እንቁልልጭ ዶላር እንቁልልጭ ዩሮ (ግርማ ቢረጋ)

0

እንቁልልጭ ወዮ እኔ አልክም ዩሮ፣
አላስገድለውም ወገኔ ነው ቄሮ ።

በፍፁም አታገኝ እኔ አልክም ብር፣

አልሰጥህም እኔ ሲያምርህ ይቅር ፣
በቃ አታገኘውም እኔ አልልክም ዶላር፣
አማራም አይሞትም እውነቴን ነው ከምር።

ከቶ አታገኘውም ጨከንኩ ዩሮ የለም፣

ንፁህ ወገኖቼን በግፍ መግደል ማለም።
ቁርጥህን እወቀው እኔ አልልክም ብሬን፣
አተርፋለው እኔም ደሙን የወገኔን።

እኔ አልሰጥም በቃ ብሬን ለጠመንጃ ፣

ከእንግዲህ ወያኔ መግቢያህንም እንጃ።

እንቁልልጭ ዶላር እንቁልልጭ ዩሮ፣

ወያኔ አበቃልህ የአኩኩሉ ኑሮ።

2018

ስቶክሆልም