በወያኔ ካራ ምድሩ በደም ታጥቧል (በሃያሬ ተንሰሉ)

0

በወያኔ ካራ ምድሩ በደም ታጥቧል፣
ደም ካልፈሰሰማ መቼስ ረግቶ ያውቃል።

ወያኔ ተነሥቷል፣
ትላንትም ነበረ ዛሬም ይዳክራል፣
ምድሩንም በሞላ በደም አጨማልቋል፣
የኢንተርሃምዊ ግብሩን የጅምላ ጭፍጨፋ በሥፋት ይዞታል።

ንፁሃንን በሞላ ወጣት አዛውንቱን፣
እርጉዝ እመጫቱን፣
ባልወለደ አንጀቱ እንደ ጉድ ይቆላል፣
በሽፍታ ጭካኔው እንደ ጉድ ይገላል፣
ዋግምቱን ደቅኖ ደምን ይጎነጫል።
ተስፋን ለሠነቀ አዲስ ፀሐይ ወጥቶ ብርሃንን ይተፋል፣
ደውሉም ይሠማል! ሲያልቅ አያምር ሆኗል፣

ወያኔም ይሞታል!
ከቀብሩም በፊት ፍትሐት ተካሂዷል፣
በሠፈረው ቁና መሠፈር ጀምሯል፣
በተጎነጨው ደም፤ በጎረሠው ሥጋ ከፉ ፆሙን ሽሯል፣
ለሃጢያቱ ዋጋ ፍፃሜው ደረሠ ሞቱን ይገሸራል፣
‘ወያኔ ተነሥቷል፤ ወያኔም ይሞታል!’