ህወሃት ባለስልጣናቶቿን ከሱዳንና ከደቡብ ሱዳን ጋር ያላትን ቁርኝት እንዲያጠነክሩላት አሰማራች

0

አባይ ሚዲያ ዜና
አቢሰሎም ፍሰሃ

የውጭ ጉዳይ ምንስቴር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ከሱዳኑ አቻቸው ኢብራሂም ጋሃንዱር ጋር በመሆን ደቡብ አፍሪካ ድረስ በመሄድ የቀድሞ ምክትል ፕሬዝዳንትና የአሁኑ የደቡብ ሱዳን አማጽያን መሪ የሆኑትን ሬክ ማቻርን ማነጋገራቸው ተሰማ። የዶክተር ወርቅነህ ትልቁ እቅድ የነበረው አገራቸው ደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያን ተቃዋሚ እንዳትረዳ ማስማማት እንደነበር ታውቋል።

ህወሓት የሱዳንን የድንበር ጉዳይ በብአዴኑ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በኩል እያደላደለ ነው። በሱዳንና አማራ ድንበሮች አካባቢ በስፋት የሚንቀሳቀሱ የነፃነት ሃይሎችን ሱዳን በህወሃት የተቸራትንና በውሰት የተሰጣትን ለም መሬት በእጇ አድርጋ እንዳትጠቀም ዛሬም ከስጋት ነፃ መሆን ስላልቻለች ወደ አማራው ክልል እየገባች ቅሬታዋን እያቀረበች ነው።

በድንበር አካባቢ እንደ አዲስ የተቋቋመው ጥምር ጦር በተደጋጋሚ እየተመታና ወጣ ገባ እያለ ያሰበውን ፀረ ህወሃት እንቅስቃሴ የነፃነት ሃይሎችን መቆጣጠር ባለመቻሉ በየጊዜው በተለያዩ ከተሞች ስምምነት እየተባለ ሲፈራረሙ ማየት እየተለመደ መጥቷል። በቋራ፣ መተማና ባህር ዳር ከ5 ጊዜ በላይ በተለያዩ ሰበቦች ስምምነት ተፈራርመዋል፤ ስለቀጠናው የነፃነት ሃይሎች እንቅስቃሴ ተመካክረዋል። ነገር ግን እስካሁን መፍትሄ አለመገኘቱ ታውቋል።

የገዳሪፍ ግዛት አመራሮች በተደጋጋሚ በድንበር አካባቢ ከተሞችና ባህር ዳር ድረስ እየመጡ ሲዋዋሉ እየተመለከትን ሲሆን አንድም ጊዜ ቢሆን ያሰበውኝ አላማ አሳክቶ እንደማያውቅ ይታወቃል።