የሞቱ አህዮች ጅብ አይፈሩም! የተሰኘው ፊልም ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ሊመጣ ነው

0

አባይ ሚዲያ ዜና
ጋሻው ገብሬ

የደሃ አርሶ አድሩን በደል እናሰማ። የዲፕሎማሲ ትግላችን በአገራችን ወያኔ የሚያሰቃየውን ገበሬ ድምጽ ማሰማት ነው።

ሰለ ጋምቤላ ህዝብ በደል የሚያስረዳው “የሞቱ አህዮች ጅብ አይፈሩም”

“የሞቱ አህዮች ጅብ አይፈሩም” የሚለው በስዊድናዊው የፊልም ድሬክተር ጆ አኪም ዴመር የተዘጋጀው ነባራዊ ሁኔታን ገላጭ የፊል ስራ በዓለም ዝናን አፍርቷል። ይህ ስለ ጋምቤላ ውስጥ ህወሃት መሩ መንግስት ደሆችን እያፈናቀለ ለውጭ ከበሬቴዎች ስላደለው መሬት የሚናገረው ፊልም ዛሬ በዓለማችን ያለውን ህወሃት “እድገት” እያለው የሚያወራውን “የመሬት ቅሚያ” የሚያጋልጥ ነው።

በአውሮፓ 250 ጊዜ በላይ የታየውና ሁለት ትላልቅ ሽልማቶችን በአውሮፓ ያገኘው የስዊድናዊው ድሬክተር ጆ አኪም ዴመር የስራ ውጤት የህወሃት መንግስትን ብልሹ ስራት ከሚታገሉ ቆራጥ ኢትዮጵያውያ ጋዜጠኞችም ጋር በመተባበር የተስራ ነው። ፊልሙ በጋምቤላ ብቻ ሳይሆን በመላው ኢትዮጵያ በኢንቬትመንት ስም ስለተፈናቀለው አርሶ አድረና ስለወድመው ያገር ንብረት የሚናገር ነው።

“የሞቱ አህዮች ጅብ አይፈሩም” ደሃውን የጋምቤላ ህዝብ በማን አለብኝነት የህወሃት ባለስልጣናትና ዛሬ በሳውዲ አረብ ወህኒ ከወረደው ሼክ መሀመድ አል አሙዲ ሲመዘብሩት ለመኖራቸው ታሪካዊ ማስረጃ ነው ይላሉ ስለ ፊልሙ የሚናገሩ ኢትዮጵያውያን እና ሆኑ የውጭ አገር ሰዎች።

ህወሃት መሩ መንግስት ህዝቡን ከኑሮው ማፈናቀል ብቻ ሳይሆን የአገር ንብረት የሆነው ደንም ባላዋቂነት ከውጭ ከበርቴዎች ጋር ሲያወድመው “የሞቱ አህዮች ጅብ አይፈሩም” ፊልም ገልጾ አሳይቷል።

“የሞቱ አህዮች ጅብ አይፈሩም” በመጪው ማርች ወደ ዋሽግቶን ዲ ሲ በድጋሚ መጥቶ ለህብረተሰባችንን እና ኢትዮጵያ ጉዳይ ደጋፊዎች አሜሪካውያን እንደሚታይ ዜና ደርሶናል።

የኢትዮጵያ ወዳጆች የሆኑ አሜሪካውያን አብረውን እንዲያዩ ብናደርግ የደሀውን በደል አሰማን ማለት ነው።

Date: March 8, 2018
 8:00 PM
Avalon Theater
5612 Connecticut Avenue, NW, Washington, DC 20015