ጆዚ ሞርኒዮ በወሰዱት ውሳኔ ከትችት አመለጡ / የዛሬን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ውጤቶችን ይዘናል

አባይ ሚዲያ ስፖርት ዜና
ዘርይሁን ሹመቴ

በእንግሊዝ የፕሪሚየር ሊጉ መሪ ማንችስተር ሲቲ ዌስት ብሮምን 3 ለ 2 በማሸነፍ ግስጋሴውን በጠንካራ መንፈስ ቀጥሎበታል።

የሲቲ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በተጫዋቾቻቸውና በውጤቱ በጣም ደስተኛ እንደሆኑ በመግለጽ ተጋጣሚያቸው የነበረውን ዌስት ብሮምንም አድንቀዋል።

በሁለተኛ ደረጃ የሚገኘው ማንችስተር ዩናይትድ በሶስተኛ ደረጃ የሚገኘውን ቶትንሃምን 1 ለ 0 በማሸነፍ ከመሪው በ 5 ነጥብ እየተከተለ ይገኛል።

ብቸኛውንና የማሸነፊያ ጎሉን ለማንችስተር ዩናይትድ ያስቆጠረውን አንቶኒዮ ማርሻልን ጨዋታው ሊጠናቀቅ 20 ደቂቃዎች ሲቀሩት ተቀይሮ ወደ ሜዳ እንዲገባ አሰልጣኝ ጆሲ ሞሪኒዮ መወሰናቸው በደጋፊዎች ቅሬታን ቢያስነሳም በ81ኛው ደቂቃ ኳስን ከመረብ በማገናኘት የደጋፊዎችን ቅሬታ ወደ ደስታ እንዲቀየር አድርጎታል።

አሰልጣኝ ጆሲ ሞሪኒዮም በውሳኔያቸው ቅሬታቸውን በይፋ ሲያሰሙ ከነበሩ ደጋፊዎች ይሰነዘርባቸው ከነበረው ከፍተኛ ትችት ድነዋል።

ሃሪ ኬንን በጉዳት ያጡት የቶትንሃሙ አሰልጣኝ በማንችስተር ዩናይትድ በደረሰባቸው ሽንፈት እጅግ ማዘናቸውን  ከጨዋታው በሃላ ለሚዲያ ተናግረዋል።

ቼልሲ ቦርንማውዝን 1 ለ 0 በማሸነፍ በፕሪሚየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በ19 ነጥብ በ4ኛ ላይ ይገኛል።

አርሴናል እና ስዋንስ ሲቲ ያደረጉት ጨዋታ በመድፈኞቹ 1 ለ 0 በሆነ ድል ሲጠናቀቅ የአርሴናሉ ራምዜ 50ኛ ጎሉን ለክለቡ ማስቆጠር ችሏል።

አሰልጣኝ አርሴን ቬንገር ተጫዎቾቹ ተስፋ ሳይቆርጡ ከሃላ በመነሳት ሁለት ጎሎችን በማስቆጠር ለድል በመብቃታቸው የተሰማቸውን ኩራት ገልጸዋል።

የጀርገን ክሎፕ ሊቨርፑል ተጋጣሚውን ሃደርስ ፊልድ ላይ ሶስት ጎሎች በማስቆጠር 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ያለፈው ሳምንት በቶትንሃም 4 ለ 1 መሸነፋቸውን ወደ ሃላ ትተው የዛሬውን ጨዋታ በድል ለማጠናቀቅ ተጫዎቾቹ ባሳዩት ጥሩ ብቃት በጣም ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።