የወልድያ ከተማ እግር ኳስ ቡድን ተበተነ

0

አባይ ሚዲያ ዜና
አቢሰሎም ፍሰሃ

የወልዲያ እግር ኳስ ክለብ ስብስብ ለጊዜው ተበትኗል ሲል የብአዴን ልሳን የሆነው የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዛሬ በገጹ አስነበበ።

የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ገረመው ካሳ እንደተናገሩት ክለቡ በ12ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሜር ሊግ ከጅማ አባጅፋር ጋር ካደረገው ጨዋታ በኋላ ወደ ወልዲያ ቢመለስም በከተማዋ በተፈጠረው አለመረጋጋት ምክንያት በቀጣይ ለሚካሄዱት ተከታታይ ጨዋታዎች በጋራ ዝግጅት ለማድረግ ስላልተቻለ እንዲፈርስ ተደርጓል።

የክለቡ የበላይ አመራሮች እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሁኔታዎችን ከግምት ያስገባ ምቹ ሁኔታዎችን እንዲፈጥሩ እና በመጭው ጥር 24 እና 27 ክለቡ ያሉበትን ጨዋታዎች እንዲያሸጋግርላቸው በደብዳቤ መጠየቃቸውን ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የወልዲያ እግር ኳስ ተጫዋቾቹ በሌላ ከተማ ሆነው ልምምዳቸውን መቀጠል እንዲችሉ ሁኔታዎችን ከማመቻቸት ይልቅ ብዙ መስዋትነት የተከፈለበትን ክለብ እንዲፈርስ ማደረጉ አነጋጋሪ ሆኗል።