አባይ  ሚዲያ ስፖርት ዜና

በአዲስ አበባ ስታዲየም የፕሪሚየር ሊጉን ጨዋታ ከወላይታ ድቻ ጋር ያደረገው የቡና ክለብ ድል ሳይቀናው ቀርቷል።

ሁለቱ ክለቦች ያደረጉት ግጥሚያ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል። በውጤቱም ኢትዮጵያ ቡና በ12 ነጥብ 8ኛ ደረጃን ሲያዝ ወላይታ ድቻ በ 9 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ፋሲል ከነማ ክለብን በአዲስ አበባ ስታዲየም የገጠመው የመከላከያ ክለብ ሽንፈትን ማስተናገድ ግድ ሆኖበታል።

እንግዳው ፋሲል ከነማ ተጋጣሚውን መከላከያ ክለብን 1 ለ 0 በሆነ ብቸኛ ጎል በማሸነፍ በ 15 ነጥብ በ 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በፋሲል ከነማ ሽንፈት የገጠመው መከላከያ ክለብ በ 11 ነጥብ  በደረጃ ሰንጠረዡ 10ኛ ላይ ተቀምጧል።

ወደ አዲስ አበባ በማቅናት ኢትዮ ኤሌትሪክን የገጠመው የአዳማ ከነማ ክለብ ድልን ለማጣጣም ችሏል።

አዳማ ከነማ ኢትዮ ኤሌትሪክን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ባሸነፈበት ጨዋታ ላይ የመሃል ዳኛው ለአዳማ ክለብ አንድ ለኢትዮ ኤሌትሪክ ደግሞ ሁለት ፍጽም ቅጣቶችን ሰጥተዋል።

አዳማ ከተማ 15 ነጥብ በመሰብሰብ በደረጃ ሰንጠረዡ 4ኛ ላይ ሲገኝኢትዮ ኤሌትሪክ በ8 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በትግራይ ስታዲየም መቀለ ከተማ ድሬደዋ ከተማን 2 ለ 0 በማሸነፍ በ 14 ነጥብ 6 ኛ ደረጃን ይዟል።

በሲዳማ ስታዲየም ሃዋሳ ከተማን የገጠመው የሲዳማ ቡና ክለብ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ደደቢት በ 22 ነጥብ በ 1ኛ ደረጃ ፕሪሚየር ሊጉን እየመራ ሲገኝ አርባ ምንጭ በ 6 ነጥብ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ባሳለፍነው ሃሙስ በአዲስ አበባ ስታዲየም ቅዱስ ጊዮርጊስ ጅማ አባጅፋርን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፉ ይታወቃል።