የኢህአዴግ የግል ባንኮችና ኢንሹራንሶች!!! የላጪን ልጅ ቅማል በላት (በፀ/ት ፂዩን ዘማርያም)

0

(ክፍል ሁለት)

የህወኃት/ኢህአዴግ መንግሥት ወንዝ አፈራሽ፣ ዘር አፈራሽ የጡብና አዳፍኔ ዘመን ባንኮች በብሄር፣ በፓርቲና ሃይማኖት ተኮር ሆነው መመሥረታቸው የሃገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ በመቋጣጠር፣የባንክ ሥራ እውቀትን፤በዘር ተኮርነት በማዋቀር የትግራይ ባንክ፣ የኦሮሞ ባንክ፣ የአማራ ባንክ፣ የደቡብ ባንክ ወዘተ በማለት የአንድ ብሄር ቆንቆ ተናጋሪ ሙያተኞች በመቅጠር ኃለቀርነታቸውን በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ያስመሠከሩ ማህይሞች ናቸው፡፡ በአፄ ምኒሊክ ዘመነ መንግሥት በ1906 እኤአ የተመሰረተው አቢሲንያ ባንክ ህብረ-ብሄር ሙያተኞችን አብሮ ያሠራና ስንት ስመ ጥሩ የባንክ ሙያተኞችን ያፈራ እንደነበር ታሪክ ይመሠክራል፡፡ ከዛን ዘመን ጀምሮ ባንኮችና የባንክ ሠራተኞች በዕውቀት የተካኑ፣ የባንኩ ደንበኞች በሚሰጦቸው አገልግሎቶች በመርካትና የባንክ ሙያተኞች  በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትና ታላቅ እምነት ያሳደሩ ነበር፡፡ በሃገሪቱ ህግና ደንብ መሠረት ባንኮች የሚቋቋሙት በባለ አክሲዩኖች ሲሆን ከዘር፣ ከሃይማኖትና ከፖለቲካ ነፃ ሆነው የህዝብ አገልጋይ እንዲሆኑ ነው፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች በንግድ ዘርፍ ውስጥ መሳተፍ እንደሌለባቸው የኢትዩጵያ ህገ-መንግሥት ደንግጎል፡፡ ከህወሓት/ኢህአዴግ የፖለቲካ ፓርቲዎች በኢትዩጵያ ኢኮኖሚን የፋይናንስ ዘርፍ በመቆጣጠር  ፓርቲዎች የሃገሪቱን ባንኮችና ኢንሹራንሶች 75 በመቶ ኃብት ድርሻ ይዘዋል፡፡ በግሉ ዘርፍ ኢኮኖሚ የፋይናንስ ባንክና ኢንሹራንስ ዘርፍ ውስጥ፤ ያላቸውን ድርሻ እንቃኛለን፡-

  • ህዝባዊ ወያኔ ሃርነነት ትግራይ (ህወኃት) ንብረት የሆነው የትግራዩ ኢፈርት፣ ወጋገን ባንክ፣ ፀሃይ ኢንሹራንስ፣አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ ንብ ኢንሹራንስ፣ እናት ባንክ፣ ናሽናል ኢንሹራንስ ይገኙበታል፡፡
  • የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ንብረት የሆነው የአማራው ጥረት አባይ ባንክ፣ አባይ ኢንሹራንስ፣
  • የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ንብረት የሆነው የኦሮሚያው ቱምሳ የኦሮሚያ ህብረት ባንክ፣ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ፣
  • የደቡብ ኢትዩጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ለደኢሕዴግ) ንብረት የሆነው የደቡቡ ወንዶ ደቡብ ግሎባል ባንክ፣ ሉሲ ኢንሹራንስ በሚል ስያሜ የሃገሪቱን የባንክና ኢንሹራንስ ድርጅቶችን ተቆጣጠረዋል፡፡

እነዚህ ከህወሓት/ኢህአዴግ ፓርቲዎች ንብረት የሆኑ የአውራው ፓርቲ የባንክና ኢንሹራንስ ድርጅቶች የኢትጵያን ብሄራዊ ባንክ በማዘዝ የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ፣ የኢትዩጵያ ልማት ባንክ፣ የኮንስትራክሽን ቢዝነስ ባንክ ተቆጣጥረው ለከፍተኛ ኪሳራ ዳርገዋል፡፡ ቶማስ ጃፈርሰን እንዳሉት ‹‹በእኔ እምነት መሠረት የባንክ ኢንስቲቲውሽንስ ወይም ተቋማት ለእኛ ነፃነት በጣም አደገኞች ናቸው፣ ከመደበኛው ጦርሠራዊት የበለጠ/ይልቅ!!›› ይላሉ፡፡“I believe that banking institutions are more dangerous to our liberties than standing armies.” ― Thomas Jefferson

የኢትዩጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የባንክና ኢንሹራንስ ንግድ ኢንተርፕራይዝ

{1}ኢፈርት The Endowment Fund For The Rehabilitation of Tigrai (EFFORT) አንደኛው በህወሃት የፖለቲካ ድርጅት የሃብት ቁጥጥር ስር የሚገኘው (ትእምት)  የሚባል የንግድ ድርጅት በ1987 ሲሆን የዚህም የሃብት ምንጭ ህወሃት በሽፍትነት ለአስራ ሰባት ዓመታት ከኢትዬጵያ ህዝብ የዘረፈው ሃብት ነው፡፡ ኢፈርት ሁለት ክንፎች አሉት አንደኛው ክንፉ የኢንቨስትመንት መዓከል ሲሆን ሁለተኛው ክንፉ ደግሞ በጎአድራጎት ማዕከል ናቸው፡፡ የኢፈርት የኢንቨስትመንት መዓከል በ14 የተለያዩ ካንፓኒዎች የተደራጅ ናቸው፡፡ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የኢኮኖሚ ምሶሶ የሆነው ኢፈርት የቢዝነስ ኢምፓየር በኢትዬጵያ የግሉን ዘርፍ ባለኃብት በመቀናቀንና ሥራዎችን በመንጠቅ የሃገሪቱን ኃብት በሞኖፖል የሚቋጣጠር የህቡዕ ወይም ሚስጥራዊ ስውር ድርጁት ነው፡፡  የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ በ1991እኤአ በትረ ስልጣኑን ከደርግ እንደተረከበ ማረት በእርዳታና መልሶ ማቋቋም ማስተባበሪያ ኮሚሽን በበጎ አድራጎት ድርጅት(“NGO”) ስም ተመዝግቦ  የህወሓት መንግስት የገንዘብ ድጋፍ በጡጦ እየተጋተ ከአፍሪካ አህጉር ውስጥ በኃብት ትልቁ ኤንጂኦ ለመሆን በቃ፡፡ በ1995 እኤአ ህወሓት ለማረት ብረት መዝጊያና ጠንካራ አጋር ድርጅት መሠረተለት፣ትግራይ እንዶንመንት (EFFORT), የተቋቋመበት የኢንቨስትመንት የቢዝነስ ዶሴ ኢፈርት በሁለት ነጥብ ሰባት (2.7) ቢልዩን ብር መሆኑን ገልፆ በማግስቱ አንድ ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር መሆኑ ተገልፆል፡፡

የክልል መንግስታት የጋራ የንግድ ኢንዶንመንት ካንፓኒዎች (Joint endowment-linked companies)

የክልል መንግስታት የጋራ የንግድ ኢንዶንመንት ካንፓኒዎች ኢፈርት የትግራይ፣ጥረት የአማራ፣ ቱምሳ ኦሮሚያና ወንዶ የደቡብ የክልል መንግስታት የህብረት የንግድ ድርጅቶች ናቸው፡፡ እነሱም 1ኛ/ ወጋጋን ባንክ፣ 2ኛ/አፍሪካ ኢንሹራንስ 3ኛ/ሜጋ ፓብሊሽንግ 4ኛ/ ዋልታ መረጃ መዕከል 5ኛ/ ፋና ሬዲዩ ያካትታል፡፡ የትግራዩ ኢፈርት ከአንድ እስከ አራት የተዘረዘሩትን ኃብቶች የግሉ አድርጎቸዋል፡፡ የህወኃት የወጋጋን ባንክና አፍሪካ ኢንሹራንስ ንግድ ኢንተርፕራይዝ ሙሉ በሙሉ የግሉ አድርጎል፡፡

ወጋጋን ባንክ፣(Wegagen Bank)ወጋጋን ባንክ በ1997እኤአ ሲቋቋም  ኢፈርት 15 በመቶ  ሼር ነበረው፡፡ የኢትጵያ ህግ አንድ ኢንቬስተር 5 በመቶ ሼር ብቻ መሸፈን እንዳለበት ህግ በመደንገጉ ኢፈርትና የሌሎቹም  ሼር 4 በመቶ ሆነ፡፡ በ2010 እኤአ ወጋጋን ባንክ 223 ሚሊዩን ብር ከታክስ በኃላ ትርፍና 23 በመቶ እድገት ማግኘቱን አስታውቆል፡፡  ወጋጋን ባንክ የተቋቋመበት የተከፈለ ካፒታል 633 ሚሊዩን ብር በመሆን በሃገሪቱ ካሉት ባንኮች ትልቁ መሆን ችሎል፡፡ ወጋጋን ባንክ 3.8 ቢሊዩን ብር ተቀማጭ ገንዘብ ያለው ሲሆን ብድር የማበደር  አቅሙ ስፊ መሆኑ  ይስተዋላል፡፡

አፍሪካ ኢንሹራንስ(Africa Insurance in the financial sector) አፍሪካ ኢንሹራንስ ሁለተኛው የፋይናንሻል ዘርፍ ካንፓኒው ሲሆን በ2009/10እኤአ 19 ሚሊዩን ብር የተጣራ ትርፍ አግኝቶል፡፡ አፍሪካ ኢንሹራንስ 291 ሚሊዩን ብር አጠቃላይ ንብረት እንዳለው ተገልፆል፡፡ በመላ ሃገሪቱ ውስጥ 15 ቅርንጫፍች አሉት፡፡ አፍሪካ ኢንሹራንስ 40 ሚሊዩን ብር ሼር በወጋጋን ባንክ አለው፡፡በኢትዩጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ የኢትዩጵያ የግል ባንኮች የፋይናንስ ዘርፍ በመቋጣጠር ከህወሓት/ኢህአዴግ ፓርቲዎች የሃገሪቱን ባንኮች ኃብትን ከሚቋጣጠሩት ውስጥ  የትግራዩ ኢፈርት ወጋገን ባንክ፣ ፀሃይ ኢንሹራንስ፣አንበሳ ኢንተርናሽናል  ባንክ፣ንብ ኢንሹራንስ፣ እናት ባንክ፣ ናሽናል ኢንሹራንስ ይገኙበታል፡፡ ከሠንጠረጁ ላይ 2014/15 ገቢያቸውን ማስተዋል ይቻላል፡፡

ተ/ቁ የባንኩ ስም የባንኮች ትርፍ በኢትዩጵያ ብር (2014/15) የኢንሹራንሰ ስም ኢንሹራንስ ትርፍ

በኢትዩጵያ ብር

(2014/15)

1 አባይ ባንክ 125.0 አባይ 26.8
2 አዲስ ኢንተርናሽናል  ባንክ 44.6 አዋሽ 64.3
3 አዋሽ ባንክ 639.0 ብርሃን 3.4
4 አቢሲኒያ ባንክ 270.7 አፍሪካ 37.0
5 ብርሃን ኢንተርኛሽናል ባንክ 104.5 ቡና 7.8
6 ቡና ኢንተርናሽናል  ባንክ 134.5 ኢትዩጵያን 60.3
7 የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ 907.0 ኢትዩላይፍ 8.6
8 የኦሮሚያ ህብረት ባንክ
9 ዳሽን ባንክ 729.3 ላየን 13.1
10 ደቡብ ግሎባል ባንክ 18.5 ሉሲ 8.5
11 የኢትዩጵያ ልማት ባንክ
12 እናት ባንክ 53.0 ናሽናል 28.0
13 አንበሳ ኢንተርናሽናል  ባንክ 200.0 ንብ 62.3
14 ንብ ኢንተርናሽናል  ባንክ 337.1 ኒያላ 64.9
15 ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል  ባንክ
16 ህብረት ባንክ 281.0 ኦሮሚያ 100.0
17 ወጋገን ባንክ 352.4 ፀሃይ 45.8
18 ዘመን ባንክ 128.0 ዩናይትድ 62.3
ጠቅላላ 14,425,000,000

የክልላዊ ፖለቲካ ፓርቲዎች የባንክና ኢንሹራንስ ንግድ ኢንተርፕራይዝ

የክልላዊ መንግስቶች የፓርቲ ንግድ ኢንተርፕራይዝ (Regional state-owned enterprise (RSOE) sector)

የኢህአዴግ ፓርቲዎች የንግድ ድርጅቶችና ክልላዊ የልማት ድርጅቶች (Regional development organizations &  endowment-owned businesses) ከህወሓት/ኢህአዴግ ፓርቲዎች የተወረሱ የንግድ ድርጅቶች በፓርቲዎች በስጦታ ወይም በችሮታ የተላለፉ የንግድ ድርጅቶች እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡ የህወሓት/ኢህአዴግ ፓርቲና ቢዝነስ (የንግድ ሥራ) እጅና ጎንት በመሆን የግሉን ዘርፍ ደፈጠጡት፡፡በህወሓት መንግስት የቢዝነስና የፖለቲካ ጣምራ ግንኙነቶች በልማታዊ መንግሥት ስም ከ1991እኤአ ጀምሮ በኢትዩጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ከህወሓት/ኢህአዴግ ፓርቲዎች ተወርሰው ሙሉ በሙሉ የፓርቲያቸው ንብርትና ኃብት አደረጉ፡፡ ኢፈርት በትግራይ፣ ጥረት በአማራ፣ ቱምሳ በኦሮሚያና ወንዶ በደቡብ ክልላዊ መንግስቶች ውስጥ የባንክና ኢንሹራንስ ኩባንያዎች መሠረቱ ቅርንጮፎቻቸውም እነደአሸን ፈሉ፡፡ የክልላዊ ፖለቲካ ፓርቲዎች በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች ውስጥ እየተሰማሩና በልዩ ልዩ የንግድ ድርጅቶች ስም እየተንሰራፋ መጡ፡፡ የግሉ ዘርፍ ኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ኃይል ተመታ፡፡

{2}ጥረት በአማራ (The Amhara National Regional Rehabilitation and Development Fund, Endeavour or Tiret)

ጥረት በአማራ፤የአማራ ብሔራዊ ክላልዊ መልሶ ማቋቋምና ልማት ማህበር ወይም ጥረት በመባል ይታወቃል፡፡ ጥረት በ1995 እኤአ ሲቆቆም አስቀድመው የተመሠረቱትን የንግድ ድርጅቶችና ካንፓኒዎች በማካተት፣ለምሳሌ አንባሰል ትሬዲንግ በ1993 እኤአ፣ብሉ ናይል ትራንስፖርት በ1992 እኤአ፣ዳሽን የቢራ ፋብሪካ በ1995እኤአ፣ እንዲሁም በ አግሮ ፕሮሰሲንግ  ዘለቀ አግሪካልቸራል ሜካናይዤሽን በ1996እኤአ የሥጋ ውጤቶች ፋብሪካና ልዩ ልዩ ንግዶች፣ ሌሎች ካንፓኒዎች ሼባ ኢንደስትሪስ (ሠሊጥ ፕሮሰሲንግ ታሂና እና ሃልዋ) እንዲሁም የደጋ ቡና ሁለቱም በ1993እኤአ ተቆቆሙ፡፡ በ1998እኤአ የአማራው ክልልዊ መንግስት ጥረት  መቀመጫውን ፈረንሳይ ካደረገው ቢጂአይ ጋር በመሆን የዳሽን ቢራ ፍብሪካን በጎንደር መሠረቱ፡፡ የወጋጋን ባንክን ከመሠረቱት ድርጅቶች ውስጥ ኢፈርት፣ ጥረት፣ ቱምሳና ወንዶ ሼር እንዳላቸው ይታወቃል፡፡ ጥረት የዋልታ ኢንፎርሜሽን ሴንተረና የአማራ ክልል የብድርና ቁጠባ ድርጅትን መስርተዋል፡፡ በተጨማሪም ጥረት   የአማራ የልማት ማህበርና የአማራ መልሶ ማቋቋም (Amhara Development Association (ADA) ና የልማት ማሕበር (Organisation for Relief and Development in Amhara (ORDA). ምስረታ ላይ እገዛ አድርጎል፡፡ ጥረት የአማራው ክልል መንግስት፣ የንግድ ካንፓኒ በአጠቃላይ 2800 ሠራተኞች ቀጥሮ ሲያሰራ በአንፃሩ ኢፈርት የትግራይ ክልል መንግስት የንግድ ካንፕኒዎች 14000ቆሚ ሠራተኞችና 34000 ጊዜያዊ ሠራተኞች እንዳሉት ለማወቅ ተችሎል፡፡በኢትዩጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ የኢትዩጵያ የግል ባንኮች የፋይናንስ ዘርፍ በመቋጣጠር ከህወሓት/ኢህአዴግ ፓርቲዎች የሃገሪቱን ባንኮች ኃብትን ከሚቋጣጠሩት ውስጥ የአማራው ጥረት አባይ ባንክ፣ አባይ ኢንሹራንስ፣ በሚል ስያሜ የባንክና ኢንሹራንስ ድርጅቶችን ተቋጣጠረዋል፡፡ከሠንጠረጁ ላይ 2014/15 ገቢያቸውን ማስተዋል ይቻላል፡፡

{3}ቱምሳ በኦሮሚያ (Tumsa Endowment Fund in Oromia)

በኦሮሚያ ክልል ቱምሳ ኢንዶውንመንት ፈንድ በ2001እኤአ ተመሠረተ፣አስቀድመው የተቋቋሙት ዲንሾ ኢንተርፕራይዝ በ1992 እኤአ የተመሠረተ፣ ዲንሾ አግሮ-ኢንደስትሪ፣ ዲንሾ የትራንስፖርት አገልግሎት፣  ዲንሾ ትሬዲንግና፣ ዲንሾ ቢፍቱ ትሬዲንግ  ቱምሳ ኢንዶውንመንት ፈንድ ሥር ተካተቱ፡፡ ዲንሾ ትሬዲንግ በ1991እኤአ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ማዳበሪያ ለገበሬዎች በሽያጭ በማከፋፈል ይታወቃል፡፡በ1993እኤአ የተቆቆመው ዲንሾ ቢፍቱ ትሬዲንግ ሰሊጥና ቡና ወደ ውጭ ሃገር በመላክ ንግድ ላይ ቆይቶ በድሬዳዋ ከፍተኛውን የጫት ንግድ በመቆጣጠር የግሉን ዘርፍ ነጋዴዎች ሥራ ነጠቀ፡፡ በምዕራብ ሐረርጌ ዞን አምራቾች ኮኦፕሬቲቨ የጫት ላኪዎች ማሕበር ዲንሾ ትሬዲንግ ዋነኛው ሼር ሆልደር ሆኖ እስከ 2005እኤአ ዘለቀ፡፡በ1999እኤአ ዲንሾ ኢንቨስትመንቱን በማጠናከር በኦሮሚያ የቡና አምራቾች ኮኦፕሬቲቨ ዩኒየን ጋር በመስራት ቡና ወደውጭ ሃገራት፣ ታላቆ ብሪታንያና ጀርመን ይልክ ነበር፡፡ በ1999እኤአ የዲንሾ ካንፓኒዎች  ዋና ስራ አስኪያጅ ዱባለ ጃሌ እንደገለፁት የዲንሾ አመታዊ ተንቀሳቃሽ ገንዘብ 900 ሚሊዩን ብር እንደነበር ለ ፎርብስ መጋዚን ገልጸዋል፡፡ዱባለ ጃሌ የቀድሞ የኢትዩጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዥ ነበሩ፡፡ በኢትዩጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ የኢትዩጵያ የግል ባንኮች የፋይናንስ ዘርፍ በመቆጣጠር ከህወሓት/ኢህአዴግ ፓርቲዎች የሃገሪቱን ባንኮች ኃብትን ከሚቆጣጠሩት ውስጥ የኦሮሚያው ቱምሳ የኦሮሚያ ህብረት ባንክ፣ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል  ባንክ፣ በሚል ስያሜ የባንክና ኢንሹራንስ ድርጅቶችን ተቋጣጠረዋል፡፡ከሠንጠረጁ ላይ 2014/15 ገቢያቸውን ማስተዋል ይቻላል፡፡

{4}ወንዶ በደቡብ ክልሎች (Wendo Endowment Fund in SNNPRS)

ወንዶ በደቡብ ክልል፣በ1994 እኤአ በሃዋሳ ከተማ ውስጥ በ6 ሚሊዩን ብር ካፒታል ተመሠረተ፡፡ ወንዶ የንግድ ድርጅት ወደ ውጭ ሃገር ቡናና ጭት በመላክና ከውጭ ንግድ ማዳበሪያ እያመጣ በደቡብ ክልል ለገበሬዎች በማከፋፈል ንግድ የተሰማራ ኩባንያ ነው፡፡ ከኢህአዴግ መነሻ ካፒታሉን እንዳገኘ ይገለፃል፡፡ የክልል መንግስታት የጋራ የንግድ ኢንዶንመንት ካንፓኒዎች

Wendo Trading was established in Awassa in 1994, with capital of ETB6million, widely understood to have been provided by other EPRDF sources. Its trade and export activities focus on fertiliser, coffee and khat. በኢትዩጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ የኢትዩጵያ የግል ባንኮች የፋይናንስ ዘርፍ በመቋጣጠር ከህወሓት/ኢህአዴግ ፓርቲዎች የሃገሪቱን ባንኮች ኃብትን ከሚቋጣጠሩት ውስጥ  የደቡቡ ወንዶ ደቡብ ግሎባል ባንክ፣ሉሲ ኢንሹራንስ በሚል ስያሜ የባንክና ኢንሹራንስ ድርጅቶችን ተቋጣጠረዋል፡፡ ከሠንጠረጁ ላይ 2014/15 ገቢያቸውን ማስተዋል ይቻላል፡፡

የኢትዩጵያ ሕዝቦች አብዩታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) መንግሥት፣ለህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ትግራይ ክልል፣ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ለኦሕዴድ) ለኦሮሚያ ክልል፣ ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ለብአዴን) ለአማራ ክልል፣ የደቡብ ኢትዩጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ለደኢሕዴግ)  ለደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል፣ዘር አፈራሽ የባንክና ኢንሹራንስ እንደከፈተላቸው ወደፊት አጋሮቹ ለሚሆኑ ለሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ለሶዴድ) ለሶማሌ ክልል፣አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (አዴድ) የአፋር ክልል፣ ቤኒሻንጉል ሕዝቦች ነፃ አውጭ ንቅናቄ (ለቤህነን) የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ለጋምቤላ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ለጋሕነን) ለጋምቤላ ክልል፣ ለሃረሪ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ሃዴድ) ለሃረሪ ሹማምንትና ካድሬዎች የሚዘወሩ የባንክና ኢንሹራንስ ድርጅቶች ይፈበረኩ ይሆናል፡፡

‹‹በሃገሪቱ ያሉ ህዝቦች የባንኮችን አሠራርና የገንዘብ ስርዓቱን አለመረዳታቸው ደህና ነው እንጂ፣ቢያውቁ ኖሮማ ከነገ ጠዋት በፊት ህዝባዊ አብዩት እንደሚነሳ አምናለሁ!!!›› ይላሉ ሄንሪ ፎርድ፡፡ “It is well enough that people of the nation do not understand our banking and monetary system, for if they did, I believe there would be a revolution before tomorrow morning.”  ― Henry Ford የኢትዩጵያ ህዝብም በሃገሪቱ ያሉ የባንኮችና ኢንሹራንሶች አሠራርና የገንዘብ ስርዓቱን አለመረዳታቸው ወያኔ/ ኢህአዴግ በጀው እንጂ፣ ቢያውቁ ኖሮማ ከነገ ጠዋት በፊት ህዝባዊ አብዩት እንደሚነሳ ምንም ጥርጥር የለንም!!! እነዚህ የኢትዩጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የባንክና ኢንሹራንስ ንግድ ኢንተርፕራይዝ ዋና መስሪያ ቤቶችና ቅርንጫፎቻቸው በአዲስአበባ፣ አዳማ፣ መቐለ፣ ባህርዳር፣ ድሬዳዋ፣ አዋሳ፣ ጋምቤላ፣ ሰመራ፣ ኦጋዴን፣ ቤኒሻንጉል ወዘተ ከተሞችን ውስጥ ከተመሠረቱ  አመታት ሲቆጠር፣ ቁጥራቸው የትየለሌ ደርሶል፣ ህዝቡም እነዚህ ባንኮች ውስጥ ገንዘቡን ያስቀምጣል፡፡

በዓለማችን አንዲት ጎጆ መሥራት የማትችል የወፍ ዘር አለቺ ታዲያ ትውልዶን የዘር ግንድ ለመቀጠል ስትል እንቁላሎን የምትጥለው ጎጆ ከምትሠራዋ የወፍ ዝርያ ጎጆ ነው፡፡ ያችኛዋ እንደራሶ ልጆች አሳድጋ ለአቅመ ወፍነት ታበቃቸዋለች፡፡ የወፎቹ የህይወታቸው ዕደቱ እንደዛ ነው ሲያድጉ ወደ ዘር አፈራሽ ቡድናቸው ይሄዳሉ፣ዳግም እንቁላል ይጥላሉ፣እነዛኞቹ ያሳድጋሉ ወዘተ ተፈጥሮ ድንቅ ናት፡፡ የኢትዩጵያ ህዝብም ገንዘቡን ህወኃት/ኢህአዴግ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለህወኃት፣ ለብአዴን፣ ለኦህዴድና ለደኢሕዴግ ባንኮችና ኢንሹራንሶች እንደ አንቁላል ይጥላሉ!!! ህዝቡን ስለ ባንክና ኢንሹራንስ ማን ያስተምረው?  ይሄን ቢያውቅ ኖሮማ ከዛሬ በፊት አብዩት አፈንድቶ ወያኔን ባባረረ ነበር፡፡ እንኮን ህዝብ ስንቱ የተማረውስ ይሄን የባንክና ኢንሹራንስ የፋይናንስ ስርዓት ያውቅ ይሆን?  የኢትዩጵያ ባንኮችና ኢንሹራንሶች የማን ኃብት ናቸው??? ምጣኔ ኃብታችንን እስካላወቅን ድረስ ኃብታችንን እንዘረፋለን፡፡ እርሻችን ይነጠቃል፣ እርስታችን ይቀማል፣ መዐድናችን ይዛቃል፣ ከብታችን ይነዳል፣ ላሞቻችን ይታለባሉ፣ ገንዘባችን ይዘረፋል፡፡ ዛሬ የግል የቴሌቪዚን፣ የሬዲዬ ሞገድና ድረ-ገፆች  ያላቸው ያገሬ ልጆች የሃገራቸውን ምጣኔ ሃብት ለህዝብ እስካላስረዱ ድረስ ትግሉ ውኃ ቅዳ፣ ውሃ መልስ ይሆናል፡፡ ትግሉ ትልቁን ወርካ ለመቁረጥ አንዴ ብቻ በመጋዝ ወደፊት ገዝግዞ፣ ወዲያው ወደኃላ ገዝግዞ ይቆማል ውጤት አይኖረውም፡፡

የህወኃት/ኢህአዴግ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣የኦሮሞን መሬት፣ አዳማ፣ ብሸፍቱ፣ አሌልቱ፣ ሰበታ፣ ወለጋ፣ አሶሳ፣ ባኮ፣ ባሌ፣ ራይቱ፣ ቦረና፣ ኢሊባቡር ወዘተ የቡናና የአበባ እርሻ ወያኔዎች ርስተ ጉልታቸው ካረጉ አመታት ተቆጥሮል፣ የለገደንቢ፣ ሳካሮ፣ የአዶላ የወርቅ ማዕድን ኃብት ለዓመታት ይዛቃል፡፡ የአማራን መሬት፣ ራያን፣ ወልቃይት፣ ጸገዴን፣ መተከል፣ አዊ፣ ፓዊ፣ ወዘተ  ነጥቆ ሠሊጥ አምርቶ ውጪ ይልካል፣ የመተከል የወርቅ መዕድን ኃብት ያዝቃል፡፡ የጋምቤላ መሬት አቦቦ፣ ኢታንግ፣ ጂካኦ፣ ጉደሬ፣ ጎግ፣ ጆር በወያኔ ተነጥቆ ይታረሳል፡፡ በቤኒ-ሻንጉል ጉባ፣ ወዘተ መሬት ይታረሳል፡፡ የአፋር የጨውና ቀይ ፖታሽ የመሬት ኃብት ተነጥቆ በወያኔ ይዛቃል፡፡ የደቡብ ክልል መሬት ሃዋሳ፣ ሲዳማ፣ ወላይታ፣ ሆሳዕና፣ አርባምንጭ፣ ወዘተ የቡና መሬት በወያኔ ተዘርፎል፡፡ የትግራይ ወርቅ በኢፈርት፣ ኢዛና እየተዛቀ ይሸጣል፡፡ በሃረሪ ርስት የጫትና የቡና እርሻ ውጪ ተልኮ ይሸጣል፣ የንግድ ማእከሉና የኮንትሮባንዱ ሥራ ሁሉ ወያኔና የክልሉ መንግሥት የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር በመሆን እየዘረፉ ይገኛል፡፡ መሬቱን የተነጠቀው ህዝብ፣ እርስቱን የተቀማው ህብረተሰብ እንደ ኦሮማና አማራ ህዝብ እንቢተኝነቱንና ተጋድሎውን በፈለገው የትግል ስልት እየተደራጀ፣ የጎበዝ አላቃ እየመረጠና በሚስጢር እየተደራጀ፣ እየታጠቀና ትግሉን መምራት ይኖርበታል፡፡ ከዛም ህብርት እየፈጠረ ህብረ-ብሄር ኢትዩጵያዊ ብሄርተኝነትን በመገንባት ብቻ ህወኃት/ኢህአዴግን ከበትረ-ሥልጣኑ መንቀል ይችላል፡፡

‹‹የኢትዩጵያ መንግሥታዊና የግል ባንኮች የፋይናንስ ዘርፍ ቀውስ 2010/ ይከሰታል!!!›› 

የኢትዩጵያ ብሔራዊ ባንክ ኃላፊነቱን ያልተወጣ ተቆም ነው፡፡ በሃገሪቱ ለተፈጠረው የፋይናንስ ዘርፍ ቀውስ፣ የገንዘብ አቅርቦት መመጠንና መቆጣጠር አለመቻሉ፣ የገንዘብ ወጪና ብድርን መወሰንና መጠበቅ አለመቻሉ፣ የሃገሪቱን የዓለም ዓቀፍ ተቀማጭና መጠባበቂያ ገንዘብ መቋጣጠርና ማስተዳደር ደካማነቱ፣ ለባንኮች ፍቃድ መስጠት፣መቋጣጠርና ክትትል ማድረግ አቅመቢስነቱ፣ የንግድ ባንኮች ተቀማጭ መያዝ፣እንዲሁም ለንግድ ባንኮች ገንዘብ ማበደር፣ የንግድ ባንኮችን ብድር መቆጣጠርና ክትትል ማድረግ እንዲሁም የወለድ መጠንን መወሰን ጣልቃ ገብነቱ፣ እንደ መንግሥት ወኪል ሆኖ በመስራትና የውጭ ምንዛሪ ምጣኔን መወሰንና መቆጣጠር ተስኖቸዋል፡፡ የባንክ ሙያተኞች በሙስና ተዘፍቀው ከሹማምንቶቹ ጋር ተመሳጥረው የሃገር ሃብት መዝብረዋል፡፡ በሱዳን የግል ካንፓኒ፣የብር ኖቶችንና ሣንቲሞችን በማሳተም የሃገሪቱን የብር ኖቶችን እንደወረቀት በማሳተም የሃገር ሉዓላዊነትንና የህዝቡን ደህንነት ለባዕድ አገር አሳልፈው የሰጡ የብሄራዊ ባንክ ገዥዎችና የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥት ለፍርድ መቅረባቸው አይቀርም፡፡ እውቁ ኢኮኖሚስት ጆሲፍ ሲቲግሊዝ በኢኮኖሚክስ የኖቪል ሽልማት ተሸላሚ እንዳሉት ‹‹ እኛ ቀስ በቀስ እያሳደግነው የመጣንው የፍትህ ስርዓት ዕይታ፣ ፍትህ ለሁሉም ከማለት ይልቅ፣ የፍትህ ስርዓት በቂ አቅም ላላቸው ይገባል፡፡ እኛ ባንኮች አሉን በጣም ትልቅ ለመውደቅ ብቻ አይደሉም፣ ነገር ግን ትልቅ የተጠያቂነት ኃላፊነት ጭምር አለባቸው፡፡ ይላሉ፡፡ “Rather than justice for all, we are evolving into a system of justice for those who can afford it. We have banks that are not only too big to fail, but too big to be held accountable.”  ― Joseph E. Stiglitz

የኢትዬጵያ የውጪ ብድር ክምችት ከብሄራዊ አማካይ ጠቅላላ አመታዊ ምርት ድርሻ በ2011 እኤአ 19.9 በመቶ የነበረ ሲሆን በ2014 እኤአ 27 በመቶ ነበር፡፡ የመንግሥታዊ ልማት ዘርፎች ብድር  ከብሄራዊ አማካይ ጠቅላላ አመታዊ ምርት ድርሻ በ2011እኤአ 20.9 በመቶ የነበረ ሲሆን በ2014 እኤአ 42.0 በመቶ ሆኖል፡፡ በ2016/17 እኤአ የህወሓት መንግስትና ብሄራዊ ባንክ ባለሞሎች የሃገሪቱን ልትወጣ በማትችለው የውጪ ብድር ክምችት ከተው ኢኮኖሚውን አዘቅት እንደሚከቱት አጥኝዎች ተንብየዋል፡፡ ለዚህም ግልፅ ማሽረጃ የ2009 ዓ/ም ዓመት እቅድና አፈጻጸም፣ በተለይ የውጪ ንግድ ገቢ ማሽቆልቆል፣ የውጪ ብድር መክፈል አቅም መሽመመድና የውጪ ምንዛሪ እጥረት በቀጣይነት ተከስቶል፡፡ በ2008ዓ/ም የውጭ ዕዳ ክፍያ 1 ቢሊዩን ዶላር ለመክፈል ተገዶል፡፡ የወለድ ክፍያው በዓመት ከ350 ሚሊዩን ዶላር ከፍ ብሎል፡፡ በ2009ዓ/ም የውጭ ዕዳና የወለድ ክፍያ 1.5 ቢሊዩን ዶላር ለመክፈል ተገዶል፡፡

ለማጠቃለል የኢትዬጵያ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) አነስተኛ መሆን ምክንያት የሃገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት፣ በተቆለለ የውጭ ብድር ክምችትና የእዳ ክፍያ ምክንያት በረጅም ግዜያት ውስጥ እንደሚናጋ ይጠበቃል፡፡ የኢትዬጵያ የውጭ ብድር በ1975 እኤአ የኢትዬጵያ የውጭ ብድር 343.7 ሚሊዩን ዩኤስ ዶለር የነበረ ሲሆን ይህውም አመታዊ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) 14% እጅ ይይዝ ነበር፡፡ በ1991 እኤአ የኢትዬጵያ የውጭ ብድር 9.1 ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር የነበረ ሲሆን ይህውም አመታዊ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) 214% እጅ ይይዝ ነበር፡፡ በጁን 30 1999 ይሄ አሃዝ 10.2 ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር ከፍ ብሎል፡፡በ2011እኤአ የኢትዬጵያ የውጭ ብድር 7.102 ቢሊዩን ዩኤስ ዶለር የነበረ ሲሆን ይህውም አመታዊ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) 23.5% እጅ ይይዝ ነበር፡፡ 2012እኤአ የኢትዬጵያ የውጭ ብድር 12 ቢሊዩን ዩኤስ ዶለር የነበረ ሲሆን ይህውም አመታዊ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) –% እጅ ይይዝ ነበር፡፡ 2013እኤአ የኢትዬጵያ የውጭ ብድር 16.11 ቢሊዩን ዩኤስ ዶለር የነበረ ሲሆን ይህውም አመታዊ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት($46) ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር (GDP) 35% እጅ ይይዝ ነበር፡፡ 2016/17እኤአ የኢትዬጵያ የውጭ ብድር 40 ቢሊዩን ዩኤስ ዶለር ሲገመት ይህውም ከአመታዊ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት($69) ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር (GDP) 58% እጅ ይይዛል፡፡  እንደ ዶክተር ሰዒድ ኑሩ ገለፃ ‹‹የውጭ ምንዛሪ የሚገኙባቸው የታወቁ ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ከኤክስፖርት፣ከውጭ በዕርዳታና ለብድር፣ በውጭ የሚኖሩ ሰዎች የሚልኩት ነው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ በእጃችን ላይ ያለው ኤክስፖርት ነው፡፡ ኤክስፖርት ደግሞ ያለው አፈጻጸም ደካማ ነው፡፡ የውጭ ዕርዳታ እየቀነሰ ነው፡፡ ለምግብ እርዳታ እንኮ እየቀነሰ ነው፡፡ ብድር አስቸጋሪ ነው፡፡ የውጭ ብድር የሚመሠረተው በኤክስፖርት አፈፃፀም ጥንካሬ ነው፡፡ የአበዳሪዎች ዋነኛው ጥያቄ መክፈል ይችላሉ ወይ ነው፡፡ እንዲህ ከሆነ የበጀት ጉድለት ባይኖር እንኮን በጀቱ በአገር ውስጥ ቢሸፈን እንኮ፣ ይሄን 320.8 ቢሊዩን ብር እዚሁ ብንሸፍን በብር አሁን ባለንበት ሁኔታ ትራንስፎርሜሽኑ ያቀደቸውን ከማሳካት አንፃር የውጭ ምንዛሪ የግድ ነው፡፡ ስለዚህ ትርጉም ባለውና ከአጠቃላይ በጀቱ ውስጥ ጎላ ባለ ደረጃ በውጭ ምንዛሪ መገኘት አለበት፡፡››ይላሉ፡፡

የኢትዩጵያ ሕዝቦች አብዩታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) መንግሥት ሹማምንትና ካድሬዎች በመደበኛ በጀት ለደሞዝና አበል የወጣ ወጪ፣ በ2002 እኢአ 14.5 ቢሊዩን ብር የነበረ ሲሆን በ2007 እኢአ 45.05 ቢሊዩን ብር፣ በ2008ዓ/ም 50 ቢሊዩን ብር፣ በ2009ዓ/ም 82 ቢሊዩን ብር መደበኛ በጀቱ በአንድ ግዜ የ31 ቢሊዩን 712 ሚሊዩን ብር ጭማሪ ህብረተሰቡን ለከፍተኛ ግብር እንደዳረገው የምጣኔ ሃብት ጠበብት ለህዝብ አስረድተዋል፡፡

የቱሪስቶች መታቀብ ሃገር ውስጥ በሆቴልና ቱሪዝም የሚገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢ ከ3 ቢሊዩን ዶላር በላይ ገቢ በህዝባዊውእንቢተኛነትና ተጋድሎ መቀጠል የተነሳ፣ ቱሪስቶች ሰላም ከሌለ ስለማይመጡ ይነጥፋል፡፡ የብዙ አገሮች መንግስታት የአሜሪካን፣ የካናዳ፣ የእንግሊዝ እንዲሁም የአውሮፓ መንግስታት መግለጫ በማውጣት በተደጋጋሚ ዜጎቻቸውን ወደ ኢትዩጵያ እንዳይሄዱ ከአሁኑ በመምከር ላይ ይገኛሉ፡፡

-የፊዴራልና ክልላዊ መንግሥት የፖለቲካ ፓርቲዎች ከባንክና ኢንሹራንስ ንግድ ውስጥ ይዉጡ!!!

የኢፈርት፣ጥረት፣ዲንሾና ወንዶ የንግድ ድርጅቶች ይወረሱ!!!

የፖለቲካ ፓርቲዎች በንግድ ዘርፍ መሠማራት ህገውጥ ሥራ ነው!!!

2010 ዓ/ም መልካም አዲስ አመት ይሁንልን!