ከፍተኛ ባለስልጣን አመለጠ በሚል ሀገሪቷ በወታደር ፍተሻ እየታመሰች መሆኗ ተሰማ

አባይ ሚዲያ
በወንድወሰን ተክሉ

በፌዴራሉ መንግስት ውስጥ ለወራት ሲካሄድ የቆየው ውስጣዊ ጦርነት ተባብሶ አዲስ አበባ ከትግራይ በመጡ አዲስ የወታደር ምሩቆች እየተጠበቀች ሲሆን በደቡብና በገሙጎፋ መስመር ሰራዊቱ መንገድ ዘግቶ እየፈተሸ እንዳለ ማምሻውን ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

ከሞያሌ እስከ ያቤሎ የመብራት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ጠፍቶ ከተሞቹ በጨለማ መዋጣቸውን እና ወታደሮችም ከፍተኛ አሰሳና ፍተሻ እያካሄዱ እንዳሉ ምንጮቻችን ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ ያለው ውጥረት በኦህዴድና በህወሃት መካከል ክፉኛ በመካረሩ ከማሰልጠኛ ተመርቀው የነበሩ የትግራይ ተወላጅ ወታደሮችን ለማምጣትና ቤተመንግስቱን እና ወሳኝ ስፍራዎችን ለማስጠበቅ ተገደዋል ይላል የምንጮቻችን መረጃ።

በህወሃት መራሹ የፌዴራል መንግስት ውስጥ ለወራት የዘለቀው ውስጣዊ ሽኩቻ በአንድ በኩል በህወሃትና በኦህዴድ መካከል በሌላ በኩል ደግሞ በእነ ጄ/ል ሳሞራ የኑስ ግሩፕና በእነ ጌታቸው አሰፋ በኩል ያለው ሃይል ጦር መማዘዝ ደረጃ እንደተዳረሱ ምንጮቻችን ጠቁመዋል።

ስርዓቱ በውስጣዊ የእርሰ በርስ ፍትጊያና ፍልሚያ የተሞላ ቢሆንም የረቡእ ቀንና ምሽት ወታዳረዊ ዘመቻ ምክንያት ግን ህወሃት መራሹ ሃይል በአባዱላ በሚመራው ኦህዴድ ላይ እየተካሄደ ያለ የማጥቃት እርምጃ ሳይሆን አይቀርም ሲሉ ይገልጻሉ።

እንደ ምንጮቻችን ዘገባ በአዲስ አበባ በደቡብና በደቡብ ምእራብ በአንድ በመሸሸ ላይ ባለ ከፍተኛ ባለስልጣን አሰሳ ላይ የተስማራ ሰራዊት ተግባር መሆኑን ገልጸው ለሰራዊቱ መዝመት ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ ያላቸውን የሁለት ባለስልጣናት ስም ጠቅሷል። እነሱም፣ አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳንና ጄ/ል ሳሞራ የኑስ መሆናቸውን አስታውቋል።

ባለፈው ሳምንት በደቡብ ምእራብ ኦሮሚያ በኢሉባቦር ቡኖ በደሌ ዞን በተካሄደ ህዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት የአከባቢው ተወላጅ በሆኑት የአማራው ተወላጆች ላይ ከፍተኛ ጥቃት የተፈጸመ ሲሆን ከአስር በላይ በግፍ ተገድለው በመቶ የሚቆጠሩት ደግሞ ከትውልድ ቀዬአቸው ለመፈናቀል መገደዳቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

አደጋውን ኦህዴድ መራሹ የኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳድር በጽኑ አውግዞ ተጠያቂዎቹንም ለፍርድ እንደሚያቀርብ የገለጸ ቢሆንም በህወሃት በኩል ደግሞ መጀመሪያ በድርጅቱ ቴሌቪዥን ጣቢያ ENN በኩል ግጭቱን በሁለቱ ነገዶች መካከል ያለው መልካም ግንኙነት እንዲበጠስ በሚያደርግ ሁኔታ ሲዘግብ ከታየ በኋላ በማግስቱም በጋዜጠኛ ሚሚ ስብሃቱ ዛሚ መገናኛ በኩል በግጭቱ የኦህዴድ እጅ እንዳለበትና የዘር ግጭት እንደሆነ በመግለጽ ከፍተኛ ውዝግብ ተፈጥሮ እንደነበረ ይታወቃል።

የኢሉባቦሩ ክስተት በኦህዴድና በህወሃት መካከል ለረዥም ግዜ እየተካሄደ ያለው የውስጥ ለውስጥ ጦርነት በይፋ አደባባይ የወጣበት ክስተት ነው የሚሉት ምንጮቻችን ዛሬ ደግሞ በወታደራዊ ዘመቻ አንደኛው ሌላኛውን ለማንበርከክ ውጊያውን እያጧጧፉ ያለበት ደረጃና ዋና ከተማዋንም ከትግራይ በመጡ ልዩ ሃይሎች ስር ለማዋል የተቻለበት ሁኔታ ላይ ተደርሷል ሲሉ ይናገራሉ።