በሐረር የኦሮሞ ተወላጆች ተቃውሞ ማሰማታቸው ተነገረ

አባይ ሚዲያ ዜና
በአሰግድ ታመነ

በሃረር ከተማ ዙሪያ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ የድሬ ጥያራ ወረዳ ነዋሪዎች በዛሬው ለት ከኦህዴድ ባለስልጣናት ጋር ባደረጉት ስብሰባ በተቃውሞና በረብሻ ስብሰባውን ማቃረታቸው ተነገረ።

ይህንን ተከትሎ፣ እኛ እስከ ጀጎል ድረስ ገብተን “ማንነታችንን እናስከብራለን” ያሉ የኦሮሞ ወጣቶች ወደ ሃረር ከተማ በተቃውሞ መጋዛቸውም ተነግራል።

“ ሃረር የእኛ” የሚሉና ሌሎችንም የሃረሪ ሊግ ባለስልጣናት የሚያወግዙ መፈክሮችን በማሰማት እየተጓዙ እያለ፣ በአመሬሳ በኩል ወደ ሃረር
ከተማ ለመግባት 5 ኪሎ ሜትር ያክል ሲቀራቸው ፣ ሙጢ የተባለው ቀበሌ ላይ የኦህዴድ ባለስልጣናት “ ለጥያቄያችሁ አፋጣኝ መልስ እንሰጣለን፣ ወደ ከተማ አትግቡ” በማለት ለምነውና ተማጽነው ህዝቡ ወደ ከተማ እንዳይገባ ማድረጋቸው ተነግራል።

የተወሰኑ ወጣቶች ግን በተለያዩ አቅጣጫዎች በመኪና ተጉዘው ወደ ከተማ መግባት የቻሉ ሲሆን፣ “ሃረር የእኛ” የሚልና የሀረሪ ሊግ
ባለስልጣናትን የሚያወግዙ መፈክሮችን አሰምተውና የኦሮምያ ክልል አርማን ሰቅለው ወጥተዋል ተብላል።

ይህ የወያኔ የሚከተለው ቋንቋን መሰረት ያደረገ አከላለን በሀገሪትዋ ላይ ሊፈትር የሚችለው ህውከት አሁን እየታየ ነው ተብላል።