የአባይ ግድብ ፕሮጀክት ለ2ኛ ዙር ከ2 ሺህ በላይ ሰራተኞችን ሊቀንስ ነው

0

አባይ ሚዲያ ዜና
አቢሰሎም ፍሰሃ

ከ85 ቢሊዮን ብር በላይ እያስፈለገ ከ9 ቢሊዮን ብር ያልበለጠ እንደተሰበሰበ የሚነገርለት የአባይ ግድብ በደረሰበት የገንዘብ እጥረት ስራ ማቆሙ የሚታወቅ ቢሆንም አሁን ደግሞ ግድቡን በተቋራጭነት በያዘው በጣሊያኑ ሳሊኒ ኮንስትራክሽን መለያ በለጠፉ ረዣዥም ተሽከርካሪዎች የተጫኑ ከጥቅም ውጭ የሆኑ አውቶቡሶችና ማሽነሪዎች ዛሬም ከአባይ ግድብ ፕሮጀክት እየወጡ ነው።

በመከላከያ ኢንጂነሪግ (ሜቴክ) ውስጥ ባለው ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ የተገጣጠሙ አውቶብሶች በብዛት ተሰባብረዉ ተጭነዉ በመውጣት ላይ ናቸው። ባለፉት 7 ቀናት ብቻ በሜቴኩ ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ የተገጣጠሙ 11 ትልልቅ የአስትራ ገልባጭ እና ከ10 የበለጡ ፒካፕ ትንንሽ ተሽከርካሪዎች ተገልብጠው አሊያም ተሰባብረው ከጥቅም ውጭ ሆነው በረዣዥም ተሳቢ ተሽከርካሪዎች ተጭነው ሲወጡ ማየታቸውን በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞች ገለጹ።

ከፕሮጀክቱ ዋና ሳይት ለ2ኛ ዙር የሚባረሩ ብዛት ያላቸው ሰራተኞች እንዳሉ እየተነገረ ነው። ኢህአዴግ፣ ሱዳንና ግብፅ ፕሮጀክቱን በተመለከተ የ3ዮሽ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወቃል። ግብፅ ይህ ስምምነት እየተጣሰ በመሆኑ ስጋቷን ገልፃለች።