አባይ ሚዲያ ስፖርት ዜና
ዘርይሁን ሹመቴ

ጀርመን በአንደኝነት በተቀመጠችበት የፊፋ የአገራት እግር ኳስ ደረጃ ላይ ኢትዮጵያ በአለም 145ኛ ላይ ሰፍራለች።

በጥር ወር 2018እኤአ በሚደረገው የአፍሪቃ ዋንጫ ሩዎንዳንና ጊንን ማሸነፍ ተስኗት ከውድድሩ የወጣችው ኢትዮጵያ በዚሁ የፊፋ ደረጃ በአፍሪቃ 44ኛ ላይ ተቀምጣለች።

ሴኔጋል ፣ ቱኒዚያ እና ግብፅ በአፍሪቃ ከሚገኙት 54 አገራት በዚሁ የፊፋ ምርጫ ከ 1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃን በቅድመ ተከተል ይዘው ተቀምጠዋል።

ከአፍሪቃ ዋንጫ ውድድር ውጪ የሆነው ብሄራዊ ቡድኑ ኬኒያ በምታዘጋጀው የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ እግር ኳስ  (ሴካፋ) ውድድር እንደሚካፈል ታውቋል።

ከሳምንት በሃላ ለሚጀመረው ለዚህ ውድድር የብሄራዊ ቡድኑ አስልጣኙ ተጫዎቾችን መምረጣቸውና ከያሉበት ክለብ ለልምምድ መጥራታቸውም ይታወሳል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት የሚደረገውን የምርጫ ሂደት ፊፋ በይፋ መኮኖኑም የሚታወስ ነው።