የቃሊቲ እስር ቤት ኮማንደር የአገዛዙን ጡንቻ በአዲስ አመትም ለማሳየት መሞከሩ ተገለጸ

0

አባይ ሚዲያ ዜና
አቢሰሎም ፍሰሃ

2010 ዘመን መለወጫን ታዋቂ ግለሰቦች እና የሃይማኖት አባቶች በእስር የሚገኙትን እንዲጎበኙ አዋጅ መሰል ትዕዛዝ ቢተላለፍም የነፃነት ታጋይ እና የእድሜ ልክ ፍርደኛ የሆኑትን ወ/ሮ እማዋይሽ አለሙን በአውዳመት ቀን ምንም ዘመድ ወይም ወዳጅ እንዳይጠይቋት የእስር ቤቱ ኮማንደር ማድረጉ ተሰማ።

ወ/ሮ እማዋይሽ አለሙ ከሚቀበሉት በደልና መከራ በላይ በአውድአመት ጊዜም ወዳጅ ዘመድ እንዳያያቸው መደረጉ የአገዛዙ የጡንቻ ጥንካሬ ማሳያ ተግባር ከፍታ እንደሆነ በግልፅ ያሳየ አጋጣሚ እንሆነ አስተያየት ሰጪዎች እየተናገሩ ይገኛሉ ፡፡

ከተመዘገቡ ሰዎች ውጭ መጠየቅ አይቻልም የተባሉ ጠያቂዎቿ ከነ እቃቸው ወ/ሮ እማዋይሽን ሳያገኙ መመለሳቸውም ተገልጿል፡፡

በሌላ ዜና ላለፉት ወራቶች ህዝቡን ለተለያዩ አድማዎች እና እስር እንዲዳረግ ምክንያት የሆነውን የቀን ገቢ ግምት ግብር ሐ እርከን ከነገ ጀምሮ እንደገና እንደአዲስ እንደሚታይላቸው አንዳንድ ያነጋገርናቸው ነጋዴዎች ይገልጻሉ።