በሻምፒየን ሊግ ቼልሲ ለቀጣዩ ዙር ማለፉን ሲያረጋግጥ ዩናይትድ ሽንፈትን አስተናግዷል/ የእረቡ ምሽት ሻምፒየን ሊግ ውጤቶች

አባይ ሚዲያ ዜና
ዘርይሁን ሹመቴ

ቀሪ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች በተደረጉበት በእረቡ ምሽት የእንግሊዙ ቼልሲ ተጋጣሚውን 4 ለ 0 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉን አረጋገጠ።

የሞሪኒዮ ማንችስተር ዩናይትድ በ89ኛው ደቂቃ በገባበት ጎል በባዝል ባልተጠበቀ ሁኔታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ሽንፈትን አስተናድዷል።

የፈረንሳዩ ፓሪስ ሴን ዠርማ  በተጋጣሚው ሴልቲክ ላይ 7 ጎሎችን በማዝነብ በጠቅላላው 7 ለ 1 ሲያሸንፍ በተመሳሳይ ግሩብ ያለው ባየር ሙኒክ ተጋጣሚውን 2 ለ 1 ለማሸነፍ ችሏል።

የአትሌቲኮ ማድሪድና የሮማ ጨዋታ በአትሌቲኮ ማድሪድ 2 ለ 0 በሆነ ድል ሲጠናቀቅ የባርሴሎናና የጁቬንቱስ ጨዋታ ያለምንም ጎል ተጠናቅቋል

ቤኒፊካ ሲኤስኬ ሞስኮን 2 ለ 0 ሲያሸንፍ ስፖርቲን ሊዝበን ኦሎፒያኮስን 3 ለ 1 አሸንፏል።