የነፃነት ኃይሎች 6 የአገዛዙን ፌደራል ፖሊሶችን መግደላቸው ታወቀ

አባይ ሚዲያ ዜና
ናትናኤል ኃይለማርያም

ከጎንደር አዲስ አበባ መንገድ ተብሎ በሚጠራው እና ልዩ ስሙ አይራ በሚባለው ስፍራ የነፃነት ኃይሎች ታሕሳስ 6, 2010 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡50 ሲሆን  በወሰዱት የማያዳግም እርምጃ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን በሚያሰቃዩ ስደስት የአገዛዙ የፌደራል የፖሊሶች ላይ እርምጃ መውሰዳቸውን ለማወቅ ተችሏል።

በወልድያ የተጀመረውን ሕዝባዊ ቁጣ አስመልክቶ በመላው የአገሪቷ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሚካሄደው የተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ ወደ ማራኪ ዩኒቨርስቲም ደርሶ ተማሪዎቹ አገዛዙን በማውገዝ ሰልፍ መውጣታቸው ተዘግቧል። የአገዛዙ የፌደራል ፖሊሶች በተማሪዎች ላይ የሚያደርጉትን ድብደባ ለመበቀል የነፃነት ኃይሎች እርምጃ እንዲወስዱ እንዳደረጋቸው ለማወቅ ተችሏል።

ተማሪዎቹ በትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ሆነው ስርዓቱን በመቃወም መፈክሮች አሰምትዋል። ወያኔ ይውደም (ዳውን ዳውን ወያኔ)፣ በዘረኛ  ስርዓት አንገዛም፣ ነፃነት እንፈልጋለን፣ ህዝብ እየተገደለ እኛ አንማርም፣ የአማራ እና የኦሮሞ ልጆችን እየለዩ መግደል ይቁም፣ ወያኔ በህዝብ ላይ የሚያደርሰውን ስቃይ እናወግዛለን፣ ወያኔ በሕዝቦች መካከል ልዩነት ማድረጉን ያቁም የሚሉና አገዛዙ በሕዝብ ላይ የሚያደርሰውን በደል ሁሉ በመዘርዘር እየተቃወሙ እንደነበር ታውቋል።

ተቃውሞውን ለማስቆም የአገዛዙ የፌደራል ፖሊሶች በተማሪዎቹ ላይ የተለመደውን ድብደባና ግድያ ለማካሔድ ወደ ዩኒቨርስቲው በመሮጥ ላይ እያሉ የነፃነት ኃይሎቹ በወሰዱት ድንገተኛ ጥቃት 6 የስርዓቱን የፖሊስ አባላት ሲገድሉ በርካታዎች ቆስለዋል። ሟቾቹን እና ቁስለኞቹን በአምቡላንስ ወደ ጎንደር ሆስፒታል እንደወሰዷቸውም ለማወቅ ተችሏል።

ከጥቃቱ በኋላ መብራት በአካባቢው እንደጠፋና የተኩስ ልውውጡ እንደቀጠለ ለማወቅ ሲቻል በኮሌጁና በልደታ በኩል ያለው መንገድ መዘጋቱን ታውቋል።