እውቋ አትሌት አልማዝ አያና ለ2017 የዓመቱ ምርጥ አትሌት ሽልማት ታጨች

0

አባይ ሚዲያ
በወንድወሰን ተክሉ

ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን [IAAF] ኢትዮጵያዊቷን አትሌት አልማዝ አያናን ለዘንድሮው ዓመት 2017 የአመቱ ምርጥ አትሌት ሽልማት ማጨቱን ይፋ አደረገ።

አትሌት አልማዝ አያና በአስር ሺህ ሜትር ሩጫ በኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ፣ የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤትና የ2016 የዓመቱ በሴቶች ምርጥ አትሌት ተሸላሚ በዘንድሮ እንቅስቃሴዋ ባስመዘገበችው ውጤት ለዓመቱ ምርጥ አትሌት ሽልማት መታጨቷን ለማወቅ ተችሏል።

አትሌክቲክስ ፌዴሬሽኑ እንደገለጸው ከተመረጡት ሶስት እጩዎች ውስጥ የአመቱን ምርጥ አትሌት ለመምረጥ የፌዴሬሽኑ ካውንስል አባላት ምርጫቸውን ቀደም ብለው በኢ-ሜይል እንዲያሳውቁ እንደሚደረግ አትቶ የተቀረው ደጋፊና አድናቂ ግን እስከ ጥቅምት 16 ቀን በሚቆየው የኦንላይን [የቀጥታ] ምርጫ በማካሄድ መሆኑን ገልጾ አድናቂዎችና ደጋፊዎች በፌዴሬሽኑ የማህበራዊ ገጾች [ፌስ ቡክና ቲዊተር] አማካኝነት ድጋፋቸውን እና ምርጫውን መፈጸም ይችላሉ ሲል ገልጿል።

አትሌት አልማዝ አያና በዘንድሮው የለንደን ውድድር ላይ በ10 ሺህ እና በ5 ሺህ ሜትር ውድድር የወርቅና ብር ሜዳሊያ መሸለሟ አይዘነጋም።