ሃሪኬን ኢርማ የካረቢያን ምድራዊ ገነቶችን ወደ ትቢያነት ለወጠ-ፍሎሪዳውያን ሽሽት ጀምረዋል

0

አባይ ሚዲያ
በወንድወሰን ተክሉ

በሃይለኝነቱ ወደር የለውም የተባለለት ሃያሉ ሃሪኬን ኢርማ የሀብታም ባለጸጎች፣ የታወቁ የሆሊውድ አክተሮች መዝናኛነት ከዓለም ተመራጭ የሚባሉትን የካረቢያን ደሴቶች በአውዳሚ አውሎ ንፋስ፣ ዝናብና ጎርፍ ክፉኛ መውደማቸውን የዓለም የመገናኛ ብዙሃን በቀዳሚ ዜናነት እየገለጹ ሲሆን ነገ ቅዳሜ መስከረም 9 ቀን 2017 ይደርስባቸዋል የተባሉት የፍሎሪዳ ነዋሪዎች የቻሉት ከተማዋን በመልቀቅ ሽሽት መጀመረቻውም እየተዘገበ ይገኛል።

በሜቲኦሮሎጂስቶች በደረጃ አምስት የተመደበው እና በሰዓት 297 ኪሎ ሜትር እሚምዘገዘገው ሃሪኬን ኢርማ በካረቢያን ያሉትን አብዛኛ ደሴቶችን እስከ 90% ድረስ ያወደመ መሆኑን እየተገለጸ ሲሆን በእስከ አሁን ሂደቱ የ11 ሰዎችን ህልፈተ ህይወት ማወቅ የተቻለ ሲሆን የተጎጂዎቹ ቁጥር በእጅጉ እንደሚጨምር የአደጋ ግዜ ደራሾች እየገለጹ ነው።

image
የቨርጂን አትላንቲክ አየር መንገድ ባለቤት የሆነው እንግሊዛዊው ሪቻርድ ብራንሰን በኒከር ደሴት ለመዝናኛ በገነባው የመንፈላሰሻ ቪላ ቤቱ እያለ የአደጋውን ሁኔታ በቲዊተሩ “ከልጅነቴ ጀምሮ እንደዚህ ዓየነት እንቅልፋ አልባ ለሊቶችን አሳልፌ አላውቅም” ሲል ገልጿል።

እንደነ ብሪቲሽ ቨርጂን ደሴት፣ ቅዱስ ማርቲን፣ የአሜሪካ ቨርጂን ደሴትና ታላላቅ የተባሉትንም ደሴቶች ያላቸውን መሰረተ ልማት ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል መልኩ ሃሪኬን ኢርማ ማውደሙን ዘገባዎች ይጠቁማሉ።

የአሜሪካዊቷ ፍሎሪዳ ሀገረ ገዢ ሪክ እስኮት የፍሎሪዳ ከተማ ነዋሪዎች በተለይም ሃሪኬኑ በቅድሚያ ያርፍባቸዋል ተብሎ የተነገረላቸውን እንደነ ትራክና ካይኮስ ደሴት ነዋሪዎች ስፍራውን ለቀው እንዲሸሹ ጥብቅ ትእዛዝ የሰጡ ሲሆን ሃሪኬኑ ነገ ይደርሳል ተብሎ ተገምቷል።

image
የካረቢያን ደሴቶች በመዝናኛ ስፍራነታቸው እጅግ የተመረጡ ሲሆኑ በዓለም ላይ ላሉ ታዋቂ ሰዎች፣ ባለጸጋ ቢሊየነሮች መምነሽነሻነት የሚያገልግሉ ድንቅ የመዝናኛ ስፍራዎች እንደሆኑ ይታወቃል።