እምዬን አሟታል (በቴዲ አበጋዝ)

አንገቷን የያዘው ነቀርሳ በሽታ
ስር እየሰደደ ብሏት አልፋታ
እየጠዘጠዘ ለረጅም ዘመናት
አናቷን ከፋፍሎ ሁሌም እያደማት
ላያድን መዳኒት ሐብቷን አስጨረሳት
ስቃዩ በዛባት በመላው አካሏ
በርሀብ በበሽታ ወጣ ምስቅልቅሏ

ነጥታና ገርጥታ ከሰው ተርታ ወርዳ
ሐብቷ ተትረፍርፎ ልመና ከባዳ
በሆዷ ወስጥ ያለው ያረገዘቺው ጊንጥ
እየቦጫጨቃት ብሏት አላስቀምጥ
ሆዷን አሳብጦት ሊፈነዳ ደርሷል
የሰራ አከላቷን ቀስፎ ይዟታል
መዳኒት ፈልጉ ልጆቿ በፍጥነት
አትገኝምና አንዴ ከሸኘናት

ፈረንጅ አታማክሩ ቀዶ ይጥላታል
ጊንጡን አያወጣም ይበታትናታል
የመቶ አመት ቂሙን ያሳርፍባታል
ግና የሚሻለው እምዬ እምትድነው
በባህል ወጌሻ ስትመረመር ነው
ያገሯ ጠቢባን ወጌሾቹ በሙሉ
መዳኒት ፈልጉ በደንብ አስተውሉ
ከመሞቷ በፊት ሳይለይ ነፍሷ
ጊንጡን አውጡትና ይታይ እስትንፋሷ

ላለም ትንገር አዋጅ በልጆቿ ድና
የሆዷን ውስጥ መርዝ አስወግዱትና
ካንሰሩም ይወገድ አንገቷ ላይ ያለው
ቀና ብላ ትሒድ ወዳጅ ደስ ይበለው
ይያቸው ልጆቿን በናታቸው ኮርተው
ተባብረን ያዳናት እናት አለን ብለው
መልኳም ተመልሶ ትታይ አሸብርቃ
ለዘላለም ትኑር ልጆቿን አስቃ
ይሔ ነው ልጅ ማለት ለናቱ ላገሩ የሚሆን ጠበቃ።

አንገቷን የያዘው ነቀርሳ በሺታ
ስር እየሰደደ ብሏት አልፋታ
እየጠዘጠዘ ለረጅም ዘመናት
አናቷን ከፋፍሎ ሁሌም እያደማት
ላያድን መዳኒት ሐብቷን አስጨረሳት
ስቃዩ በዛባት በመላው አካሏ
በርሀብ በበሽታ ወጣ ምስቅልቅሏ

ነጥታና ገርጥታ ከሰው ተርታ ወርዳ
ሐብቷ ተትረፍርፎ ልመና ከባዳ
በሆዷ ወስጥ ያለው ያረገዘቺው ጊንጥ
እየቦጫጨቃት ብሏት አላስቀምጥ
ሆዷን አሳብጦት ሊፈነዳ ደርሷል
የሰራ አከላቷን ቀስፎ ይዟታል
መዳኒት ፈልጉ ልጆቿ በፍጥነት
አትገኝምና አንደ ከሸኘናት

ፈረንጅ አታማክሩ ቀዶ ይጥላታል
ጊንጡን አያወጣም ይበታትናታል
የመቶ አመት ቂሙን ያሳርፍባታል
ግና የሚሻለው እምዬ እምትድነው
በባህል ወጌሻ ስትመረመር ነው

ያገሯ ጠቢባን ወጌሾቹ በሙሉ
መዳኒት ፈልጉ በደንብ አስተውሉ
ከመሞቷ በፊት ሳይለይ ነፍሷ
ጊንጡን አውጡትና ይታይ እስትንፋሷ
ላለም ትንገር አዋጅ በልጆቿ ድና
የሆዷን ውስጥ መርዝ አስወግዱትና

ካንሰሩም ይወገድ አንገቷ ላይ ያለው
ቀና ብላ ትሒድ ወዳጅ ደስ ይበለው
ይያቸው ልጆቿን በናታቸው ኮርተው
ተባብረን ያዳናት እናት አለን ብለው
መልኳም ተመልሶ ትታይ አሸብርቃ
ለዘላለም ትኑር ልጆቿን አስቃ
ይሔ ነው ልጅ ማለት ለናቱ ላገሩ የሚሆን ጠበቃ።