በአዳማ ናዝሬት በህዝቡና በፌደራል ፖሊስ መካከል ከፍተኛ ግጭት ተቀሰቀሰ

0

አባይ ሚዲያ ዜና
አቢሰሎም ፍሰሃ

በአዳማ ናዝሬት የከተማው አፍራሽ ግብረ ሃይል በፀጥታ ሃይሎች በመታገዝ በተለምዶ ብራዘርስ ብስኩት ፋብሪካ ጀርባ አካባቢ ያሉትን ነዋሪዎች ቤት በሃይል ማፍረስ በጀመሩ ምክንያት በታጣቂዎችና ነዋሪዎች መሃከል በተነሳ ግጭት በርካታ ሰዎች ለጉዳት ተዳርገዋል።

በአዳማ ናዝሬት ከተማ ከመሬት ስርጭትና ምሪት ጋር በተያያዘ ህዝቡ ከፍተኛ ቅሬታ ሲያሰማ እንደነበር ይታወቃል። ከመኖሪያ ቤት መስሪያ እጦት ጋር ተያይዞ ዛሬ ድረስ ችግሩ ባለመቀረፉ የተነሳ ነዋሪው የራሱን አማራጭ በመውሰድ መሬት ከገበሬ በመግዛት የጨረቃ ቤት ሰርተው እየኖሩ ይገኛል።

ይሄን ተከትሎ አመፁ ተቀጣጥሎ አዳማን መሃል ለመሃል ሰንጥቆ ከሚያልፈው ዋናው አውራ ጎዳና መንገድ ላይ ዓለም ሆቴልና ሀኒ ኬክ ቤት አካባቢ ደርሶ ህዝቡና ፌደራል ፓሊስ ተጋጭተዋል። በዚህም ግጭት የተጎዱ ሰዎች እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።

በአሁን ሰዓት የአጋዚ ልዩ ሀይል እና የፌደራል ልዩ ሀይል ፓሊስ ናዝሬትን የጦር ቀጠና በማስመሰል በህዝብ ላይ የሽብር ድርጊት እየፈፀሙ እንደሚገኙ ያገኘናቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ።

የፌደራል ፖሊስ ወታደሮች በብረት ለበስ ወታደራዊ መኪና በመታገዝ በርካታ ወጣቶችን እያፈሱ ወደ አልታወቀ ሰፍራ በማጓጓዝ ላይ እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል።