ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከዝዋይ እስር ቤት ተለቀቀ

አባይ ሚዲያ ዜና
አቢሰሎም ፍሰሃ

እንኳን ደስ አለን የሶስት አመቱን ስቃይ እና መከራ ጨርሶ መፈታት በነበረበት ጊዜ ሳይፈታ ሲቀር የርሃብ አድማ ላይ የነበረው ጀግናው ብሩሁ ወንድማችን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ተፈታ።

አርብ ይፈታል ብለውን ሳይፈቱት ሲቀሩ አዝኜ ነበር ። እንግዲህ መድኃኔዓለም እንደፈቃድህ ይሁን ብዬም ዝም ብዬ ነበር ። ነገር ግን ይኸው ደግሞ ልንፈታው ነውና መጥታችሁ ውሰዱት አሉን ታናሽ ወንድሙ ሄዷል ፣ እኔም መፈታቱን አረጋግጫለሁ ። እናም እስኪደርስ እየጠበቅኩት ነው ።

በእሱ መታሰር ከእኔ እኩል ለተጨነቁ ሁሉ እግዚአብሔር ያክብርልኝ ብለዋል የተመስገን እናት ።