የድጋፍ ድምፅ

    ኢትዮጵያና ሕዝቧ በሕዋሕት ኢሰብአዊ አመራር ሥር ለ27 ዓመታት የመከራ ጊዜ አሳልፈዋል ። በኢኮኖሚ ምዝበራ ፤ በፖለቲካ ጭቆና ፤ በማህበራዊ ፍትህ ይህ ነው የማይባል በደል ደርሶባቸዋል ።

     ከሁሉም የሚከፋው ግን በብሔር ብሔረሰብ ፤ በቋንቋና ክልል ስም ተከፋፍሎ ለመግዛት በተጠቀመው ሤራ ምክንያት እጅግ በጣም ከፍተኛ የሆነ የሰው ሕየወትና ንብረት ጥፋት ማስከተሉ ነው ።

     በአብዛኛው ግጭቶች ላይ ዳግም ሆን ተብሎ በሕዋህት የተጠና ፤ የታቀደና በሚስጥራዊ አሠራር የተቀነባበረ ሴራ መሆኑ ነው ። ለዚህም ማስረጃው ከብዙ ጥቂቱን ለማስታወስ ያህል የጋምቤላ ፤ የአኝዋክ ፤ የባህር ዳር ፡ የጐንደርና የእሬቻንዘግናኝ አፈፃፀም የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው ። ከዚህ እኩይ ድርጊቱ መማር ያልቻለውወያኔ የሰው ደም አፍስሶ የማይረካ ነውና መልሶ በጨለንቆ ፤ በጋድሎ በበርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ደገመው ።

     እግዚአብሔር በቃችሁ እስኪል ድረስና የሕዝብ እንቢተኝነትና አመፅ ትግል ይህን አስከፊ ስርዓት ወደ ከርሰ መቃብር እስከሚያስገባው ድረስ በተከሰተው አሳዛኝሁኔታ ልባችን መሰበሩን ስንገልፅ ለተጐዱት ቤተሰቦች ሁሉ እግዚአብሔር መፅናናቱንእንዲሰጣቸው እየፅለይን በሌላ በኩል ለነፃነት ፤ ለእኩልነት ፤ ለፍትህና ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት መፈጠር ለሚታገሉት የሕዝብ ልጆች ደግሞ ከጐናቸው መሆናችንን እንገልፃለን ።

                                                                                                      የኔቫዳ የራዕይ ኮሚቴ