የሺሻ ማጨስ እገዳ ተቀባይነት እያገኘ ነው

አባይ ሚዲያ ዜና
ዘርይሁን ሹመቴ

የአለም የጤና ድርጅት  ሺሻ አደገኛ፣ ጎጂ እንዲሁም ሱስ አስያዥ እንደሆነ በጥናት አረጋግጫለሁ በማለት ሪፖርት አቅርቧል።

የአለም የጤና ድርጅቱን ሪፖርት በመመርኮዝ የተለያዩ አገራት ሺሻ ማጨስን እያገዱና እየከለከሉ ናቸው። ከነዚህም ውስጥ ሳውዲ አረቢያ፣ ፓኪስታን፣ ዮርዳኖስ እንዲሁም ሲንጋፖር ይገኙበታል።

ከአፍሪቃ ታንዛኒያ በቀዳሚነት በአገሯ ሺሻ ማጨስን በይፋ በመከልከል ሺሻ ማስመጣትም ሆነ ማከፋፈል ላይ እገዳ ማውጣቷ ይታወሳል። የታንዛኒያን እርምጃ በመከተል የሩዋንዳ መንግስትም በአገሪቷ ሺሻ ማጨስን በመከልከል በአፍሪቃ ሁለተኛ አገር መሆን ችላለች።

የሩዋንዳ መንግስት ሺሻን ማገዱ ለህዝቡ ጤና በማሰብ ሳይሆን የሲጋራ ሽያጭ ከፍ እንዲል ነው በማለት እገዳውን የሚተቹ አልታጡም።

በአፍሪቃ በአብዛኛው ወጣቱ ትውልድ የሺሻ ተጠቃሚ እንደሆነ የተለያዩ መረጃዎች ያመለክታሉ።