ሊቨርፑል በሌስተርሲቲ ከዋንጫ ፉክክር ሲሰናበት መሲ ባርሴሎናን በጎል አንበሸበሸው

አባይ ሚዲያ ዜና
ዘርይሁን ሹመቴ

በካራባኦ ወይም በቀድሞው መጠሪያው ካርሊን ካፕ 3ኛ ዙር የእግር ኳስ ግጥሚያ ሊቨርፑል ድል ሳይቀናው ቀርቷል።

በሌስተር ሲቲው ኪንጅ ፓወር ስታዲየም የተደረገው ይህ የሊቨርፑልና የሌስተር ሲቲ ጨዋታ በሌስተር ሲት አሸናፊነት ተጠናቅቋል።

Leicester vs Liverpool: Carabao Cup LIVE scores, news and results

ምንም እንኳን በኳስ አያያዝ ሊቨርፑል በልጦ ቢገኝም 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፎ ከውድድሩ በ 3ኛው ዙር ለመሰናበት ግድ ሆኖበታል።

በዌምብሊ ስታዲየም በተካሄደው የቶትንሃም ስፐርስና የባርንስሌይ ጨዋታ ቶትነንሃም 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ወደ 4ኛው ዙር አልፏል።

ከፕሪሚየር ሊጉ እና ከሻፒየንስ ሊጉ እኩል ለዚህ ውድድር ክብደት መስጠት አይገባም በማለት የቶትንሃሙ አሰልጣኝ ከውድድሩ በፊት አስተያየታቸው ለሚዲያ ሰጥተዋል።

በዛሬው በተደረገ የዚሁ የካራባኦ  ጨዋታዎች ወደ 4ኛው ዙር ካለፉት ቡድኖች መካከል ክርስታል ፓላስ፣ ሚድልስብሮው፣ ኖርቪች ሲቲና ዌስትሃም ዩናይትድ ይገኙበታል።

የፕሪሜየር ሊጉ ሃያል የሆኑት ቼልሲ፣ ማንችስተር ዩናይትድና አርሴናል በዚሁ ውድድር ወደ 4ኛ ዙር ለማለፍ በነገው እለት ከተጋጣሚዎቻቸው ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

በስፔን ላሊጋ መሲ ባርሴሎናን 4 ጎሎችን ከመረብ በማገናኘት ደጋፊዎቹንና ክለቡን በጎል ሲያንበሸብሸው አምሽቷል።

Messi hugs Aleix Vidal after the midfielder set up the Argentine star for his fourth goal against Eibar

በባርሴሎና በተጋጣሚው ላይ 6 ጎሎችን በማዝነብ 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ የላሊጋ መሪነቱን በ15 ነጥብ አጠናክሯል።

ቫሌንሺያ ከማላጋ ጋር ባደረገው የላሊጋ ጨዋታ ድሉን 5 ጎሎችን በማስቆጠር ለማጣጣም ችሏል።

ቫሌንሺያ ማላጋን 5 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ በ9 ነጥብ በደረጃ ሰንጠረዡ በ3ኛ ቦታው ይገኛል።

በጀርመን ቡንደስ ሊጋ ባየር ሙኒክ ሻልካ 04ን በማሸነፍ በደረጃው ሰንጠረዥ የመሪነቱን ቦታ ተቆናጥጧል።

ባየር ሙኒክ በዚሁ ግጥሚያው ምንም ጎል ሳያስተናግድ ተጋጣሚውን 3 ለ 0 ለማሸነፍ ችሏል።

በኦግስቡርግ እና አርቢ ላይፕሲግ መካከል በተደረገው ጨዋታ ኦግስቡርግ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ በቡንደስ ሊጋው 3ኛ ደረጃን በመያዝ ተቀምጧል።