ገዢው ፓርቲ በሱማሌና በኦሮሚያ ህዝቦች መካከል የፈጠረውን ግጭት በአማራና ቅማንት ህዝቦች መካከልም እንዲፈጠር እየሰራ ነው ተባለ

አባይ ሚዲያ ዜና
በአሰግድ ታመነ

በጎንደር ከተማ ጥያቄ ባልተነሳባቸው 8 ቀበሌዎች ቅማንት በሚል መጠርያ የዘር ፍጅት ለመፍጠር አስቦ ሲንቀሳቀስ ነበር የተባለው ገዢው ፓርቲ በህዝቡ አንድነት ከሽፏል ተብሏል።

ጎንደር ላይ የተደገሰውን የመከፋፈል፣ የመበታተን፣ ህዝቡን የማጫረስ ሴራ በህዝቡ ብስለት እና ጥንቃቄ አንድነቱን መርጦ ወያኔን አንገቱን ያስደፋው ቢሆንም እንደገና ሁለቱን ህብረተሰቦች ለማጋጨትና የዘር ፍጅት እንዲፈጠር ከፍተኛ እንቅስቃሴ ላይ ነው ተብሏል።

ዛሬ መስከረም 09 / 2010 ሌሊት በጭልጋ ወረዳ ነጋዴ ባህር ከተማ ግጭት መቀስቀሱም ተነግሯል። በግጭቱም አንድ የቅማንት ተወላጅ የኮሜቴ አባል መኖሪያ ቤት ሙሉ በሙሉ መቃጠሉ የተነገረ ሲሆን እንዲሁም በገለድባ ቀበሌ 2 የቅማንት የኮሚቴው አባላት ሲገደሉ አንድ የአማራ ተወላጅ ተገድሏል ተብሏል። ገዢው ፓርቲ በኦሮሞና በሶማሌ ህዝብ ላይ እንደፈጠረው አይነት እልቂት ለማስነሳት እየተንቀሳቀሰ ነው የተባለ ሲሆን ቁጥራቸው በርካታ የሆነ ሰራዊት ወደቦታው ማንቀሳቀሱም ተነግሯል።

ይህ በህዝብ ላይ የተወጠነ የዘር ፍጅት ሁለቱም ማህበረሰቦች ተጠንቅቀውና የገዢው ፓርቲን አካሄድ ተረድተው ሊደርስ ከታሰበው አደጋ እራሳቸውን እንዲከላከሉ የተለያዩ አካላት አሳስበዋል።

dj6lyguwsaavbwm