“የተጀመረውን የአባይ ግድብ ማንም ሊያስቆመን አይችልም” ኢትዮጰያ

0

አባይ ሚዲያ ዜና
አክሊሉ ታደሰ
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር ከግብጹ ፕ/ት በተደጋጋሚ ለሚሰማው ማስጠንቀቂያ ምላሽ በሚመስል መልኩ በአባይ ላይ የተጀመረውን ግዙፍ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ግድብ ሰራን ማንም ሊያስቆመን አይችልም በማለት ምላሽ ሰጡ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ መለስ አለም ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የግድቡን ስራ ማንም ሊያስቆም እንደማይችልና የግድቡ ስራ 60% ያህል መጠናቀቁን ገልጸው ከተፋሰሱ ሀገራት ጋር በስምምነትና በመግባባት የግድቡ ስራ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

ቀደም ሲል ከግብጹ አል ሲሲ የውሀ ጉዳይ ለግብጽ የሞት ሽረት ጉዳይ ነው የሚለውና ተመሳሳይ ነግግሮችን በተመለከተ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቃል አቀባዩ እንዲህ አይነቱ ከስምምነታችን ውጭ የሆኑ መግለጫዎችን መስጠት የተሳሳተ ነው ሲሊ መግለጫዎቹም ከሀገር ውስጥ የፖለቲካ ፍጆታ ውጭ ጠቀሜታ የላቸውም ብለዋል፡፡ ቃል አቀባዩ ጨምረውም ፍትሀዊ ያልሆኑ ስምምነቶችን የቀደሞ መንግስታት አልተቀበሉትም እኛም አንቀበልም በማለት የኢትዮጵያን አቋም አስታውቀዋል፡፡

ግብጽ የአባይ ውሀን በተመለከተ በተያዘው የሶስትዮሽ ድርድር ላይ የቀድሞው የቅኝ ግዛት ውል እንዲታይላት ያቀረበችው ሃሳብ ተቀባይነት ማጣቱና ሱዳን ግድቡ በተፋሰሱ ሀገራት ላይ ችግር አያመጣም በማለትዋ ለኢትዮጰያ ታደላለች በማለት መንቀፍዋ ይታወሳል፡፡

ቃል አቀባዩ ጨምረውም ክኳታር ከሚገኝ ገንዘብ ግድቡን ለማጠናቀቅ ታስቧል የተባለውን አስመልክተው ይህ ሃሳብ ኢትዮጰያ እንደዚህ አይነት ግዙፍ ግድብ የመገንባት አቅም የላትም ከሚል የተሳሳተ ግምት የሚቀርብ ነው ሲሉም ተደምጠዋል፡፡