለቃ በላይ ይበልጣል
23 ሌ/ኮ አስቻለው አንባቸው አያሌው   24 ወ/ሳጂን አምራር ባያብል     
25 ሌ/ኮ አለሙ ጌትነት 26 ሻለቃ አዱኛ አስማማው     
27 አደፍርስ ፀጋው       28 መቶ አለቃ አባቡ
29 ሌተናል ኮነሬል ሰለሞን 30 ሌተናል ኮነሬል አለበል አማረ
  31 ጌቱ ወርቁ         32 እንደሻው እምሻው     
33 ሻለቃ አደፍርስ 34 ያረጋል ይማም
35 አወቀ አፈወርቅ 36 ጌትነት ወልደሰንበት

በኢትዩጵያ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ኢህዴን/ የጀነራል መኮንኖቹ ገድል በተለይ ብርጌደር ጀነራል ተፈራ ማሞ፣ ብ/ጄ አሣምነው ፅጌና ጀነራል ሃይሌ ጥላሁን የደርግን መንግሥት ለመጣል በተደረገ የሽምቅ ውጊያ ትግል ታሪክ በኢህዴን ዓመታዊ የምስረታ በዓል ላይ ገድላቸው ሲተረክና ሲወጋ እንደነበር የኢትዩጵያ ቴሌቨዚንና ሬዲዩ ጣቢያ ገሃድ ምስክሮች ናቸው፡፡          

 ህብረ-ብሄር የነበረው የኢትዩጵያ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ኢህዴን/ ወደ ብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ብአዴን/በዘር ሲከለስና ሲቸለስ እነዚህ የወሎ፣ የሸዋ፣ የጎንደር፣ የጎጃም አማሮች ነገሩ እየጎረበጣቸው እንዴት ከኢትዩጵያዊ ህብረ-ብሄር አመለካከት ወርደን ስለ አማራ ዘውግ/ዘር እንድናስብ እንደረጋለን? እንዴት ከኢትዩጵያዊ ብሄርተኝነት ወርደን የዘውግ/ዘር ክልላዊነት ጥላ እንይዛለን? እንዴት ከዓለም ዓቀፋዊነት እምነት ወርደን ብሄርተኝነት ወርደን ክልላዊነት እንጠባለን? ከዓለም ዓቀፋዊነት/ኢንተርናሽናሊዝም በዘመርንበት አንደበት የክልላዊነት ልሣን እንዘምራለን?  እንዴት ሶሻሊዝምን ትተን ካፒታሊዝምን እንጋታለን እናንተ ማርክሲዝምን ለ17 ዓመታት ግታችሁን ዛሬ ድል አርገን ስንገባ ነጭ ካፒታሊዝምን ታስታውኩብናላችሁ? ብለው በግዜው የተሞገቱ፣ የዋህ እውነተኛ የሃገሪቱ ልጆች ነበሩ፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር ታምራት ላይኔ ‹‹በሙስናና በሌብነት›› ወያኔ በየስብሰባው ሲለን  ከድርጅቱ አሳልፈን ሰጠንው፣ የህዝብ ቃልኪዳንና የተሰውትን ሰማዕታት ቃል ባለማክበሩ አሳልፈን ሰጠንው!!! በህወኃት/ ኢህአዴግ መንግሥት በማመን ከጫካ ትግል ጀምረው ለዚህ ስልጣን የደረሱት ጀነራል መኮንኖች ቃል በገቡትን መሠረት በሃቅ ለሃገርና ለወገን በማገልገል ተጎዙ፡፡

ጀነራል መኮንኖቹ ብሄረ አማራን ለማቅናት ደፋ ቀና ሲሉ፣ አንድ ቀን ዞር ሲሉ ጥላቸው የለም? የአማራው ክልል ህዝብ የጤና፣ የመብራት፣ የውሃ አገልግሎት የለውም፡፡ የመንገድ መሠረተ ልማት አልተዘረጋለትም፡፡ የትምህርት አገልግሎት  ተቆማትም አልተሞሉለትም!!! በአማራ ክልል የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ በኩልም፣የኤሌትሪክ ኃይል አገልግሎት ባለማግኘታቸው  ወደ ሥራ መግባት ያልቻሉ ኢንቨስተሮች ቁጥር የትየለሌ መሆኑን ታዘቡ፡፡

የጀነራል መኮንኖቹ በኢህአዴግ ጉባዔዎችና በመከላከያ ሠራዊቱ ስብሰባዎች ላይ ባነሱት ጥያቄዎች የበላይ አለቆቻቸውን ይጠይቁ ጀመረ፣ በሠራዊቱ ውስጥ የትግራይ የበላይነት እያደገ መጥቶል! በሠራዊቱ አመራር መኮንኖች፣ የተባለው የብሄር ብሄረስብ ተዋፅኦ ተግባራዊ አልሆነም፡፡ በሠራዊቱ ውስጥ በተለይ በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ውስጥ የሙስናና ንቅዘት፣የዝምድና የመጠቃቀም ሥራ በዝቶል ይስተካከል፡፡ በአፍሪካ ውስጥ፣ የኢትዩጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ሆነው በሰላም አስከባሪነት የሚሄዱት በአመዛኙ የትግራይ የሰራዊቱ አባላቶች ናቸው ከሌሎቹም ብሄር ብሄረሰብ የሠራዊቱ አባላቶች ቅሬታና ጥያቄ አስከትሎል በአስቸኮይ ይስተካከል፡፡ ሰላም አስከባሪ ኃይል በአፍሪካ ሃገራት በአስከባሪነት ከሚላኩ ወታደሮች  የጉቦና የዝምድና ሥራ ይብቃ፣የኢትዩጵያ መከላከያ ሠራዊት በወታደራዊ ሣይንስ አመራር ችሎታ ያላቸው መሪዎች ይመራ የሚሉ ጥያቄዎች አቅርበዋል፡፡

በህወኃት/ኢህአዴግ መለስ ዜናዊ ስካር ይሁን ስካEር? ዴሞክራሲ አረገ አላቸው፡፡ ከትቢያ አንስተን ሰው አረግናችሁ ሊያውም ጀነራል መኮንኖች! ቪላ ቤት ሠጠናችሁ! መኪና ከአንድም ሦስት ሠጠናችሁ!!! መሬት መራናቸው!!! ሸራተን፣ሂልተን ወዘተ ቤታችሁ አደረጋችሁ!!! እናም እኔን ለመገልበጥ ታሴሩ ጀመር?  አላቸው፣ ጀነራል መኮንኖቹ የጠፋባቸውን ጥላቸውን አዩት! ‹‹አስራ ሰባት አመታት የታገልነው ለፍትህ፣ ለእኩልነትና ለነፃነት ነው? ስንት ጎዶች መሠዋት ሆነዋል? እኛ ለሆዳችን አይደለም የምንኖረው? እኛ የህዝብ ልጆች ነን? ያን ሁሉ ዘመን የተጋትነው ፖለቲካ ለግል ጥቅም ነውን? እናንተን ቤተ መንግሥት ለማስገባት ስንት ሰው አለቀ፡፡››አሉት!!! እነዚህ የአማራ ጀነራል መኮንኖቹ  በሠራዊቱ ውስጥ ያለ የዘር አድሎ፣ የእድገት አድሎ፣ የክልላዊነት የቡድን ሥራ ይቁም፣ ወዘተ የሚሉ የሰራዊቱ ጥያቄን በመጠየቃቸው ብዙዎቹ አማራዎች  ከስራ ገበታቸው በመለስ ዜናዊ ቀጭን ትእዛዝ ተባረሩ፡፡

ህዝባዊ ዴሞክራቲክ ጋርድ፡- የቻይና ኮምኒስት ፓርቲ ንብረት የሆኑት፣ የቻይና ቴሌኮም ካንፓኒ፤ ዜድቲኢና ሀዊ ድርጅቶች ለህወሃት/ኢህአዲግ መንግስት የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎት ዘርፍ ውስጥ በመሰለልና የሃገሪቱን ምስጢርና የተቃዋሚ ፓርቲዎችን በስለላ መረብ በማስገባት ከፍተኛ ጥቃት በማድረሳቸው የአንድ ወር የሞባይል ስልክና ካርድ ያለመጠቀም አድማ እንዲደረግ ለአስተባባሪዎቹ ህዝባዊ ጥያቄ አቅርበናል፡፡

የኢትዩጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ የቴሌኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት በ14 ጁላይ 2009 እኤአ የሰዎችን የስልክ ንግግሮች ጠልፎ ለፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ መምሪያ (የወንጀል መዝገብ ቤት) በማስረከብ በተከሳሾቹ ላይ ፍርድ ቤት እንደማስረጃ ተቆጥሮ ባደረጉት የስልክ ንግግር ብቻ ስለምን ጉዳይ እንደተወያዩ ሳይገለፅ በመንግሥት መገልበጥ ወንጀለኛ ተብለው በአሰቃቂ ግርፋትና ድብደባ ተደርጎባቸው እስካሁን በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ የቻይናውያኑ ዜድቲኢ እና ሀዊ  ካንፓኒዎችና የቴሌኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት የጠለፈውን የስልክ ንግግሮች የያዘ የስለላ ሠነድ ከመኃተምና ከፊርማ ጋር ተያይዞ በማስረጃነት ቀርቦል፣ እያነበቡ የቴሌን ጆሮ ጠቢዎች ጠንቀቅ ይበሉ፡፡

የኢትዩጵያ መከላከያ ሠራዊት አፈሙዝህን ወደ ወያኔ አዙር!!!

ኢትዩጵያ የህዝቦች እስር ቤት!!!

ከኦሮሚያ ፕሮፊስር መራራ ጉዲና፣ በቀለ ገርባና ሌሎችም ይፈቱ!!!

ከወልቃይት ኮለኔል ደመቀ ዘውዴ ሌሎችም ይፈቱ!!!

ከጋምቤላ ቱወት ፖል ሌሎችም ይፈቱ!!!

ከኦጋዴን አብዲከሪም ሼህ ሙሴ ሌሎችም ይፈቱ!!!

ለኢትዩጵያ ከፍታ፣ ለወያኔ ዝቅታ

‹‹ወያኔ ቤት የፍቅር ቀን፣ ህዝብ ቤት የሐዘን ቀን››

ለተጨማሪ  የቻይናውያኑ ዜድቲኢ እና ሀዊ  ካንፓኒዎችና የቴሌኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት የጠለፈውን የስልክ ንግግሮች የያዘ የስለላ ሠነድ  ለማንበብ የሚቀጥለውን አስፈንጣሪ ይጫኑ።

ethiotelecom-part-ii