ለዔሊ ድንጋይ ያለበሳት አምላክ (ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY)

0

‹‹ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ ከአፍሪካ 18ኛ፣ ከዓለም 121ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡!!!››   

‹‹ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር ዶክተር እሸቱ ጮሌ ክበብ››

‹‹ዔሊን ሊገሉሽ  መጡ?››  ይሎታል ‹‹ዔሊም እግዚሃብሄርም አለበት ወይ?››  ብላ ጠየቀች፡፡ደግም  ሌሎች ጎረቤቶቾ መጥተው ‹‹ዔሊን ሊገሉሽ  መጡ? ይሎታል›› ‹‹ዔሊም እግዚሃብሄርም አለበት ወይ!!!›› ብላ ጠየቀች ይባላል፡፡› እግዚአብሄርም ዔሊን በእምነቶና ፅናቶ ሊታደጋት ብሎ፣  ዔሊን ድንጋይ አለበሳት ብላኝ እናቴ  አወጋችኝ  ከዛም ጊዜ ጀምሮ ‹‹ዔሊን ድንጋይ ያለበሳት አምላክ›› ይባላል፡፡ ‹‹አግአዚ ሊገድልህ መጣ?››  ፈጣሪ ህዝቡን እንደ ዔሊ ድንጋይ አልብሶታል!!! የአግአዚ ጦር ጥይት ያልቃል፣ህዝብ አያልቅም፡፡ ወያኔ ቤት ጥይት፣ ህዝብ ቤት ክብሪት አይጠፋም!!! የሚባለው ለዚህ ነው፡፡ ለአግአዚ ጦር ሠራዊት ደሞዝ የሚከፍለው ህዝብ እንደሆነ አያውቁም፡፡ በኦሮሚያ የቄሮ አልገዛም እምቢተኝነት ትግል፣ የአማራ የፋኖ የተጋድሎ ትግል፣ የጋምቤላ፣ የአፋር፣ የሱማሌ፣ የደቡብ ክልል እየተቀጣጠለ የሄደው የኢትዮጵያ ህዝባዊ ትግል ጥሪ፣ በትግራይ ወጣቶችን ድጋፍና ህብረት ይጠይቃል፡፡  ‹‹አግአዚ ጦር ሠራዊት እየገደለን ነው?›› ዛሬም ከቀያችን ‹‹አግአዚ ሊገድልህ መጣ?››  ዛሬም ወንዛችንን ተሸግሮ ‹‹አግአዚ ጦር ህጻናት ገደለ?›› ሲባል የትግራይ ህዝብ ለቅሶ እንኮ አይደርሰንም፣ ይላችሆል!!! የአግአዚ ጦር በአብዛኛው የተመለመለው ከወያኔ ወጣቶች በመሆኑ፣ የመከላከያ ሰራዊቱም ጀነራል መኮንኖች ህልቆ መሣፍርቱ አውራ ተዋፆኦ የተዋቀረው በወያኔ ደደቢት ቡድን ነው፣ የትግራይን ህዝብ እንዲጠሉ ዋና ምክንያት ሆኖል፡፡  የኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ ገቢ ተሸመድምዶል፣ ወያኔ የሃገሪቱን ገፅታ በወጣቶች ርሸናና ስብዓዊ መብት ረገጣ አጨልሞታል፡፡ የእሬቻ በአል አከባበር የዜጎች ገደላ የተነሳ  የባህር ማዶ ጎብኝዎች ቁጥር ቀንሶል፡፡  የአፋር አርተሌ የቱሪስቶች ሞት ጎብኝዎች  ወደ ሃገራችን እንዳይመጡ አድርጎል!!!  የወልዲያ ቃና ዘገሊላ በዓለ ንግስ የተነሳ የውጭ ጎብኝዎች  ወደ ሃገራችን በቀጣይነት እንዳይገቡ ያደርጋል!!! ሰለም በሌለበት ሽህ ገዳይ መንግስት የውጪ ኢንቨስተሮችና ቱሪስት ምን ከዳቸው!!! ስንት የፍቅር ዓለም እያለ ለእሶ ሊቀመጡ አይመጡም!!!  

‹‹የአስራ ሦስት ወራት የፀሃይ ፀጋ!!! ወይስ ‹‹ኢትዮጵያ የሁሉ መገኛ ምድር››

“Thirteen Months of Sunshine” OR “Ethiopia Land of Origin”

የኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለዘመናት የቱሪዝም መለያ ‹‹የአስራ ሦስት ወራት ፀጋ!!!›› የባህር ማዶ ጎብኝዎች  ሃገሪቱንና ህዝቦን ያስተዋወቀ ብርሃን ፈንጣቂ፣ ራዕይ አምጣቂ፣ በዓለማችን አስራ ሦስት ወራት ያላት ብቸኛ ሃገር የሃገራችን ተምሳሌት፣ የሰንደቃችን ዓርማ፣ የህዝባችን ምልክት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቀለማት ከሰማየ ሰማያቱ በቀስተደመና መከሰት ዓይነት ያለው ተምሳሌትን ይገልፃል፡፡ ህወሓት የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓለማ፣ ብሄራዊ መዝሙር፣ የአስራ ሦስት ወራት ፀጋ፣ ታሪክ በማጠልሸጥ የራሱን ታሪክ ለመሥራት ይሮሮጣል፡፡ ‹‹ላንድ ኦፍ ኦሪጅንስ›› የኢትዩጵያን ተፈጥሮ፣ ባህልና ታሪክ ሶስቱን በአንድ ለመግለፅ  የሉሲ፣የቡናና የራሳF ፊደል እንዲሁም ብዙ ለየት ያለ ነገር ያላት መሆናFን ያሳያል፡፡መለያው ገላጭ ነው፡፡ ይሉናል፡፡ ‹‹ኢትዩጵያ የሁሉ መገኛ ምድር›› ወይስ ‹‹አፍሪካ የሁሉ መገኛ ምድር›› በሳይንሱ የስነ ቅድመ የስው ልጅ ተመራማሪ (አርኪዮሎጅ) ጥናት መሠረት የሉሲ ወይም ድንቅነሽ አፅም ከ3 ሚሊዩን ዓመታት በላይ እድሜ በማስቆጠሩ፣ ‹‹ኢትዩጵያ የሁሉ መገኛ ምድር›› ሲያሰኛት ቢቆይም ሌሎች ቅሬተአካላት ከሉሲም በፊት የነበሩ አዳዲስ ሳይንሳዊ ግኝቶች በደቡብ አፍሪካ በመገኘቱ የተነሳ  ‹‹አፍሪካ የሁሉ መገኛ ምድር›› አስብሎታል፡፡ ስለዚህ ይሄ ተምሳሌት ለመላ አፍሪካ አገራቶች የተሰጠ እንጅ የኢትጵያ ብቻ ሊሆን አይችልም፡፡ ህወሓት በኢትዩጵያ ታሪካዊ ስሞችን በመቀየር ጥንታዊ ተምሳሌቶችን በማጥፋትና ቀስ በቀስ በመሸርሸር በአዲሱ ትውልድ ላይ የስነልቦና ጦርነት ከከፈተ ቆይቶል፡፡ የብዙ መንግስታዊ መስሪያ ቤቶች፣ ሚንስትር ቢሮዎች ስም ለምሳሌ የቴሌኮሙኒኬሽን፣ መብራት ኃይል፣ ወዘተ ሥም ተቀይሮል፡፡ የኢትዩጵያ ፖሊስ ሠራዊት የማዕረግ ሥም ተቀይሮል፡፡ሜቴክ የመከላከያ ሠራዊቱን ልዮ ልዮ ፋብሪካዎች ሥም ለውጦል፡፡ በአጠቃላይ የጥንት የጠዋቱ ሥሞች ሁሉ  በወያኔ ተሸረዋል፡፡   

‹‹ከቱሪዝም የሚገኘው ገቢ ከውጪ ንግድ እየበለጠ ነው››1 ‹‹ከውጪ ንግድ ይልቅ ከቱሪዝም ዘርፍ ሚገኘው የውጪ ምንዛሪ እየበለጠ መሆኑን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አመለከተ፡፡ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር አክሊሉ ኃይለሚካኤል ባለፈው ዓመት የቱሪስት መስህቦችን ለማስተዋወቅ በተሠራው ሥራ 870 ሺ ቱሪስቶች ኢትዮጵያን  እንዲጎበኑ በማድረግ 3.3 ቢሊዮን ዶላር ማግኘት ተችሎል፡፡ ከዘርፉ የተገኘው ገቢ ባለፈው ዓመት ከውጪ ንግድ ከተገኘው 2.9 ቢሊዮን ዶላር ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ልዩነት እንዳለው ገልፀዋል፡፡››ከቱሪዝም የሚገኘው ገቢ ከውጪ ንግድ አይበልጥም የተሳሳተ መረጃ ነው፡፡ ከአገልግሎት ዘርፍ የሚገኘው ገቢ ከውጪ ንግድ እየበለጠ መሄዱን ግን በተጨባጭ መረጃ ማሳየት ይቻላል፡፡ የውጪ ንግድ የአገልግሎት ዘርፍ ገቢ (Export of Services) ከሚካተቱት ውስጥ (1ኛ) ቱሪዝም (2ኛ) የኢትዩጵያ አየር መንገድ   (3ኛ) የኢትዩጵያ ንግድ መርከብ (4ኛ) የኢትዩጵያ ቴሌኮም (5ኛ) የኢትዩጵያ ኤሌትሪክ ኃይል የአገልግሎት ዘርፍ ገቢዎች ይካተታሉ፡፡ (1ኛ) ሬሚታንስ   (2ኛ) ብድር   (3ኛ) ዕርዳታ በሰለጠኑት ዓለም ያሉ ሌሎች የአገልግሎት ዘርፍ ውስጥ (1ኛ) ሴክስ ቱሪዝም (2ኛ) የህክምና አገልግሎት (3ኛ) የትምህርት አገልግሎት (4ኛ) የፊልም ኢንዱስትሪ (5ኛ) የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ምርት ሽያጭ (6ኛ) ጌምና ልዩ ልዩ ሶፍት ዌሮች ምርቶች ሽያጭ (7ኛ) የመፅኃፍትና የኤሌክትሮኒክስ መፅሃፍት ሽያጭ (8ኛ) የኢንተርኔት ኢኮኖሚ አገልግሎት (9ኛ) የጠፈር ቱሪዝም (ለአንድ ሰው በመንኮራኩር ወደ ጠፈር ጉብኝት ለማድረግ 20 ሚሊዩን ዶላር ይከፈላል) ወዘተ  የአገልግሎት ዘርፍ ገቢዎች ናቸው፡፡ የብሄራዊ አማካይ ጠቅላላ አመታዊ ምርት (Real GDP) እድገት መገለጫዎች በሃገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች፣በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፎች አስተዎፅኦ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡

አገልግሎት ዘርፍ፤ የአየር፣ የየብስና ባህር ትራንስፖርት አገልግሎቶች፣ የቱሪዝምና ሆቴሎች፣የቴሌኮም፣የኤሌትሪክ ኃይል አገልግሎቶች ሽያጭ ወዘተ

ግብርናው ዘርፍ፤ ምርቶች የእህል፣የሰብል፣ካሽ ክሮፕስ፣ብና፣ሰሊጥ፣የቅባት እህሎች፣ አትክልትና ጥራጥሬ፣ የአበባ ምርት ወዘተ

ኢንዱስትሪው ዘርፍ፤ ምርትና ሸቀጦች የማዕድን ምርቶች፣(ወርቅ፣ ታንታለም፣ ብረት፣የሲሚንቶ ምርቶች፣ ወዘተ) የማኑፋክቸሪንግ ምርቶች ልብስና አልባሳቶች፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ የስካር፣ የዘይት፣ የዱቄት፣ የወተት፣ወዘተ ምርቶች በየአመቱ በምን ያህል አደጉ? ለስንት ሚሊዩን ሰዎች የስራ እድል ፈጠሩ?፣ የነፍስ ወከፍ ገቢቸውን በምን ያህል ብር በየአመቱ ጨመረ?፣ ለውጪ ንግድ ድርሻው በምን ያህል አደገ?፣ በየአመቱ ምን ያህል የውጪ ምንዛሪ ከዘርፎቹ ተገኘ? የሚለውን በመረጃ አስደግፎ መተንተን አስፈላጊ ይሆናል፡፡

ግብርናውን ዘርፍ ምርታማነትን በማሳደግ ትርፍ በማምርት ረቢ ኃብት (Capital) በማከማቸት ብቻ ነው የኢኮኖሚ እድገት፣ በምግብ ራስን መቻል፣ የሥራ እድል ፈጠራ፣ የውጪ ንግድ ገቢያችንን መጨመር የምንችለው፡፡ ከግብርና ከኢንዱስትሪ ሌላ ኃብት ማመንጫ የቱሪዝም ዘርፍ ነው፡፡በተባበሩት መንግስታት የዓለም ቱሪዝም ድርጅት (United Nations World Tourism Organization)ትርጉም መሠረት፣ ቱሪዝም ጎብኝ ተብለው በተለያዩ ሰዎች የሚፈፀም ድርጊት ነው፡፡ ጎብኚ በመደበኛነት ከሚኖርበት አካባቢ ተነስቶ ቢያንስ ለተወሰነ ጊዜት  ቆይታ  በዓልን ማክበር፣ ጊዜን ማሳለፍና መዝናናትን፣ ሥራን፣ ህክምናን፣ ትምህርትን፣ ጨምሮ ለተለያዩ ጉዳዬች  ወደሌላ መዳረሻ የሚጎዝ ሰው ማለት ነው፡፡ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣የሳይንስና የባህል ድርጅት-ዩኔስኮ (The United Nations Educational, Scientific And Cultural Organization-UNESCO) የተመዘገቡ የኢትጵያ ታሪካዊና ተፈጥሮዊ ቅርሶች አስራ አንድ ሲሆኑ እነርሱም፣ የአክሱም ሃውልቶች፣ የላልይበላ አብያተ ክርስቲያኖች፣ የጎንደር ፋሲል ግምብ፣ የሐረር ጆጎል ግንብ፣ የጢያ ትክል ድንጋዩች፣ የሰሜን ብሄራዊ ፓርክ፣ የኮንሶ ሰው ሰራሽ መልከዓ ምድር፣ የታችኛው አዋሽ ሸለቆና የታችኛው ኦሞ ሸለቆ፣ እንዲሁም በማይጨበጥ የባህል ቅርስነት የመስቀል የደመራ በዓልና የሲዳማ የዘመን መለወጫ ፊቼ ጨምበላላ ናቸው፡፡ ሌሎች ለመመዝገብ በሂደት ላይ ያሉም አሉ፡፡ የባሌ ተራራዎች ብሄራዊ ፓርክ፣ ድሬ ሽህ ሁሴን መስጊድ፣ ሶፍ ኡመር ዋሻ፣ የጌዲ ሰው ሰራሽና ተፈጥሮዊ መልክዓ ምድር፣ መልካ ኩንቱሬና ባቺልት አርኪሎጂ ስፍራዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ከባህላዊ ቅርሶች ደግሞ የኦሮሞ ገዳ ሥርዓት፣የትግራይና የአማራ ክልሎች የአሸንዳና የሻደይ በዓላትንም የማስመዝገብ እቅድ አለ፡፡ በአጠቃላይ ተፈጥሮዊ መስህቦችን፣ ሃያማኖታዊ በዓላትን ባህላዊ ትውፊቶችን፣ የዱር እንሰስትን ሃብትና ሌሎችንም ቱሪዝም መዳረሻዎች ሥፍራዎች ያጠቃልላሉ፡፡ የኤርታአሌ የእሳተ ገሞራ ሀይቅና የዓለማችን እጅግ ረባዳና ሞቃት ስፍራ ዳሎል፣ የሙሴ ፅላት በአክሱም ፅዩን ቤተክርስቲያን፣ የሉሲ ወይም ድንቅነሽ አፅም ከ3 ሚሊዩን ዓመታት በላይ እድሜ ያስቆጠረው፣ የአለማችን ረጅሙ ወንዝ ጥቁር አባይና መነሻው ጣና ሃይቅ፣ በርካታ የስምጥ ሸለቆ ሃይቆችና ፍል ውኃዎችና የዱር እንሰሳት ፓርኮች ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያ ከ1974/75 እኤአ እስከ 2013/14 እኤአ ባሉ ዓመታት ውስጥ የጎብኝዎች ቁጥርና በኢትዮጵያ ዓየር መንገድ የተጎጎዙ ደንበኞች ቁጥር በመረጃ ይቀርባል፡፡ Foreign visitor arrivals – the number of arrivals of foreign visitors, including same-day and overnight visitors (tourists) to the country

Appendix F: Descriptive Statistics of Major Variables

Year ዓመታት ፣ VISITORS የጎብኝዎች ቁጥር፣ PASSENGER ዓየር መንገድ የተጎጎዙ ደንበኞች ቁጥር

Year 1974/75 1975/76 1976/77 1977/78 1978/79 1979/80 1980/81 1981/82 1982/83 1983/84 1984/85 1985/86 1986/87 1987/88
VISITORS 20355     22302     24436     26774     29336     32143     35219     38589     42281     46327     50759     55616     60938     66768    
PASSENGER 212357 181756 218574 149034 100253 102439 137489 210588 205411 213317 238750 293537 330286 375183
Year 1988/89 1989/90 1990/91 1991/92 1992/93 1993/94 1994/95 1995/96 1996/97 1997/98 1998/99 1999/00 2000/01 2001/02
VISITORS 73157     80157     79495     82333     85139     95197     100308    105695    111371    125975    101437    131242    142791    151281   
PASSENGER 349591 381048 320863 326854 456963 475808 409814 427639 448097 410301 413666 563668 638154 481735
Year 2002/03 2003/04 2004/05 2005/06 2006/07 2007/08 2008/09 2009/10 2010/11 2011/12 2012/13 2013/14 2014/2015 2016/17
VISITORS 161676    185214    195785    274375   293745   322865   356411   460640   508995   537269   633263   633245   870000
PASSENGER 545238 561787 782885 1015041 1056750 1589450 1881656 2085820 2419660 3282376.7 3703604.9 3949154.4

‹‹ኢትዩጵያ በጎብኒዎች ቁጥር ከአፍሪካ 18ኛ ከዓለም 121ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡!!!››  

አዲስ ዘመን ጋዜጣ የወጣዉን የተጣረሰ መረጃ ከዓለም አቀፍ የቱሪስት መረጃ ማገናዘብና የባህር ማዶ ጎብኝዎችንና በኢትዮጵያ ዓየር መንገድ የተጎጎዙ ደንበኞች በመረጃው ያገናዝቡ፡፡  

  • በ2004 ዓ/ም ኢትዩጵያን የጎበኙ ቱሪስቶች ቁጥር 561 ሽህ 787 ሲሆን ከዘርፍ 1.2 ቢሊዩን ብር/ዶላር ገቢ ተገኝቶ ነበር፡፡
  • በ2006 ዓ/ም በጀት አመት ኢትዩጵያ የጎበኙ ቱሪስቶች ቁጥር 600 ሽህ ሲሆን ከዘርፍ 2.5 ቢሊዩን ብር/ዶላር ገቢ ተገኝቶ ነበር፡፡

በ2008 ዓ/ም በጀት አመት ኢትዩጵያ የጎበኙ ቱሪስቶች ቁጥር 911 ሽህ ሲሆን ከዘርፍ 3.4 ቢሊዩን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ገቢ ተገኝቶል፡፡ 3.4 ቢሊዩን ዶላር ሲባዛ 23 ብር ይሆናል 69 ቢሊዩን 92 ሚሊዩን ብር ነበር፡፡ ይህ ገቢ ሃገሪቱ በውጭ ንግድ ከምታገኘው ገቢ የላቀ መሆኑ ይስተዋላል፡፡2

  • ‹‹በአሁኑ ወቅት የቱሪስት ፍሰት በአንድ ወር በአማካይ እስከ 88 ሺ እንደሚደርስምና የቆይታ ጊዜውም እስከ 16 ቀናት መሆኑን አቶ ገዛህኝ አባተ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አመልክተዋል፡፡ በጉብኝት፣በንግድ፣በኤግዚቪሽን፣ በኮንፍረንስ፣ዘመድ ጥየቃና በተለያዩ ምክንያቶች ወደ አገሪ የሚመጡ የውጭ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ለዘርፉ ማደግ አስተዋፅኦ ማድገጉን ጠቅሰዋል፡፡ በአሁኑ ወቅትም በአገልግትና በተለያየ የግንባታ ደረጃ  ላይ የሚገኙ ደረጃቸውን የጠበቁ 700 ሆቴሌች እና 460 አስጎብኝ ድርጅቶች መኖራቸውን ገልፀዋል፡፡››3
  • በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ማብቂያ ዘመን ላይ በአፍሪካ በቱሪስት መዳረሻነት 5ኛ ደረጃ ላይ ለማድረስ ግብ ተጥሎል፡፡ በዚህ መሰረት የቱሪዝምን ዘርፍ ለማልማት ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የኢትዩጵያ ቱሪዝም ድርጅትና የኢትዩጵያ ቱሪዝም ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት ተቆማት ተቆቁመዋል፡፡ ከአፍሪካ አገራቶች ውስጥ 18 ደረጃ ላይ የምትገኝና ገና አንድ ሚሊዩን ጎብኝዎች ያላስተናገደች ሃገረ-ኢትዩጵያ  በቱሪዝም እንዴት 5ኛ ደረጃ ለመድረስ ይቻላታል፡፡ ወያኔ ጦር በገደላ በአፍሪካ 1ኛ ደረጃ ላይ እያለ!!!

በ2004 ዓ/ም አፍሪካን ከጎበኙት 52.3 ሚሊዩን ቱሪስቶች ሲሆኑ ከዘርፉ  34 ቢሊዩን ዶላር ገቢ ተገኝቶ ነበር፡፡ ኢትዩጵያ በጎብኒዎች ቁጥር ከአፍሪካ 18ኛ ከዓለም 121ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ የጎብኒዎች ቁጥርን ለመጨመር በሃገሪቱ ውስጥ ዴሞክራሲና ሠላም ዋነኛ መሠረት ናቸው፡፡ የወልዲያ ወጣቶች ቃና ዘገሊላ በሚያከብሩበት ዕለተ ቀን በአጋዚ ጦር ሰዎች እንደከርከሮ ከተገደሉ ቱሪስት አይመጣም፡፡ በኦሮሚያ የእሬቻ  በዓል ሰዎች በግፍ በመገደላቸው ቱሪስት አይመጣም፡፡ ወያኔ የሃገሪሩን ገፅታ ያጨለመው በዚህ የተኮላሸ ሥራው ነው፡፡ 

Table 7.5.a: Arrivals of non-resident tourists at the border (1000)

አገራት 2004 2006 2008 2010 2011 2012 2013
ግብፅ 7,795 9,083 12,835 14,731 9,845 11,532 9,192
ሞሮኮ 5,477 6,777 8,209 9,752 9,834 9,800 9,943
ደቡብ አፍሪካ 6,678 6,259 7,157 8,074 8,339 9,188 9,515
ቱኒስያ 5,998 7,176 7,750 7,715 5,451 7,635
ናይጀሪያ 962 3,056 5,820 6,113 6,078 6,516

                  (Source: Statistics Division,AUC) The European Union and the African Union 2014 edition

  • ከአፍሪካ አገራቶች፣ ቱሪስቶች ከ5 ሚሊዩን በላይ ጎብኝዎች በማስተናገድ የሚታወቁ አንደኛ ግብፅ፣ ሁለተኛ ሞሮኮ፣ ሦስተኛ ደቡብ አፍሪካ፣ አራተኛ ቱኒስያ አምስተኛ ናይጀሪያ ናቸው፡፡ 
  • ከአፍሪካ አገራቶች፣ከ1 እሰከ 3 ሚሊዩን በላይ ጎብኝ ቱሪስቶች ያስተናገዱ 13 የአፍሪካ ሃገራት ውስጥ አልጀሪያ፣ቤኒን፣ቦትስዋና፣ጋና፣ኬንያ፣ሞሪሽየስ፣ሞዛንቢክ፣ናሚቢያ፣ርዋንዳ፣ሴኒጋል፣ስዋዚላንድ፣ኡጋንዳ፣ዚንባዌ ናቸው፡፡
  • ከአፍሪካ አገራቶች፣ከ1 ሚሊዩን በታች ጎብኝ ቱሪስቶች ያስተናገዱ 36 የአፍሪካ ሃገራት ውስጥ፣ አንጎላ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ብሩንዲ፣ ካሜሩን፣ ኬፕቭርዴ፣ ሴንትራል አፍሪካ ሪፓብሊክ፣ ቻድ፣ ኮሞሮስ፣ ኮንጎ፣ ኮንጎ ዴክራቲክ ሪፓፕሊክ፣ ኮትዲቮር፣ ጅቡቲ፣ ኢኮቶሪያል ጊኒ፣ ኤርትር፣ኢትዩጵያ፣ጋቦን፣ ጋምቢያ፣ ጊኒ፣ ጊኒቢሳው፣ ሌሴቶ፣ላይቬሪያ፣ ሊቢያ፣ ማዳጋስካር፣ ማላዊ፣ ማሊ፣ ሞሪታንያ፣ ኒጀር፣ ሳዎቶሜና ፕሪንሲፒ፣ ሽሴልስ፣ ሴራሊዩን፣ ሶማልያ፣ ሳውዝ ሱዳን፣  ሱዳን፣ ታንዛኒያ፣ ቶጎ፣ ዛምቢያ ናቸው፡፡

የቱሪዝም ዘርፍ አስተዋፅኦ፣ {1} የውጭ ምንዛሪ ምንጭነት፣ ቀጥተኛ አስተዎፅኦ አመታዊ አጠቃላይ ብሄራዊ ምርት(ጂዲፒ) Direct contribution to GDP ከዚህ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚመነጨው በቀጥታ ከቱሪስቶች፣በተጨማሪም ከሆቴሎች፣ አስጎብኝ ድርጅቶች፣አየር መንገዶችና ሌሎች የትራንስፖርት አገልግሎቶች እንዲሁም ሬስቶራንቶችና የመዝናኛ ኢንዱስትሪዎች በቀጥታ ከቱሪስቶች ጋር የተያያዙ ዘርፎች ያካትታል፡፡ Direct contribution to GDP – GDP generated by industries that deal directly with tourists, including hotels, travel agents, airlines and other passenger transport services, as well as the activities of restaurant and leisure industries that deal directly with tourists. It is equivalent to total internal Travel & Tourism spending (see below) within a country less the purchases made by those industries (including imports). In terms of the UN’s Tourism Satellite Account methodology it is consistent with total GDP calculated in table 6 of the TSA: RMF 2008.

                         {2} ለዜጎች የስራ እድል፣  በግብርናውና ኢንዱስትሪ  ዘርፎች  ከሚገኘው የውጭ ንግድ ገቢ የአገልግሎት ዘርፍ ገቢ መብለጡ በግብርና ዘርፍ የተሰማራው 80 በመቶ የሰው ኃይልና የተፈጥሮ ኃብት ማለትም መሬትና የእንሰሳት ኃብት አጠቃቀም  በውጭ ንግድ ገቢ የተገኘው ገቢ ዝቅተኛ መሆን በዘርፉ ብዙ መሠራት እንዳለበት አመላካች ነው፡፡ በተመሳሳይም በኢንዱስትሪ  ዘርፍ የተሰማራው የሰው ኃይልና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ ብዙ ፋብሪካዎችና የኢንዱስትሪ ዞኖች በውጭ ንግድ ገቢ ያስገኙት ዝቅተኛ መሆኑ ያሳያል፡፡

የቱሪዝም ዘርፍ፣ ተግዳሮቶች የቱሪስቶች መታቀብ በኢትዩጵያ ከ2008ዓ/ም ጀምሮ የተቀሰቀሰው ህዝባዊ አብዮት፣ በኦሮሞ የአንገዛም እንቢተኛነት ትግልና በአማራ ተጋድሎ ቀጥሎም በኦሮሞ ቄሮዎችና በአማራ ፋኖዎች ህዝባዊ አመጽ የተነሳ የሃገር ጎብኝዎች ቁጥር በመቀነሱ በቱሪዝም ዘርፍ ይገኝ የነበረው ገቢ ቀንሶል፡፡ ሃገር ውስጥ በሆቴልና ቱሪዝም የሚገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢ ቱሪስቶች ሰላም ከሌለ ስለማይመጡ ነጥፋል፡፡

የሆቴሎችና ቱሪዝም ዘርፍ ተግዳሮቶች ‹‹የአዲስአባባ ሆቴሎች በአስቸካይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት የ380 ሚሊዮን ብር ኪሳራ  እንደደረሰባቸው ይፋ አደረጉ››5 በአዲስ አበባ የሚንቀሳቀሱ ሆቴሎች በአገሪቱ በተከሰተው ህዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት በታወጀው አስቸካይ ጊዜ አዋጅ ይህንን ተከትሎ አገሮች ባወጡት የጉዞ ክልከላና ማስጠንቀቂያ ሣቢያ በዚህ በጀት አመት ብቻ የ380 ሚሊዩን ብር ኪሣራ አንዳጋጠማቸው  አስታወቁ፡፡›› በአዲስ አበባ ከሚገኙ150 ሆቴሎች ውስጥ 105ቱ የሚወክሉበት የአዲስአበባ ሁቴሎች ባለንብረቶች የዘርፍ ማህበር ኃላፊዎች፣ ሚያዝያ 11 ቀን 2009 ዓ/ም በሰጡት መግለጫ መሠረት በአገሪቱ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ የታወጀው አስቸካይ ጊዜ አዋና አገሮች ያወጦቸው የጉዞ ክልከላዎች ባደረጉት ጫና ምክንያት ሆቴሎች ከዚህ ቀደም ነበራቸውን የ67 በመቶ የክፍል ተከራዩች ቁጥር በአማካይ በ20.5 በመቶ እንዲቀንስባቸው  ምክንያት ሆኖል፡፡ በቱሪዝም መስክ የደረሰውን ጉዳት ያባባሰው ግን አገሮች ዜጎቻቸውን ወደ ኢትዩጵያ እንዳይጎዙ የሚከለክሉና የሚያስጠነቅቁ ማሳሰቢያዎችን ማውጣታቸው ነው፡፡ በዚህም የተነሳ የሆቴሎች የማህበር ዘርፍ መንግስትን ከጠየቁት ውስጥ አንደኛ፣ በዚህ በጀት ዓመት መክፈል የሚጠበቅባቸውን የንግድ ትርፍ ግብር እንዲነሳላቸው  ሁለተኛ አብዛኞቹ ሆቴሎች ያለባቸውን የባንክ እዳ ከነወለዱ የመክፈያ ጊዜ በአንድ ዓመት እንዲራዘምላቸው ሦስተኛ የደረሰውን ኪሳራ የሚያካክስ ገንዘብ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡ በአገሪቱ የግንባታ ሂደት ላይ የሚገኙ ከ100 ያላነሱ ሆቴሎች እንደሚገኙ ከእነዚህም ውስጥ እስከ 25 በመቶ የሚገመቱት ዓለም ዐቀፍ ብራንድ ያላቸው የውጪ ሆቴሎች ግንባታ በተለያዩ ችግሮች የተነሳ ተቀዛቅዞል፡፡ 

ለውጪ ንግድ ማሽቆልቆል ከተጠቀሱት ምክንያቶች በህገወጥ መንገድ የወርቅ ማዕድን ምርት፣ የቁም እንሰሳት ሃብት እንዲሁም በርካታ የግብርና ምርቶች የጫት ንግድ፣ ድንበር አቆርጠው የሚወጡ በመሆናቸው፣እንዲሁም ከድንበርተኛ ሃገሮች ወደ ኢትዩጵያ የሚገቡ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በህወኃት የጦር አበጋዞች መንግስት ጀነራል መኮንኖች፣የደህንነት ሰዎች፣ የፖለቲካ ካድሬዎች፣ የክልል መንግስታት ሹማምንትና ካድሬዎች አማካኝነት በመሆኑ በሃገሪቱ ፍትሃዊ የንግድ ስርዓት አለመኖር፣ የቢሮክራሲ ውጣ ውረዶች፣በግብዓት አቅርቦት፣ በጥራት ችግር፣ ገዥ ኩባንያዎች በተለያዩ ምክንያቶች ውል በመሰረዛቸው  እንደሆነ ሲታወቅ በዋናነት  የኦሮሚያ ህዝባዊ እንቢተኛነትና የአማራ ህዝብ ተጋድሎ፣ የደቡብ ህዝብ አመፅ ወዘተ ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው፡፡ የንግዱ ህብረተሰብ ላይ የተጫነው ግብር ድንበር ዘለል ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴ እስካልተገታ፣የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ወደ ሃገር ውስጥ መግባት እስካልቆመና ፍትሃዊ የንግድ ስርዓት በእኩልነት፣በፍታዊነትና በህግና ደንብ እስካልተከወነ ድረስ ህዝቡ ለወያኔ ዘረኛ ፋሽስታዊ አገዛዝ ግብር መገበር አይጠበቅበትም፡፡  

አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ የእርነስትና ያንግ ተባባሪ ሥራ አስኪያጅ የነበሩ፣  በሃገሪቱ በተነሳው የኦሮሞ የአንገዛም እንቢተኛነት ትግልና የአማራ ተጋድሎ ምንም ችግር አያስከትልም ኢንቨስተሮችም ቱሪስቶችም ወደ ሃገራችን ይመጣሉ በማለት ፍርደ ገምድል ካድሬዊ አድርባይነታቸውን በቃለ ምልልስ ገልፀው ነበር፡፡ ‹‹በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ኢትዩጵያ የኢንዱስትሪዎች መጠለያ እንደምትሆን እጠብቃለሁ››(እሁድ ሀምሌ 5 ቀን 2007 ዓ/ም ሪፖርተር ጋዜጣ ቃለ መጠይቅ) ‹‹የውጭ ኢንቨስተሮች ከወቅታዊ ችግሮች ባሻገር ዘላቂ ዕድሎችን ይመለከታሉ›› (ሐምሌ15ቀን 2008ዓ/ም ሪፖርተር ጋዜጣ) እኤአ በ2012/13 ኢትዩጵያ ከአቪዬሽን አገልግሎት 3.2 ቢሊዩን ዶላር አግኝታለች፡፡ (ሐምሌ  ቀን 2007 ሪፖርት ጋዜጣ) ሪፖርትር ጋዜጣ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ መጠቀሚያነት አንዴ በቱሪዝም 3.2 ቢሊዩን ዶላር ተገኘ ብሎ ይፅፍና ሌላ ጊዜ ደግሞ ከአቪዬሽን አገልግሎት 3.2 ቢሊዩን ዶላር ተገኘ ቀጥሎም በኢትዮጵያ አየር መንገድ አልያም በአገልግሎት ዘርፍ 3.2 ቢሊዩን ዶላር ተገኘ በማለት የተደጋገመ ውሸት በሪፖርተር ጋዜጣ በማተም የተጣረሰ የኢኮኖሚ መረጃ በመስጠት ህዝብና ይቀጥፋል፡፡

የቱሪዝም ዘርፍ ገቢ መቀነስ ዋና ዋናዎቹ ምክንያቶችም ከ2008ዓ/ም ጀምሮ መንግስት የደነገገው የአስቸካይ ግዜ አዋጅ ዘርፍን የበለጠ ተፅዕኖ ውስጥ መክተቱ፣ እንዲሁም ዲፕሎማቶች ካማንድ ፖስቱ ሳያሳውቁ እንዳይጎዙ መታገድ፡፡ በግጭቱ ወቅት በብሄራዊ ፓርኮች፣ በሎጆችና በሪዞርት ሆቴሎች ላይ በአብያታ ሻላ ብሄራዊ ፓርኮች፣ በባሌ ብሄራዊ ፓርክ በዙሪያቸው የሚገኙ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቆማት መውደም፡፡ ‹‹ለመገንባት አስር አመት፣ ለማቃጠል አንድ ሰዓት!!!›› ስለሆነ ችግርን በጠረጵዛ ዙሪያ በዴሞክራሲያዊ መንገድ መፍታት የሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን አማራጭ የሌለው መንገድ ነው፡፡ በተጨማሪም መንግስት በመላ ሃገሪቱ የጣለው የኢንተርኔትና የማህበራዊ ሚዲያዎች መረቦች መዘጋታቸው፣ የቱሪስቶችን ፍሰትና ገቢ ቀንሶታል፡፡ ከ2009 እስከ 2010ዓ/ም የኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ ገቢ ተሸመድምዶል፣ ወያኔ የሃገሪቱን ገፅታ በወጣቶች ርሸናና ስብዓዊ መብት ረገጣ አጨልሞታል፡-የእሬቻ በአል አከባበር የዜጎች ገደላ የተነሳ የባህር ማዶ ጎብኝዎች ወደ ኢትዮጵያ  እንዳይገቡ አድርጎል!!!  የወልዲያ ቃና ዘገሊላ በአል አከባበር የተነሳ በቀጣይነት የባህር ማዶ ጎብኝዎች  ወደ ሃገራችን እንዳይገቡ ያደርጋል፡፡ በአፋር አርተሌ የቱሪስቶች ሞት የተነሳ ጎብኝዎች  ወደ ሃገራችን እንዳይመጡ ያደርጋል፡፡ የተለያዩ አገራቶች መንግሥታት የአሜሪካን፣ ካናዳ፣ የአውሮፓ መንግስታት በተደጋጋሚ ዜጎቻቸውን ወደ ኢትዩጵያ እንዳይሄዱ ሲመክሩና መግለጫ ሲያወጡ  ቆይተዋል፡፡ ይህም ለዘርፉ ትልቅ አደጋ አስከትሎል፡፡ የውጭ ምንዛሪውም ነጥፎል፡፡

ጋዜጣዊ ሥነ-ምግባር የሌላቸው ውሸታም ምላሳዊ ጋዜጠኞች ለአንዴም ለሁሌም በኢትዮጵያ ምድር ንስሃ የሚገቡበት የትሃድሶ ዘመን ይመጣል፡፡ የወያኔ ካድሬ ጋዜጠኞች ዘመን ያበቃል፡፡ ሃቀኛ የህዝብ ልጆች የሆኑ ጋዜጠኞች እስክንድር ነጋ የመሳሰሉት በእስር ቤት ይወጣሉ፣ ብዙዎቹም ከስደት ይመለሳሉ፡፡ የህወሓት አንባገነን መንግስት በጠመንጃ አፈሙዝ ለ27 ዓመታት እየገደለና እያሰረ በኃይል ገዛ፡፡  ህወሓት  አግአዚ ጦር ሠራዊት የህዝብ ልጆችን እየገደለ የትግራይ ህዝብ እንዲጠላ አድርጎል፡፡ በአመዛኙ ከትግራይ የተመለመሉት የአግአዚ ጦር ሠራዊት ለትግራይ ህዝብ መጠላት፣ ገዳያችን የትግራይ ጦር ሠራዊት ናቸው ህዝቡ እንዲል አድርጎታል፡፡ የትግራይ ህዝብ ይህን በመቃወም ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር አጋርነቱን መግለፅ ይጠበቅበታል፡፡ የአግአዝ ገዳዮች ለፍርድ እንዲቀርቡ መጠየቅ ታሪካዊ የኢትዮጵያዊነት መገለጫና የሃገርና ወገን አሌንታነት ማሳያ ነውና!!!  የሃገራችን ህዝብ በሰላም፣ በእኩልነትና ፍትህ በአንድነት በፍቅር ይኖራል፡፡ ዴሞክራሲ ያብባል፣ ህዝባዊ  መንግስት ይመሠረታል፡፡  

የወያኔ መንግሥታዊ ነጭ ሽብር በህዝባዊ አመፅ ይከሽፋል!!!   ብሄራዊ የፖለቲካ ጠቅላይ መምሪያ ይቆቆም!!!

ለኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ፣ ለኢትዮጵያዊያን የጋራ ግበረ ኃይል፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ፣ ለኢትዮጵያውያን ተጋሩ፣ ለሁሉም ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራቶች፡- የህወሓት/ ኢህአዴግ ፋሽስታዊ መንግሥት የአግዓዚ ጦር መንግሥታዊ ነጭ ሽብር ቀጥሎል፣ የኢትዮጵያዊያንን ህዝባዊ ትግል በጠመንጃ አፈሙዝ ለማፈን ግን ጭራሽ አይቻለውም፡፡ ፋሽታዊው የአግዓዚ ጦር  ነፍሰበላ ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ፣ የአግዓዚ ጦር ትጥቅ ፈትቶ በመከላከያ ሠራዊት ይተካ ፡፡ ይህንን ትግል ከዳር ለማድረስ ሃገር አቀፍ ትግል ግድ ይላል፣ ትግሉን የምትመሩ ድርጅቶች የሦስት ቀን የቤት ውስጥ መቀመጥ አድማ፣ በመላ ሃገሪቱ እንድትጠሩ እንጠይቃለን፡፡

የህወሓት አግአዚ ጦር ሠራዊት ለፍርድ ይቅረቡ!!! ክብር  ለተሠው ኢትዮጵያውያን ሠማዕታት ይሁን!!!   በአንድ ላይ በህብረት እንነሳ!!! 

ምንጭ

{1}አዲስ ዘመን ጋዜጣ ጥር 9 ቀን 2010ዓ/ም

{2} ነሐሴ 27 ቀን 2008ዓ/ም አዲስ ዘመን ጋዜጣ

{3} ሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ/ም አዲስ ዘመን ጋዜጣ

{4} ጥቅምት 2 ቀን 2010 ዓ/ም አዲስ ዘመን ጋዜጣ

{5} ሚያዝያ 15 ቀን 2009ዓ/ም ሪፖርተር ጋዜጣ