የጂሃዲዝም ማእከል በቻድ ዋና ከተማ እንጃሜና ውስጥ ተገነባ

0

አባይ ሚዲያ ዜና
አቢሰሎም ፍሰሃ

የቻድ ዋና ከተማ፣ እንጃሜና የጅሃዲስት ዲፕሎማሲን ለማጥናትና ለመከላከል የሚውል ማእከል ተቋቋመ ተባለ።

ገለልተኛ የሆኑ የቻድ ምሁራን ቡድን በዚህ ማዕከል/ፕሮጀክት ላይ በስፋት እየሠሩ እንደሆነ የታወቀ ሲሆን ይህ ቡድን በተለይም በወጣቶችና በህፃናት ላይ ፅንፈኝነትን ለመከላከል አስተዋፅኦ ማበርከት ዋነኛ አላማው እንደሆነ ታውቋል።

ሽብርተኝነትን በጦር መሳሪያዎች ብቻ ልናስቆመው እንደማንችል ስለታወቀ፣ የማእከሉ መቋቋም ጥሩ መነሻ ስለሆነ ሊበረታታ ይገባዋል ሲሉ የካሜሩኑ ምሁር ተናግረዋል። በካሜሩን የዓለም አቀፍ ግንኙነት ኢንስቲትዩት ምሁር እና ማህበራዊ-አንትሮፖሎጂስት አቶ አህመድ አይንግ ሌሎችም ሀገራት መሰል ተግባራትን እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።

ይህ ተቋም አላማ ያደረገው ሽብርተኝነትን መቆጣጠር፣ መከላከል እና ለጂሃዲስቶች ተሃድሶ መስጠት ከመሆኑም ባለፈ መጽሔቶችን ጨምሮ የመገናኛ መረጃዎችን እና ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የሚረዱ የጥናት እና የምርምር ላብራቶሪ ለመሆን ነው።

አቶ አህመድ ሲቀጥሉ፣ የመካከለኛው አፍሪካ ሀገሮች ካሜሩን፣ ጋቦን፣ ቻድ እና የመሳሰሉት ሀገሮች በሙሉ ማዕከሉን በማስፋፋት እውቅና ያገኘ ዓለም አቀፍ ማዕከል እንዲሆን መስራት አለባቸው ብለዋል።