አባይ ሚዲያ ስፖርት ዜና

ደደቢት ክለብና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ክለብ ባደረጉት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ ደደቢት በሰፊ ውጤት አሸነፈ።

ደደቢት በተጋጣሚው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ክለብ ላይ 4 ጎሎችን በማስቆጠር 4 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

በዚህም  ውጤት ደደቢት የፕሪሚየረ ሊጉን ውድድር በ 25 ነጥብ በመምራት በ 1ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ወደ አዳማ ተጉዞ አዳማ ከተማን የገጠመው ኢትዮጵያ ቡና ሽንፈትን ማስተናገድ ግድ ሆኖበታል። አዳማ ከነማ ኢትዮጵያ ቡናን 2 ለ 1 በማሸነፍ በደረጃው ሰንጠረዥ በ 18 ነጥብ 2ኛ ላይ ሲገኝ ኢትዮጵያ ቡና በ12 ነጥብ 9ኛ ላይ ይገኛል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ በወልድያ ስታዲየም ከወልድያ ጋር ባደረገው ውድድር 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቶ በ17 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

መከላከያና ጅማ አባጅፋር ያደረጉት ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ሲጠናቀቅ ድሬደዋ ከተማ እና ሲዳማ ቡናም እንዲሁ 1 ለ 1 በሆነ ውጤት ተለያይተዋል።

በአዲስ አበባ የተካሄደው የመቀለ ከተማ እና የፋሲል ከነማ ክለብ ጨዋታ ያለ ምንም ጎል 0 ለ 0 በሆነ ውጤት ተጠናቅቋል። በውጤቱም ፋሲል ከነማ በ 16 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ መቀለ ከተማ በ 15 ነጥብ 6ኛ ደረጃን ይዟል።