የአጼ ቴዎድሮስ ሀውልት በደብረታቦር ከተማ ተመረቀ

0

አባይ ሚዲያ ዜና
አቢሰሎም ፍሰሃ

በደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ በሁለት ሚሊዮን ብር የተገነባው የአጼ ቴዎድሮስ ሀውልት 7.5 ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን ዛሬ ጥር 29, 2010 ዓ.ም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ያለው አባተ፣ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ሂሩት ካሳው እና ብዛት ያለው ህዝብ በተገኘበት ተመርቋል፡፡

ታሪካዊቷ የደብረታቦር ከተማ የነገስታት መናገሻ በመሆን ለረዥም ጊዜ እንዳገለገለች ይታወቃል። ንጉስ ወልደጊወርጊስ፣ ራስ ጉግሳ እና አጼ ቴዎድሮስ ይህችን ከተማ መርጠው ለመናገሻነት ተገልግለውባታል።

እንደ አውሮፖውያኑ አቆጣጠር በ1818 የተወለዱት አጼ ቴዎድሮስ ከ1855 ህይወታቸው እሰካለፈበት 1868 ድረስ ለኢትዮጵያ ንጉስ ሆነው ስማቸውን ከመቃብር በላይ እዲኖር ያበቋቸውን በርካታ ስራዎችን ለሃገራቸው የሰሩ ቆራጥና ዘመናዊ መሪ ነበሩ።

በደብረታቦር ከተማ በአጼ ቴዎድሮስ ስም ት/ቤቶች አደበባይና የመሳሰሉት ተሰይመው እንደሚገኙ ይታወቃል። አጼ ቴዎድሮስ ለውጭ ወራሪ መመከቻ ያሠሩት የሴባስቶፖል መድፍ የተሠራውም ከከተማዋ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ህሩይ ጊወርጊስ እንደነበር ታሪክ ያሳያል።