በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አገር ወዳዶች በህወሃት መንግስት ላይ ዲፕሎማሲያዊ ትግላቸውን አጠናክረው እየገፉ ነው

0

አባይ ሚዲያ ዜና
ጋሻው ገብሬ

የኢትዮጵያ አድቮኬሲ ኔትዎርክ እና የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል ህገ ረቂቅ 128ን ወደ አሜሪካ ምክር ቤት ምርጫ ለማራመድ እየቀናቸው እንደሆነ የሚቀርቡ መግለጫዎች እያስረዱ ነው። በዚህ ዲፕሎማሲያዊ ርብርብ የኦሮሞ ህዝብ ተጠሪዎች፣ የሰቆቃ ተግባራት ሰለባዎች፣ ሌሎችም የሰባዊ መብት ጥሰትን የሚኮንኑ ድረጅቶች ታክለውበታል።

ህግ ረቂቅ 128 በአሜሪካ የህዝብ ምክር ቤት በኢትዮጵያ እየደረሰ ስላለው የሰባዊ መብቶች ጥሰት የህወሃት መንግስትን ተጠያቂ ለማድረግ የተረቀቀ ንድፈ ህግ ነው። የህወሃት መንግስት በህገ ረቂቅ 128 (HR128) ላይ ያለው ፍራቻ ተጠያቂነትና እርዳታ የመነፈግ ጉዳዮች ናቸው። ህገ ረቂቁ በዋናነት ያካተተቸው ጉዳዮች፤

  • የ2015 ዓ.ም ምርጫ ማጭበርበር የህወሃት መንግስት መቶ እጅ አቸነፍኩ ያለበት
  • በ2016 በኦሮሚያ እና አማራ የኢትዮጵያ ክፍሎች ህዝባዊ አመጽ ተነስቶ በነበረበት ወቅት ተፈጽሞ ለነበረው ያለፍርድ ግድያ፣ እስራትና ሰቆቃ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ዜጎች ሞት
  • የመናገር፣ መጻፍል፣ መሰብሰብና መደራጀት መብቶች መታፈን፣ በጋዜጠኖች ላይ የሰቆቃ እስራት መፈጸም
  • ጸረ ሽብረተኛ “ህግ” አወጣሁ በማለት ተቃዋሚ ሃይሎች እንዳይላወሱ ማድረግ ናቸው።

ኤች አር 128 ካጠቃለላቸው አንቀጾች የሰባዊ መብት ጥሰቶችን የፈጸሙ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት እቀባ እንዲደረግባቸው የሚጠይቅ ሲሆን ለዚህ መጪ ውሳኔ ይረዳ ዘንድ  የተባበሩት መንግስታት መልእክተኛ ቡድን በኢትዮጵያ ተገኝቶ ካለምንም ገደብ የሰባዊ መብት ጥሰቶችን እንዲመረምር ጠይቋል።

ከ1981 ጀምሮ የኢትዮጵያን የሰባዊ መብት ጥሰቶችን በአሜሪካው ምክር ቤት በማቅረብ የሚታወቁት ክሪስ ስሚዝ እና የኮሎራዶው የህዝብ ተወካይ ሚስተር ማይክ ኮፍማን ሰኞ ጃንዋሪ 29 ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። “ህገ ረቂቅ ኤች አር 128 ለምርጫ ዝግጁ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ተጨባጭ መሻሻሎችን ካላደረገ ምክር ቤቱ የሚወስንበት ይሆናል” በማለት ለምክር ቤቱ ብዙሃን መሪ ኬቪን ማካርቲ ጉዳዩን ማስታወቃቸው ኮንግረስ ማን ክሪስ ስሚዝ አስረድተዋል። ክሪስ ስሚዝ በመጭው ማርች ወርም በኢትዮጵያ ጉዳይ የምስክርነት ጉባኤ እንደሚጠሩ አስታውቀዋል።

ክሪስ ስሚዝ ሲያጠቃልሉ “አሜሪካ የጸረ ሽብርተኛ አጋራችን” በሚል መመሪያ ላይ ብቻ በማተኮር የኢትዮጵያ መንግስት የገዛ ህዝቡ ላይ ሽብር ሲነዛ አሜሪካ ችላ ብላለች።” በማለት ተናግረዋል።

በዚህ በያዝነው ሳምንት ሰኞ ጃንዋሪ 29 እና ማክሰኞ ጃንዋሪ 30 በኮሎራዶው የህዝብ ተመራጭ ሚስተር ማይክ ኮፍማን አቅራቢነት ኢትዮጵያውያን አገር ወዳዶች በብዙ የተለያዩ የህግ አማካሪ ረዳቶችና የመንግስት ባለስልጣኖች ፊት ቀርበው የህወሃት መንግስት በኢትዮጵያ ስለሚያደርገው ያልተቋረጠ የንጹሃን እስርና ግድያን አስረድተዋል።

ህወሃት ከዚህ በፊት  ስላደረገው አሳዛኝ ግድያዎችና በደሎች በተጨማሪ ሰሞኑን በወልዲያ ስለሆነው አሳዛኝ ድርጊት ተናግረዋል። ህዝበ ክርስቲያኑ በወልዲያ  ታቦት ሊያነግስ በወጣበት ወቅት ህዝብና ቤተክርስቲያንን፣ ባህልን በመርገጥ ህወሃት ያደረገውን እኩይ ተግባር ለአሜሪካ ባለስልጣናት አስረድተዋል።

ህገ ረቂቅ 128 ወደ ምርጫ ተራምዶ ህግ ሆኖ እንዳይጸድቅ ህወሃት ኤስ አር ጂ (S.G.R. LLC) ለተሰኘ ኩባንያ በወር 150 ሺህ ዶላር ወይም ባመት 1.8 ሚሊዮን ዶላር በመክፈል ያላደረገው ነገር ባይኖርም ይህን ሁሉ የማዘግያ ዘዴዎችን ተቋቁሞ በደጋሚ የቀረበ መሆኑ ተጠቅሷል።

ኢትዮጵያውያን ከዚህ ቀደም ካደረጉት አቤቱታ ካስገኘው ለየ