ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ለነጻነት ለከፈለው ዋጋ የ2018 ተሸላሚ ሆነ

አባይ ሚዲያ ዜና
አክሊሉ ታደሰ

የ18 አመት እስራት ተፈርዶበት በወህኒ የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በሁለት አለም አቀፍ ድርጅቶች የ2018 ዓ.ም ተሸላሚ አድርገው መረጡት። ሽልማቱን በመጪው ሀሙስ ዘሄግ ኔዘርላንድ በሚደረርግ ስነስርአት ላይ እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን የ2018 ዓ.ም ተሸላሚ አድርገው የመረጡት ኦክስፎርድ ኖቪብና ፔን ኢንተርናሽናል የተባሉ ሁለት አለም አቀፍ ድርጅቶች ሲሆኑ ጋዜጠኛ እስክንድር ለዚህ ሽልማት የበቃው በከፍተኛ ተጽእኖና ማስፈራርያ ውስጥ ለነጻነት በከፈለው ዋጋ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

እነዚህ ሁለት ድርጅቶች በጋራ ለ2018 ዓ.ም ተሸላሚ በማድረግ የመረጧቸው ሁለት ብእረኞች ሲሆኑ ከጋዜጠኛ እስክንድር ጋር ለሽልማት የበቃችው ቬኑዙዌሊያዊቷ ጸሃፊ ሚላጎርስ ስኮሮ ሲሆኑ በመጪው ሀሙስ በሄግ ኔዘርላንድ በሚደረገው የሽልማቱ አሰጣጥ ስነ-ስርአት ላይ የከተማዋ ከንቲባ ፓሊን ክሪክ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡

18 አመት እስራት ተፈርዶበት ላለፉት ስድስት አመታት በወህኒ የቆየውና ዛሬም በወህኒ የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ከዚህ ቀደም ከፔን ዩ ኤስ ኤና ሂዩመን ራይት ወች እንዲሁም ፔን ካናዳና ከመሳሰሉት በርካታ አለም አቀፍ ተቋማት ሽልማቶች ማግኘቱ ይታወሳል፡፡