አፈጉባኤ አባዱላ ስራ ለመልቀቅ መጠየቃቸውን ይፋ አደረጉ

0

አባይ ሚዲያ
በወንድወሰን ተክሉ

የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ በመሆን ላለፉት ሰባት ዓመታት ያገለገሉት ብ/ጄ/ አባዱላ ገመዳ ከሃላፊነታቸው በፍቃዳቸው ለመነሳት የመልቀቂያ ደብዳቤ ለምክር ቤቱና ለፓርቲያቸው እንዳስገቡ ዛሬ ይፋ አደረጉ።`

የአፈጉባኤው የስራ መልቀቅ ዜና ከሁለተኛ አካል ከተሰማ ግዜ ጀምሮ በጉዳዩ ላይ ይፋ መግለጫ ያልሰጡት አባዱላ ገመዳ ዛሬ በመንግስታዊው ኢቢሲ በኩል በሃላፊነት መቀጠል ባለመቻላቸው ስራቸውን ለመልቀቅ መንግስትን እና ፓርቲያቸውን መጠያቀቸውን መግለጻቸው ቪ.ኦ.ኤ ገልጿል። ሆኖም ከአፈጉባኤነታቸው እንጂ ከድርጅታቸውና ከህዝብ ተወካዮች ተመራጭነታቸው እንደማይነሱ ሲገልጹ “ከሃላፊነቴ በመነሳት ላስመረጠኝ ድርጅትና የተወካዮች ምክር ቤት አባልነቴ ግን እቀጥላለሁ” ሲሉ ተናግረዋል።

ጄ/ል አባዱላ ገመዳ የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ይፋ ባደረጉበት በዛሬው መግለጫቸው ሃላፊነታቸውን ለመልቀቅ የተገደዱበትን ዋና ምክንያት ግን ወደ ፊት ለሕዝቡ ይፋ እንደሚያደርጉ በመግለጽ አልፈውታል።