የመጨረሻው የጠላት እስትንፋስ ባንሆንስ

ግርማ ቢረጋ
ምንም አይነት ጥቅም ለሕዝባቸውም ሆነ እንወክለዋለን ለሚሉት ብሔረተኝነት አበርክተው ቀርቶ ለራሳቸው ምን ላይ እንደቆሙ ቢጠየቁ መናገር የማይችሉ ጥቂት ዘረኞች አይደለም እነሱ ራሱ ሥርዓቱ አንድን ድርጅት ደጋግመው ስም በመጥራት ፍርሃታቸውን ከመግለፅ ውጪ ሥማቸውን ጠርቶ የማያውቃቸው መሆኑን እንዴት መገንዘብ እንዳቃታቸው ያስተዋለ ሁሉ ሌላውን ከመተቸት እንዲቆጠቡ ሊነግራቸው በተገባ ነበረ። አለመታደል ሆኖ አሁን አሁንማ የራሳችንን ትተን የሌላውን የምናማስል ጉደኞች ሆነን መቅረታችን ከመብዛቱ የተነሳ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሰናል።

አሁን ባለው የወቅቱ የሃገራችን ሁኔታ አኳያ ከተለያዩ ምሁራን ፣ ፖለቲከኞች ፣ የዜና አውታሮች እንዲሁም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተደጋጋሚና አፅንዖት ተሰጥቶት ሲጠቀስ ከምንሰማቸው ነገሮች በዋናነት የሚጠቀሰው ህወሓት አምባገነን ፣ ዘረኛ እና ጨፍጫፊ መሆኑን ነው ። ከዛም ባለፈ ህወሓት ማነው? ማንስ ነው ደጋፊው? የሚሉትን ጥያቄዎች ከማጤን ይልቅ የጎንዮሽ ትችቶች እና ፍትጊያው ላይ አተኩረው ከምናያቸው ውጪ ሌላ ማን ሊሆን ይችላል የኢትዮጵያና የህዝቧ ጠላት።

አዎን ህወሓት ገዳይ ነው ይሄን ማንም ሰው ሊክደው አይችልም ከጥቂት የራሳቸውን ተላላኪ እና የጥቅም ተካፋይ ቡችሎቹ በስተቀር ለዚህም ደግሞ ምክንያታዊ የሆኑ ብዙ ነገሮችን ማንሳት ይቻላል ከብዙው ጥቂቶችን ብቻ ብናይ የሃገራችን ገበሬን ከግብርና ሕይወቱ ላይ የተለያዩ እንቅፋቶች በማዘጋጀት በግብርና ሙያው መስራት የማይችልበትን ሁኔታ በመፍጠር ሳይወድ በግዱ መሬቱን እንዲሸጥ ሲያደርጉትና ከዛም ባለፈ መሬቱን እስከመቀማት ብሎም ሌላ የማጉረምረም ሁኔታ አንኳ ቢፈጠር በመግደል በማሰርና በማሰቃየት በብዙ ጥረት ያፈራቸውን ንብረትና ከብቶቹን ሸጦ ወይም ሜዳ ላይ በትኖ ለስደት እንዲዳረግ ያመቻቹታል። ከሁሉ የሚገርመው ይህ ሁሉ በደል ተፈፅሞበት አልበቃ ሲላቸው ገበሬውን ከገደሉ ወይም ካሰቃዩ በኋላ መሬቱን የሚገዙት እነሱ መሆናቸው ነው።

ወደ መጀመሪያው ሃሣብ ስንመለስ በነዚህ በሚያሰማሙን ነገሮች ላይ ብቻ በመመርኮዝ ይህን ጨፍጫፊነት ፣ አምባገነንነት ወይም ዘረኝነትን ማስወገድን በተመለከተ ወደ ጋራ መተሳሰብና መሰባሰብ ተቀይሮ አንድ የጋራ የሆነ አቋም ለመያዝ ምንድን ነው እንቅፋት የሆነን ወይም ደግሞ በጋራ መሰባሰቡና ልዩነቶችን በሌላ አጀንዳ በመያዝ ቀጣዩ የጋራ የሆነ ጠላታችን በምን መልኩ አፀፋ ከመስጠት ባለፈ እስከማስወገድና እስከመጨረሻው የተጠያቂነት ሰረገላ መድረስ እና ማሳፈሩ የጋራ ጠላታችንን በጋራ የማስወገዱ ሂደት ሊሆን ይገባዋል።

ብዙውን ጊዜ እራሱ ህወሓትም ቢሆን ደፍሮ የሚናገረው ነገር ቢኖር ኢትዮጵያዊያን ከዚህ በኋላ በጋራ የመጓዝ አቅማችን ተሟጦ ማለቁንና መቀራረቡ ቢፈጠር እንኳን ለመበታተን በጣም ቀላል እንደሚሆንለት ነበረ ። ለነገሩ ሕወሓቶችም ቢሆኑ ለ27 አየገደሉን እያዋረዱን እና አየዘረፉን የኖሩት አቅም ኖሮዋቸው ሳይሆን ከተለያዩ ብሔሮች የራሳቸው ጉዳይ አስፈፃሚ የብሄር ተወካዮች ስለነበራቸው ነው። እነዚህ የብሔር ተወካይ ተብዬዎች አሁንም ሊያውቁት የሚገባው በየሜዳው የሚፈሰው የህፃናት ወጣቶችና አረጋውያን ደም እስከመጨረሻው ያሳድዳቸዋል።

በርግጥ አሁን ላይ ሆነን ይህን ግፍ እና መከራ አካሄዱን ስናየው ሁኔታዎች ሁሉ ከነበሩበት በከፍተኛ ሁኔታ ተለዋዋጭና ያለው መንፈስ ህወሓትን ክፉኛ እንዳስጨነቀው ልብ ይሉዋል ። በየትኛውም መመዘኛ አሁን ያለውን የደከመ የወያኔ ርብርቦሽ መፈራገጥ ለመላላጥ ካልሆነ በስተቀረ ኢትዮጵያና ኢትዩጵያዊያንን እያንቋሸሹ እንዲሁም እያዋረዱ መኖር በፍፁም የማይቻል መሆኑ የተረጋገጠበት ደረጃ ላይ ተደርሷል ፣ ታዲያ ለዚህ ለተቀረው የድል ጎዳና የበኩላችንን መድረግ ባንችል እንኳን የሌላውን ትግል ለማንቋሸሽ መሞከር ወይም እራስን ፍፁም አድርጎ ለመቁጠር የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ሁሉ የማንነት መገለጫዎች ይሆናሉና ራሳችሁን ላለማስገመት ሌላው ቢቀር ዝምታን ምረጡ ”ዝም ባለ አፍ ዝንብ አይገባበትምና”።

ፌብሩዋሪ 2018
ስቶክሆልም