አሜሪካ ሮናልድ ሬገንን የጦር መርከብ ወደ ኮሪያ አንቀሳቀሰች

0

አባይ ሚዲያ
በወንድወሰን ተክሉ

አሜሪካ ከደቡብ ኮሪያ ጋር ለምታደርገው የጦር ልምምድና ከሰሜን ኮሪያ ጋር ለምታደርገው ውጊያ ዝግጅት ግዝፉን ተዋጊ አይሮፕላኖችን ተሸካሚዋን ሮናልድ ሬገንን የጦር መርከብ ከቻይና ባህር ወደ ኮሪያ ባሕረ ሰላጤ መላኳን አስታወቀች።

የአሜሪካው ጦር መሪ Rear Admiral Marc Dalton, commander of the USS Ronald Reagan’s strike group, ሪል አድሚራል ማርክ ዳልቶን የሮናልድ ሬገን ጦር መርከብ ከቻይና ሲንቀሳቀሱ እንደተናገሩት “The United States has been very clear about leveraging all options in order to get North Korea to change its path,” አሜሪካ የሰሜን ኮሪያን አቋም ለማስለወጥ ማንኛውንም መንገድ [ወታዳራዊ እርምጃንም] እንደምትጠቀም በግልጽ አስቀምጣለች” ያሉ ሲሆን እርምጃው ፒዮንግያንግን ክፉኛ እንዳበሳጫት የዛሬይቱ ራሺያ [RT] ዜና ጣቢያ ዘግቧል።

የፊታችን ጥቅምት 20 በሚካሄደው በዚሁ ወታደራዊ ልምምድ ላይ ጄኔራሉ ዋና ትኩረታቸው ከሰሜን ኮሪያ የሚተኮሱትን ሚሳይሎች በመጥለፍና በማክሸፍ ላይ ያተኩራል ያሉ ሲሆን አጋሮቻችንን [ደቡብ ኮሪያና ጃፓንን ማለታቸው ነው] ከሰሜን ኮሪያ ጥቃት የተጠበቁ መሆናቸውንም ማረጋገጥና ለውጊያ ማዘጋጀት ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

ፒዮንግያንግ በአሜሪካን እና በደቡብ ኮሪያ መካከል የሚካሄደው ማንኛውም ወታደራዊ ልምምድ ዓላማው ሉዓላዊነቴ ላይ ያነጣጠረ ነው በማለት አጥብቃ ከመቃወምና ከመክሰስ ባሻገር ድርጊቱ እራሴን ለመከላከል የአጸፋ እርምጃ ስለሚያስወስደኝ ወደ ያልተጠበቀ የኒውክሌር ጦርነት ይመራናል በሚል ማስጠንቀቂያ ዋሽንግተንን ብታስጠነቅቅም ተቀባይነትን ባለማግኘቱ ድርጊቱ ከባለፈው ሐምሌ ወር ልምምድ በባሰ ሁኔታ ጨምሮ ለመካሄድ ሲዘጋጁ እየታየ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የሰሜን ኮሪያን ዋና ከተማ ፒዮንግያንግን ጎብኝተው የነበሩት የራሺያ ሕግ አውጪ አባላት ትናት ዓረብ ለራሺያ የዜና ጣቢያ ፒዮንጊግያንግ በቅርቡ አንድ ረጅም ርቀት የሚጓዝ ባልስቲክ ሚሳይል እንደምትሞክር እንደተነገራቸው የገለጹ ሲሆን ሁኔታውንም ሲያስረዱ
“They even gave us mathematical calculations that they believe prove that their missile can hit the west coast of the United States,” ምእራባማዊውን የአሜሪካን ጠረፍ ግዛት ሊመታ የሚችል ሚሳይልን ከእነ የሂሳብ ስልቱ አሳይተውናል” ሲል አንቶን ሞሮቮ የራሺያ ፓርላሜንት አባልና ዓለም አቀፍ ኮሚቴ አባል ሞስኮ ላይ ትናንት ዓርብ ተናግሯል።

በአሜሪካን እና ሰሜን ኮሪያ መካከል ሲካሄድ የነበረው የቃላት ጦርነት በተመድ በተጣለ ከበድ ያለ ማእቀብና ከዚያም በተናጥል በዋሽንግተን በኩል በተጣለ ተከታታይ ማእቀብ ታጅቦ ፍጥጫው እየተካረረ እንጂ እየላላ ሲመጣ አልታየም። ባለፈው ሳምንት በዋሽንግተን በኩል የውጭ ጉዳይ ምኒስትሩ ሬክስ ቴልርሰንና መከላከያ ምኒስትሩ ጂም ማቲስ በአንድ ወገን ሞስኮና ቤጄንግ ደግሞ በሌላ ወገን ሆነው ለፍጥጫው ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ ለመፈለግ ያደረጉት ከፍተኛ ጥረት ለፍሬ አልበቃም። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለውጭ ጉዳይ ምኒስትራቸው “ቴልርሰን ግዜህንና ጉልበትህን አትጨርስ። የፒዮንግያንጉ ሰውዬ ንግግር ሳይሆን የሚያስፈልገው ሃይል ነው” በማለት እንዳከሸፉባቸው ይታወቃል።

አሜሪካ ከአጋሯ ደቡብ ኮሪያ ጋር የፊታችን ጥቅምት 20 ቀን ለማካሄድ ያቀደችው ወታደራዊ ልምምድና [Drill] ዝግጅት ወቅት በተመሳሳይ ሁኔታ ሰሜን ኮሪያ በልዩና በደመቀ ሁኔታ የምታከብረው የገዢው ኮምኒስት ፓርቲ የተመሰረተበት ክብረ በዓል ወቅት በመሆኑ ይበልጥ እንዳሰጋ ተንታኞች ይናገራሉ።
የአሜሪካው የጦር መሪ አድሚራል ስለሰጡት የተንቀሳቀስ ወታደራዊ ትእዛዝ ሲናገሩ “As of Friday afternoon, the USS Ronald Reagan, with nearly 80 aircraft on board, was in the South China Sea on its way to the shores of US ally South Korea” ከዛሬ ዓርብ ከሰዓት ጀምሮ USS ሮናልድ ሬገን ወደ 80 የሚጠጉ አይሮፕላኖችን እንደጫነች ከደቡብ ቻይና ባህር ወደ ደቡብ ኮሪያ አጋራችን ጠረፎች እየተጋዘች ነው” ሲሉ መግለጫ ሰጥተዋል።
ባለፈው ሳምንት ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ በጋራ ባወጡት ማስጠንቀቂያ ባላንጣቸው ፒዮንግያንግ በጥቅምቱ የኮምኒስት ፓርቲው ምስርታ ክብረ በዓል ላይ ለየት ያለ እርምጃ ለመውሰድ እየተዘጋጀች መሆኑን መረጃ አግኝተናል በማለት ጩኸት ያሰሙ ሲሆን ቤጂንግና ሞስኮ በመቀባበል ውጥረቱን አታባብሱና ጉዳዩን በሰላማዊ የዲፕሎማሲ መንገድ እንድትፈቱት ሁለታችሁም [ፒዮንግያንግን እና ዋሽንግተን፣ ሶልና ቶኪዮን ማለታቸው ነው] መነጋገር ይኖርባችኋልና ለንግግር በር ክፈቱ የሚል ጥሪ እንዳስተላለፉ ይታወሳል። ሆኖም በአሜሪካን በኩል ማክሰኞ እለት “We’ve been clear that now is not the time to talk,” አሁን የንግግር ግዜ አለመሆኑን ግልጽ አድርገናል” በማለት የነጩ ቤት ቃል አቀባይ ሳራ ሳንደርስ መግለጻቸው አይዘነጋም።