በመቀሌ የተሰበሰበው የህወሃት አመራር በኦህዴድ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ አለ

አባይ ሚዲያ
በወንድወሰን ተክሉ

የህወሃት ከፍተኛ አመራር ድርጅታዊ ስብሰባውን ማካሄድ በጀመረ በ5ኛው ቀን በገዢው ፓርቲ ላይ ያንዣበበውን አደጋ ለመከላከል እርምጃ እንደሚወስድ ፍንጭ መስጠቱ ተሰማ።

በመቀሌ የተሰበሰቡት የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በአጣዳፊነታቸው ቅድሚያ ሰጥቶ እየተወያየበት ካሉው አጀንዳዎች ውስጥ በኦሮሚያና አማራ ክልል መካከል እየተካሄደ ባለው ግንኙነትና በተለይም በኦህዴድ ውስጥ እየተፈጠረ ስላለው ሃይል ዙሪያ በጥልቀት የተመከረበትና ውሳኔ የተላለፈበት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

እንደምንጮቻችን መረጃ በመቀሌው ስብሰባ የአል-አሙዲን አጀንዳ በድንገተኛነት እንዲያዝ ከመደረጉ በቀር ትልቁን ቦታና ግዜ የወሰደው አጀንዳ ግን የራሱ የህወሃትን ውስጣዊ ህጸጽ በመፍታት ላይ ያተኮረ እንደሆነ ያስረዳል።

የኢህአዴግ አባል ሆኖ ግን በውጭ ባሉ ከአርበኞች ግንቦት 7፣ ከኦነግ እንዲሁም ከሌሎች ጋር ሆኖ ውስጥ ለውስጥ በመስራት የፌዴራሉን ስርዓት ለአደጋ ባጋለጡ ውስጣዊ ሃይሎች ላይ እርምጃ እንወስዳለን ያለው የመቀሌው ተሰብሳቢ እርምጃ የሚወሰድበትን ድርጅት ባይገልጽም ታዛቢዎች ግን ኦህዴድን የሚመለከት ነው ይላሉ።

የመቀሌውን ተሰብሳቢ ዛቻ በሚያጠናክር መልኩ ጠ/ሚ ደሳለኝ ሃይለማርያምም ለሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በሀገሪቱ ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ውሳኔ መሰረት መንግስት የፖለቲካ ቀውስ በፈጠሩ ሃይሎችና አመራሮች ላይ የህግ እርምጃ ይወስዳል ብለዋል።