ራሺያ በሰሜን ኮሪያ ጉዳይ በዝምታ አትቀመጥም ሲሉ ፑቲን አስጠነቀቁ

0

አባይ ሚዲያ
በወንድወሰን ተክሉ

ሰሜን ኮሪያን የኒውክሌር ትጥቅ ለማስፈታት [Disarm] ዓለም የተቀናጀ ዓለም አቀፍ ጥቃት መክፈት ይቻላል ነገር ግን ጥቃቱ የታለመለትን የጦር መሳሪያን ክምችት ማውደም ይቻለዋል ወይ ብለን ስንጠይቅ መልሱ አይቻልም ወይም አይታወቅም ነው ያሉት የራሺያው ፕሬዚዳንት ቮላድሚር ፑቲን አያይዘውም “ከሁሉ በላይ ሰሜን ኮሪያ ስትደበደብ ራሺያ በዝምታ ታልፋለች ማለት ስህተት ነው” ማለታቸውን የዛሬይቱ ራሺያ [RT] ድረ ገጽ ዘገበ።

ፕሬዚዳንቱ ይህን የተናገሩት እረቡእ እለት በንግግር በከፈቱት ዓለም አቀፍ የኢነርጂ ፎረም ላይ ሲሆን ሀገራቸው በሰሜን ኮሪያ ላይ ጥቃት ቢከፈት በዝምታ የማታይበትን ምክንያት ሲያስረዱ “We have a shared border and the Korean nuclear testing range lies 200km away from the Russian border,” ሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር ቦምቦች መሞከሪያ ስፍራ ከራሺያ ድንበር በ200ኪሎ ሜትር ያህል ራቅ ባለበት አካባቢን ጨምሮ ከራሺያ ጋር ይዋሰናሉ” በማለት ገልጸው ያ-ማለት ደግሞ የሰሜን ኮሪያን የኒውክሌር መሳሪያ አሜሪካና አባሪዎቻ የሃይል እርምጃ ቢወስዱ ራሺያንም የሚያጠፋ በመሆኑ መንግስታቸው በዝምታ እንደማያልፍ ያስጠነቀቁት።
ባለፈው ሳምንት በቤጂንግና ሞስኮ የኮሪያን ልሳነ ምድር ቀውስ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት ከፍተኛ እርብርብ ሲካሄድ እንደነበረ ይታወቃል። የምስጢራዊ ድርድር ተብሎ ለጋዜጠኞች ይፋ ያልተደረገና የሰሜን ኮሪያ ከፍተኛ ባለስልጣን የተገኘበት ንግግር በሞስኮ ተካሄዳል።

በቤጂንግ ደግሞ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ምኒስትር ሬክስ ቴለርሰን ከቻይናው ፕሬዚዳንትና ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በሰሜን ኮሪያ ጉዳይ የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን የሃል እርምጃ ውሳኔን ለማስቀየር የሚያስችል ሰላማዊ መንገድ ላይ ድርድር ቢካሄድም የተገኘ ውጤት ስለመኖሩ ሳይገለጽ ፕሬዚዳት ትራምፕ ለውጪ ጉዳይ ምኒስትራቸው “ለሰሜን ኮሪያ ድርድር ግዜህን አታቃጥል።ፒዮንጊያንግ ሃይል እንጂ ድርድር አይገባትም” በማለት በጥረታቸው ላይ ቀዝቃዛ ውሃ እንደቸለሱበት ይታወቃል።

ማክሰኞ ጥቅምት 3ቀን የነጮቹ ቤት ቃል አቀባይ የሆነችው ሳራ ሳራ ሳንደርስ ከፒዮንጊያንግ ጋር የድርድር ግዜ አብቅታል በማለት ለጋዜጠኞች ገልጻለች።

ቃለ አቀባያ የፕሬዚዳንቱን በድርድሩ ላይ ያላቸውን አቃም ስትገልጽ..We’ve been clear that now is not the time to talk,” አሁን የንግግር ግዜ አለመሆኑን በግልጽ አስረድተናል ካለች በሃላ በፒዮንጊያንግና በዋሽንግተን መካከል ሊኖር የሚችለው ንግግር በሰሜን ኮሪያ እስር ቤት ያሉትን የአሜሪካን ዜጎች በማስፈታት ላይ ብቻ ያተኮረ ንግግር ሊኖረን ይችላል “The only conversations that have taken place were that … would be on bringing back Americans who have been detained,” እንጂ ከዚህ አርእስት ያለፈ ንግግር በዋሽንግተን እና በኩል ከሰሜን ኮሪያ ጋር ለመደራድርም ሆነ ለመነጋገር በዚህ ሰዓት የሚቻል አይደለም Beyond that, there will be no conversations with North Korea at this time.” በማለት የዲፕሎማሲውን የሰላም ሩጫ ፍሬ አልባማነትን ከወዲሁ አስቀምጠዋል።
የራሺያው ፕሬዚዳንት ቮላድሚር ፑቲን የዋሽንግተን ከፒዮንጊያንግ ጋር ለመደራደር አለመፈለግን ከዲፕሎማሲያዊ መንገድ ይልቅ በሃይል እርምጃ ላይ የተመረኮዘ ውሳኔን ዋሽንግተን በመምረጣ ነው ብለው ያስባሉ።
ሞስኮና ቤጂንግ በጋራ [Double Freeze ]የተባለ የማስማሚያና ማደራደሪያ ረቂቅን ለፒዮንጊያንግና ለዋሽንግተን አቅርበው በሰሜን ኮሪያ በኩል ተቀባይነትን ሲያገኝ በአሜሪካ በኩል ውድቅ እንደተደረገባቸው ይታወቃል። በሞስኮና ቤጂንግ የጋራ Double Freeze ረቂቅ ማስታረቂያና እርሰ በርስ ማነጋገሪያ ሰነድ ውስጥ በሰሜን ኮሪያ በኩል የኒውክሌርና የሚሳዪል ሙከራዎቻን እንድታቆምና በአሜሪካን በኩል ደግሞ ከደቡብ ኮሪያ ጋር የምታደርገውን ተንካሽ ወታደራዊ ልምምድ እንድታቆምና ወደ መደራደሪያው ጠረጴዛ እንዲቀርቡ የሚጠይቅ ሲሆን ዋሽንግተን አሻፈረኝ በማለት ሀሳቡን ውድቅ ማድረጋ ይታወቃል።