የዲቪ ሎተሪ ፎርም ከጥቅምት 18 አዲስ እንደሚጀምር ተገለጸ

አባይ ሚዲያ
በወንድወሰን ተክሉ

ከጥቅምት 3 ቀን 2017 ጀምሮ እየተካሄደ የነበረው የዘንድሮ ዲቪ 2019 ፎርም በቴክኒክ ብልሽት ምክንያት መሰረዙን እስቴት ዲፓርትመንት አስታወቀ።

መስሪያ ቤቱ እየተካሄደ ባለው የዲቪ ሎተሪ ሂደት ላይ በሰጠው መግለጫ ከጥቅምት 3ቀን ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ፎርም የሙሉ አመልካቾች በሙሉ በተፈጠረ የኮምፒውተር ችግር ምክንያት መሰረዙን ይፋ አድርጓል።

እንደ የስቴት ዲፕራትመንቱ አገላለጽ የዘንድሮው ዲቪ ሎተሪ 2019 በተፈጠረ የኮሚፒውተር ችግር ምክንያት እሰካዜሬ ድረስ ፎርሙን የሞሉ አመልካቾች በድጋሚ መሙላት ይገባቸዋል በማለት የገለጸ ሲሆን ሆኖም ግን አመልካቾች ከአንድ ግዜ በላይ ፎርሙን እንዳይሞሉ ያሳሰበ ሲሆን የመውጣት እድል ለማስፋት በሚል ከአንድ በላይ ፎርም የሚሞሉ ሰዎች ኮምፒተሩ ስለሚተፋቸው አጠቃላይ ከመሳተፍ ይባረራሉ ሲል አስጠንቅቋል።

በዚህም መሰረት ይላል የስቴት ዲፓርትመንቱ መግለጫ – የዘንድሮው ዲቪ ሎተሪ ከጥቅምት 3 ቀን እስከ ህዳር 7 ቀን 2017 የነበረው ፕሮግራም ተሰርዞ ከጥቅምት 18 ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 18 ቀን 2017 የሚካሄድ ነው ሲል ገልጾ ከዚህ በፊት የሞሉትም በድጋሚ መሙላት ይገባቸዋል ሲል አብራርቷል።

አመልካቾች ከታች በምታገኙት አድራሻ የበለጠ መረጃ ታገኛላችሁ ሲል አድራሻውንም አስቀምጧል።
usvisas.state.gov/dv/instructions.