የኢትዮጲያ ወቅታዊ ሁኔታ (ፍጵም ጉርፋ ስዩም)

በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን ኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣው የእርስ በእርስ ግጭት አድማሱን አስፍቶ መቀጠሉ ይታወቃል። ለዚህም በኦሮሚያና በሶማሌ ክልል ውስጥ የተቀሰቀሰው ጎሳን ወይም ብሄርን ያማከለ ግጭት አንዱ ነው።

በመቶዎች ለሚቆጠሩ ንጹሀን ዜጎች ሞትና በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች መፈናቀል ምክንያት ሆኗል ። ለግጭቶቹ መነሻም መንግስት የሚከተለው የዘረኝነት ስርአት በመሆኑ ዜጎች በሀገሪቱ ውስጥ በመረጡበት ቦታና የስራ መስክ እንዳኖሩና እንዳይሰማሩ የራሱ የሆነ አሉታዊ ጎን እንዳለው ምሁራን የራሳቸውን ስጋት የገለጹበት ጉዳይ ነው።

ነገር ግን ስልጣኑን ማስጠበቅ ብቻ ስራውን ያደረገው ስርአት በተለያዮ አካባቢዎች የሚነሱ መሰል ግጭቶችን አስቀድሞ ጥንቃቄ ባለማድረግና ችላ በማለት የብዙሀን ህይወትና ንብረት ጠፍቷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ሶማሊያ ውስጥ ሃርጌሣ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ላይ ጥቃት እየተፈፀመ መሆኑን እዚው ነዋሪ የሆኑ ስደተኞች ለቪኦኤ ገልፀዋል።

ጉዳዩ በጣም አሳሳቢ ነው እልባት ካልተገኝለት ወደ አጉራባች ሀገሮችና ምስራቅ አፍሪቃ ሊስፋፋ እንደሚችል ቢገለፅም። ጉዳዩን ግን መንግስት ምንም አይነት ትኩረት አልሰጠውም ይባስ ብሎም በሱማሌ ክልል የተፈጸመው ግድያም ሆነ መፈናቀል በሱማሌ ልዩ ሀይልና በእራሱ በፌደራል መንግስት እጁ ያለበት ጉዳይ መሆኑን ተፈናቃዮች ለተለያዩ ሚድያዎች ገልፀዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here