እነ አቶ በቀለ ገርባ በድጋሚ የ 6 ወር እስራት ተፈረደባቸው

0

አባይ ሚዲያ ዜና
አቤኔዘር አህመድ

በእስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አመራሮች ላይ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ተጨማሪ የ6 ወር የእስር ቅጣት ወሰነባቸው።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ አቶ አዲሱ ቡላላ እና አቶ ጉርሜሳ አያኖ መቅረባቸውን ለማረጋገጥ ሲጠሩ ከመቀመጫቸው ባለመነሳታቸው ችሎት በመድፈር በሚል ቅጣት ተላልፎባቸዋል። ከመቀመጫቸው ሳይነሱ እጃቸውን በማውጣት መገኘታቸውን ማረጋገጣቸው የአይን እማኞች ለዶች ቬሌ ተናግረዋል። እነ አቶ በቀለ ገርባ ከዚህ በፊት በመናገራችን የእስር ቅጣት የተላለፈብን በመሆኑ አንናገርም በማለት በጠበቃቸው በኩል አስረድተዋል።

ዳኞቹ በመነጋገር፣ የችሎቱን የስራ ሰዓት በማስተጓጎልና በመድፈር በሚል ክስ እያንዳንዱ ተከሳሽ ላይ የ6 ወር እስራት አስተላልፏል።

በተመሳሳይ ከወራት በፊት ችሎት ላይ በመዝፈን ተቋውሞ በማሰማታቸው ምክንያት የ6 ወር እስራት እንደተፈረደባቸው ይታወቃል።