ሁሉም መብቶች ለሁሉም (በአብራሃም ለቤዛ)

0

ዘር፣ ቀለም፣ ሃይማኖት በሰብዓዊነት ተተክቶ
ሕይወት ክቡር ሁና ደህንነቶ ፀንቶ
ብዝበዛ፣ ጭቆና፣ ሽኩቻ ከአገር ተወግዶ
አገር ሰላም ሁና ፍትህ እኩልነት ሁሉም ተዋህዶ

በእምየ ኢትዮጵያ መቼ ነው የማየው?

ዴሞክራሲ ሰፍኖ ህግ የበላይ ሁኖ
በሰላማዊ ትግል ስልጣን ከህዝብ መጥቶ
ገደብ ተቀምጦ ተጠያቂነት ጎልቶ
ፍርድ ነፃ ሁኖ ጣልቃ ገብነት ቀርቶ

በእምየ ኢትዮጵያ መቼ ነው የማየው?

ሃይማኖት፣ ባህል፣ ቋንቋ ሆነው ጌጦቻችን
አንዱ አንዱን ሳይኮንን ሳይሆኑ ሳንካችን
ሰብዓዊነትን ሰብከው እውቀትን አስፋፍተው
ፍቅርን አጎልብተው ሰላምን አፍርተው

በእምየ ኢትዮጵያ መቼ ነው የማየው?

ዛሬ ሌላው ዓለም ተራቆ  ዲሞክራሲ ጎልብቶ
ሰላም ደህንነቱን ለህግ አደራ ሰጥቶ
ህግ የበላይ ሁኖ ፍትህ አስገኝቶ
ሰርተው ይኖራሉ አደራቸው ወጥቶ
በኢትዮጵያ ምድር በአፍሪካችን አህጉር
የዴሞክራሲ እጦጥ የፍትህ ባይተዋርነት
ልማትም ህልም ሁኗል ደህነትም ቅዠት
ረሃብ፣ በሽታ፣ ድንቁርና ጦርነት ሆነውናል ሕይወት
ይህ ሁሉ ተወግዶ ሰብዓዊነት ለምልሞ

በእምየ አፍሪካ  መቼ ነው የማየው?

ህዳር 21/ 19 99 ዓ/ም