ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ከስልጣናቸው እንዲነሱ ተደረገ

0

አባይ ሚዲያ ዜና
አቢሰሎም ፍሰሃ

የዚምባብዌ ገዢው ፓርቲ ዛኑ፡ፒኤፍ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤን ከስልጣን አንስቶ በምትካቸው ከሁለት ሳምንት በፊት ሙጋቤ ከስልጣን ያባረሩአቸውን የቀድሞ የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩትን ኤመርሰን ማናጋትዋን ሾሟል።

የ93 አመቱ ሙጋቤ ከዚህ በፊት በጦር አዛዡ ጄ/ል ኮንስታንቲን ቹዌንጋ የተሰጣቸውን ከስልጣን የመልቀቂያ ገደብ ማሳለፋቸውን ዘግበን እንደነበር ይታወቃል።

ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ከ 1980 ጀምሮ የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት በመሆን ለ 37 ዓመታት ያህል ፕሬዝዳንት ሆነው ያገለገሉ ሲሆን ፓርቲያቸው እስከ ሰኞ 10:00 ሰዓት ድረስ በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣን መልቀቃቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ለድርጅታቸው ማቅረብ እንዳለባቸው ማሳወቁ ይታወሳል።

የተቀመጠው ቀነ ገደብ ካለፈ ግን በፕሬዚዳንት ሙጋቤ ላይ የዛኑ፡ፒኤፍ ማዕከላዊ ኮሚቴ የመፍትሄ አሰጣጥ ሂደቱን እንደሚጀምር አሳውቋል።

የፕሬዝዳንቱ ባለቤት ቀዳማዊ እመቤት ግሬስ ሙጋቤ እና ሌሎች በርካታ ከፍተኛ ባለስልጣት ከፓርቲው ሙሉ በሙሉ መወገዳቸውም ተሰምቷል። 

ለ37 አመታት በስልጣን ላይ የቆዩትን ሙጋቤን በመቃወምና የአገሪቱ የጦር ሃይል ያደረገውን ጣልቃ ገብነት በመደገፍ በቅዳሜ እለት ሰልፍ መካሄዱም የሚታወስ ነው።