የቱርኩ ኤርዳጎን እና የራሺያው ፑቲን የ2.5 ቢሊዮን ዶላር መሳሪያ ግዢ ተፈራረሙ

0

አባይ ሚዲያ
በወንድወሰን ተክሉ

የቱርኩ ፕሬዚዳንት ኤርዳጎን ታይፔ ከራሺያው አቻቸው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር የ2.5 ቢሊዮን ዶላር ዘመናዊ የአየር መከላከያ ሚሳይል ሽያጭ መፈራረማቸውን የዛሬይቱ ሩሲያ ዜና [RT] ገለጸ።

ቱርክ በሰሜን አትላንቲካ ቃል ኪዳን ሀገራት ኔቶ [NATO] ውስጥ ከአሜሪካን ቀጥሎ በሁለተኛነት ደረጃ ላይ ያለች ሀገር በመሆኗ ከራሺያ ጋር እያደረገች ያለው ግንኙነት ምእራባዊያኑን እንዳሰጋ ቢነገርም አንካራ ግን የአውሮፓ ህብረት አባልነቷ ላይ ተስፋ በመቁረጥ ይበልጥ ወደ ምስራቅ ስታቀና እየታየ መሆኑን ተንታኞች ያስረዳሉ።

በሁለቱ ሀገራት መሪዎች ስምምነት መሰረት ሞስኮ በሶሪያ እንደተከለችው ዓይነት ኤስ-400 የዓየር መከላከያ ሚሳይል ለአንካራ ለመሸጥ የተስማሙ ሲሆን ይህም ቱርክን በአከባቢው መሳሪውን የተሰጠች ብቸኛ ሀገር አድርጓታል የተባለ ሲሆን ለሞስኮም በቀጠናው ያላትን ተጽእኖ ያጠናክርላታል ተብሏል።

ሞስኮ ለአንካራ ለመሸጥ የተስማማችውን የአየር መከላከያ መሳሪያ ኤስ-400 ጸረ-ሚሳይል ሲስተም በ248 ማይልስ ርቀት ውስጥ ያሉትን እስከ 80 የሚደርሱ ጸረ አይሮፕላን ሚሳይሎችን በአንድ ኢላማ ማውደም ይቻለዋል [Russia says the S-400 system has a range of 248 miles and can shot down up to 80 targets in one go] ስትል ትገልጻለች። ከሁለት ዓመት በፊት ቱርክ የራሺያን ተዋጊ ጄት በሶሪያ ግዳጅ ላይ ያለን የዓየር ግዛቷን ጥሶ ሲገባ በመምታት በአንካራ እና በሞስኮ መካከል ዲፕሎማሲያዊ ግጭት ተፈጥሮ የነበረ ሲሆን በኋላ ላይ ሁለቱም ግንኙነታቸውን እንዳሻሻሉ የሚታወቅ ሲሆን አንካራ የሞስኮን በሶሪያ መገኘት ደጋፊ ሆናም ታይታለች።