አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በአሜሪካ የተካሔደውን የቺካጎ ማራቶን አሸነፊ ሆነች

0

አባይ ሚዲያ
በወንድወሰን ተክሉ

እውቋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ጥሩነሽ ዲቢባ ዛሬ በአሜሪካን ቺካጎ የተካሄደውን የማራቶን ውድድርን በአሸናፊነት ማጠናቀቋ ታወቀ።

አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ የዓለም እና የኦሎምፒክ የረጅም ርቀት ሻምፒዮና በመሆን የምትታወቅ ሲሆን በማራቶን ውድድር ስታሸንፍ ይህ የዛሬው ድል የመጀመሪያዋ እንደሆነም ማወቅ ተችሏል።

ጥሩነሽ ዲባባ በዛሬው ማራቶን ውድድር ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው ድረስ ያለማሟረጥ በመሪነት ያከናወነችው ሲሆን በ2 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ31 ሰከንድ በመግባት ቀዳሚ ሆና ውድድሩን አጠናቃለች። ጥሩነሽን ተከተላ የገባችው የኬንያዋ ብሪግድ ኮስጌይ እና አሜሪካዊቷ ጆርዳን ሐሳይ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ሆነው አጠናቀዋል።

ከውድድሩ በኋላ ጥሩነሽ ዲባባ በሰጠችው ቃል የሺካጎ ማራቶንን ለማሸነፍ ጠንካራ ዝግጅት ማድረጓን የተናገረችው ጥሩነሽ ዲባባ “ብቻዬን እንደመራሁ ነው የጨረስኩት። ክብረ-ወሰን ለመስበር አሯሯጭ ያስፈልጋል። ትንሽም ንፋስ አለ። በማሸነፌ በጣም ደስ ብሎኛል” በማለት ጥሩ አሯሯጭ እንዳላገኘች ገልጻለች።