አቶ በቀለ ገርባ ከችሎቱ ምንም አይነት ፍትሀዊ ውሳኔ አልጠብቅም አሉ

0

አባይ ሚዲያ ዜና
አክሊሉ ታደሰ

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የተወሰነላቸውን የዋስትን መብት ላገደባቸው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት መልስ የሰጡት አቶ በቀለ ገርባ ከሰበር ሰሚው ችሎት ምንም አይነት ፍትሀዊ ውሳኔ አልጠብቅም  ሲሉ የዋስትና መብታቸውን ላገደው ሰበር ሰሚ ችሎት መልስ ሰጡ፡፡

አቶ በቀለ ገርባ በይግባኝ ሰሚ ችሎት የተወሰነላቸውን የ30ሺህ ብር ውስትና ላገደባቸው የሰበር ሰሚ ችሎት በጽሁፍ የሰጡትና በጠበቆቻቸው አማካኝነት ለሬጅስትራሩ ባስገቡት ምላሻቸው ከዚህ ቀደምም በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተወሰነላቸው የዋስትና መብት ከህግ አግባብ ውጭ ሲጓተት መቆየቱና በመጨረሻም ከትክክለኛው ፍትህ የራቀ ውሳኔ የተወሰነባቸው መሆኑን ጠቅሰው ከሰበር ሰሚው ችሎት ምንም አይነት ፍትሃዊ ውሳኔ እንደማይጠብቁ ነገር ግን ይህን መልስ የምሰጠው ወደፊት በከፍተኛ ደረጃ ለሚገኙ የህግ ተማሪዎችና ተመራማሪዎች ማገናዘቢያ ይጠቅማል ከሚል መሆኑን አስፍረዋል፡፡

አቶ በቀለ ገርባ በበታች ፍ/ቤት (ፌ/ከ/ፍ/ቤት) ቅር ተሰኝተው ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በጠበቆቻቸው አማካኝንት አቤቱታቸውን አቅርበው የተወሰነላቸው የ30ሺህ ብር ዋስትና ተፈጻሚ ሳይሆን ቆይቶ በመጨረሻ አቃቤ ህጉ በሰበር ችሎት ውሳኔው እንዲታገድ በማድረጉ በእስር እንዲቆዩ መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡

ለሰበር ሰሚው ችሎት በጠበቆቻቸው አማካኘነት በጽሁፍ የሰጡትን ምላሽ ጠበቆቻቸው ለሬጅስትራር ባቀረቡበት ወቅት ቢሮው የአቃቤ ህጉን መልስ ለመስማት ለታህሳስ 2 2010 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ታውቋል፡፡