ፒየር-ኤምሪክ አቡሚያንግ በ56 ሚ ፓውንድ አርሰናልን መቀላቀሉ ተነገረ

አባይ ሚዲያ ስፖርት

አሰግድ ታመነ

የቦሩሲያ ዶርቱሙንድ ተጫዋች የነበረው አፍሪካዊዊዉ የጋቦን ተወላጅ አቡሚያንግ በ2013 -213 ጨዋታዎችን ተጫውቶ 141 ግቦችን ማስቆጠሩ የሚታወቅ ሲሆን በሀያ አራት ጨዋታ ሀያ አንድ ጎል ማስቆጠሩም ተዘግባል።

ይህ ተጫዋች ክለቡ ከዎልፍስበርግ ጋር በነበረው ጨዋታ በቡድኑ ስብሰባ ላይ አልተገኘም በሚል ያልተሰለፈ ሲሆን በቀጣዩም  የቡድኑ ባለስልጣኖች ተጨዋቹ በቂ ትኩረት አያደርግም በሚል ከቡድን ውስጥ አላካተቱትም ነበር ነገርግን በመጨረሻ 90 ደቂቃ የተጫወተ መሆኑና 2-2 ጨዋታው ማለቁ ተነግራል።

አቡሚያንግ በ 2013 ከደቡብ ፈረንሳይ Saint-Etienne ክለብ ወደ ቦሩሱያ ዶርቱሙንድ መቀላቀሉ ይነገረራ።

ለጋቦን 56 ጊዜ ያሸነፈ ሲሆን 23 ግቦቶችን አስቆጥራል። ለአርሰናል ደጋፊዎች የተጫዋቹ ክለቡን መቀላቀል ያስደሰተ ዜና ሆንዋል።