አባይ ሚዲያ ዜና
አክሊሉ ታደሰ

በወልዲያ የተፈጸመውን ኢ-ሰብአዊ ጭፍጨፋን ተከትሎ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ባወጣው መግለጫ ህወሀት ከስህተት የማይታረም ስርአቱም ጊዜው ያለፈበትና መቃብሩ የተማሰለት ስርአት መሆኑን ጠቅሶ  የህወሓት መወገድና በምትኩ የሽግግር መንግሥት መቋቋም የወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ ሆኗል። በዚህም ምክንያት ህወሓትን ከስልጣን ማስወገድና ወንጀለኖችን ለፍርድ ማቅረብ የቅርብ ጊዜ ግባችን ሆኗል  ስለሆነም እያንዳንዱ ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያዊ ከሚያምነው ወዳጁ ጋር  በመሆን ይደራጅ፤ በአርበኞች ግንቦት 7 መዋቅር ይታቀፍ ሲል ከወልዲያ ሰማዕታት ስርየት የሚኖረን የህወሓትን አገዛዝ አስወግደን በሕዝብ ተቀባይነት ያለው አስተዳደር ስናቆም ብቻ  ነው ብሏል፡፡ የመግለጫውን ሙሉ ቃል በመግለጫዎች አምዳችን ላይ ይመልከቱ