የ2018 የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ግጥሚያዎች ውጤቶች / ሆላንድ ወደቀች

0

አባይ ሚዲያ ስፖርት ዜና
ዘርይሁን ሹመቴ

በ2018እኤአ በሩሲያ ለሚደረገው የአለም የእግር ኳስ ዋንጫ የማጣሪያ ውድድሮች በማክሰኞ ጥቅምት 10 ቀን 2017እኤአ በተለያዩ አገራት ተካሂደዋል።

በአውስትራሊያ ሲዲኒ በተካሄደው የአውስትራሊያና የሶሪያ እግር ኳስ ቡድን ግጥሚያ አውስትራሊያ የሶሪያን የአለም ዋንጫ ህልም አክስማለች።

በጦርነት የተመሰቃቀለችው ሶሪያ በአውስትራሊያ 3 ለ 2 በሆነ አግሪጌት ውጤት ለ 2018ቱ የአለም የእግር ኳስ ውድድር ህልሟን በጊዜው ሲቀጭ ለማየት ግድ ሆኖባታል።

ፈረንሳይ ኦሊቨር ጂሩድ ባስቆጠረው ጎል ቤላሩስን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለ 2018ቱ የአለም የእርግ ኳስ ዋንጫ ተሳታፊ መሆናን አረጋግጣለች።

ፓርቹጋል ስዊዘርላንድን 2 ለ 0 በማሸነፍ ክርስቲያኖ ሮናልዶን በማሰለፍ ወደ ሞስኮ እንደሚያቀኑ ለማረጋገጥ ችለዋል።

በተቃራኒው የሆላንድ ብሄራዊ ቡድን ከ2002እኤአ በሃላ ለመጀመሪያ ጌዜ የአለም የእግር ኳስ ዋንጫን መሳተፍ አቅቶታል። ምንም እንኳን ተጋጣሚውን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ቢያሸንፍም ለ2018ቱ የአለም የእግር ኳስ ዋንጫ ለመሳተፍ የሚያበቃ ነጥብ ሳያገኝ ቀርቷል።

ቀድሞ ለሩሲያው የአለም የእግር ኳስ ውድድር ማለፉን ያረጋገጠው የቤልጄም ቡድን በተጋጣሚው ሲፕረስ ቡድን ላይ 4 ጎሎችን በማሳረፍ 4 ለ 0 አሸንፏል።